ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ምንጮች አስታወቁ። እስረኞች የደንብ ልብስ እንዲለብሱ የሚገደዱት ወደ ቤተሰብ ሲወጡና ተነስተው ሲዘዋወሩ ብቻ ቢሆንም፣አሁን ግን የተኙ እስረኞች ሳይቀር የደንብ ልብስ አለበሳችሁም እየተባሉ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ እና የአመክሮ እስራት ጊዜ እንዲቀሙ ተደርገዋል። ማንገላታቱ እና አካላዊ ጥቃቶች ከሚፈጸምባቸው መካከል የፖለቲካ እስረኞች በቀዳሚነ ተርታ ይመደባሉ። እነዚህ እስረኞቹ ተለይተው ከፍተኛ ድብደባ ይፈፀምባቸዋል፣ ከፍተኛ ክትትል ይደረግባቸዋል፤ ካለጥፋታቸው ከአልጋ ወርደው መሬት ወለል ላይ እንዲተኙም ይደረጋሉ። በእስር ቤቱ የፍርደኞች ክፍል በተለምዶ 6ኛ ቤት በመባል በሚጠራውና አምስት ክፍሎች ባሉት ክፍሎች የሚፈጸመው ሰቆቃ ከሁሉም የከፋ ሲሆን የጸሃይ ብርሃን እንዳያገኙም ይዘጋባቸዋል። ታንከር በመባል በሚታወቀው ክፍል የሚገኙት እነ ኮሎኔል ደምሰው አንተነህ እንዲሁም በዞን አራት የሚገኙት እነ ዶክተር መረራ
Thursday, June 29, 2017
ህወሃት በዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚሃብሄር በኩል በአማራ ክልል ፖሊስ አዛዦች ላይ ምርመራ ጀመረ
ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ በክልሉ ከታየው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በሁዋላ የታየው የፖሊሶች አቋም፣ ለህወሃት ህልውና አደገኛ ነው በሚል እምነት፣ ራሱ በሚመራው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት እየገመገመ ስራቸውን እንዲለቁ፣ ወንጀል ስርተዋል እያለ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ካደረገ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ዋና ዋና በሚባሉት የፖሊስ አዛዦች ላይ በህወሃቱ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር በሚመራው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት አማካኝነት ክስ ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀምሯል። የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች ከሆኑት መካከል ዋና ኮሚሽነር ሙሉጌታ ወርቁ እና ረዳት ኮሚሽነር ደስየ ደጀን የተባሉት አዛዦች፣ ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ከፍትህ ሚኒስቴር ቢሮ በመጣ ደብዳቤ ተጠርተው ሚስጥራዊ የሆነ ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን፣ የምርምራ መዝገብም ተከፍቶባቸዋል። የምርመራ መዝገቡ በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በቅማንት ማህበረሰብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው። በወቅቱ
Tuesday, June 27, 2017
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ መልሱን የሰጠው ኢሳት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና የምዕራብ ጎጃም ዞን የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ኮማንደር በላይ ካሴ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በማስመልከት ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ ነው
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ መልሱን የሰጠው ኢሳት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና የምዕራብ ጎጃም ዞን የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ኮማንደር በላይ ካሴ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በማስመልከት ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ማህበራዊ ሚዲያ አራማጆች የአማራ ክልል ኪሚሽን ስራ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና ኮማንደር በላይ ካሴ በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ለመቀጠል እንደሚቸገሩና እንደለቀቁ መዘገቡ የሃሰት ወሬ ነው ብሎአል። ይህን ይበል እንጅ ኮሚሽኑ ሁለቱም ሰዎች ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ለመደበቅ አልቻለም። ኮሚሽኑ “ኮማንደር አሰፋ የለቀቁት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰብአዊ መብት ምርምራና ክትትል ዳይሬክቶሬት ሆነው በመሾማቸው ነው” ብሎአል። ኮማንደር አሰፋ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲሰሩበት ከነበረውና ቦታ ወርደው ስሙ ብዙም የማይታወቅ የአንድ ከተማ የሰብአዊ መብት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲሰሩ መደረጉ ፣ እንዴት ተሾሙ ሊባል እንደሚችል ፖሊስ በመግለጫው አላብራራም። የዜናው ምንጮች በፖሊስ የቀረበውን ማስተባበያ አሳፋሪ ብለውታል። የክልሉን ፖሊሶች በበላይነት ሲመራ የነበረው ሰው፣ ስራውን ከእንግዲህ አልፈልግም ብሎ ሲለቅና ዜናው በኢሳት ከተሰራጨ በሁዋላ፣ በአንድ ከተማ የሰብአዊ መብት ደርጅት ውስጥ እንዲወሸቅ አድርገው፣ “ሹመት ሰጠነው እንጅ ስራውን አልለቀቀም” በማለት ለመካድ መሞከራቸው ለህዝቡ ያላቸውን ንቀት ያሳያል ይላሉ። ኮማንደር አሰፋ፣ በግምገማ ወቅት፣ “ዛሬ ላይ ማን ለማን እንደሚሰራ አይታወቅም” በማለት ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ መዘገቡ ይታወቃል። የክልሉን ፖሊሶች ለማረጋገት በሚል የተሰጠው መግለጫ፣ የክልሉ ፖሊሶች ኮሚሽኑ ሙሉ በሙሉ በህወሃት ኮማንድ ፖስት ወድቋል በሚል ለሚያቀርቡት ትችት ተጨማሪ ማረጋገጫ የሚሰጥና እያሳዩት ያለውን ተቃውሞ ይበልጥ አጠናክረው እንዲገፉበት የሚያደርግ ነው ሲሉ የፖሊስ ምንጮቻችን ይናገራሉ። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽን የምዕራብ ጎጃም የወንጀል ምርምራ ሃላፊው ኮማንደር በላይ ካሴም ስራ
የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች በየቀኑ ከ50 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ይቀበላሉ። ወንዶ ድርጅት ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚሄደውን ጫት ቀረጥ እንዲሰበስብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፣ በየኬላዎቹ ጫት ጭነው ከሚመጡ መኪኖች በኪሎ ግራም ለቀረጥ ለኮቴና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል 11 ብር ይቀበላል። አንድ መኪና በአማካኝ እስከ 5 ሺ ኪሎ ግራም ጫት የሚጭን በመሆኑ፣ በመኪና እስከ 55 ሺ ብር ከፍያ ይፈጸማል። ወንዶ ድርጅት ለመንግስት የሚያስገባው በቀን 60 ሺ ብር ሲሆን ይህም ከአንድ መኪና ጫት ከሚገኘው ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ነው። በእየቀኑ እስከ 20 መኪና ጫት የሚቀረጽ ሲሆን፣ በቀን እስከ 1 ሚሊዮን 100 ሺ ብር ይሰበሰባል። አዲተሮች በ2005 ዓም ባደረጉት ምርመራ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አለመሆ
Monday, June 26, 2017
የመውጫ ቀነገደቡ ቢያበቃም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ከሳውዲ አለመውጣታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)
በርካታ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እሁድ ረፋድ ላይ በተካሄደው ስነ- ስርአት የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አመራሮች ታዋቂ ሰዎች መታደማቸውም ተመልክቷል።
የታዋቂው የህክምና ባለሙያ የመኢህድ መስራችና ፕሬዝዳንት የነበሩት የፕሮ/ር አስራት ወልደየስ መካነ- መቃብርና ሃውልት ላለፉት 18 አመታት ከነበረበት ባለወልድ ቤተክርስቲያን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንዲነሳ መወሰኑ ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል።
የመውጫ ቀነገደቡ ቢያበቃም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ከሳውዲ አለመውጣታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)
የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጪ ሐገር ዜጎች ሀገር ለቀው አንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ቢጠናቀቅም ከመቶ ሺዎች በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አንዳልወጡ ህወሐት መራሹ መንግስት አመነ ። የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት ወደ አገር ቤት የተመለሱት ከ 42 በመቶ በታች ነው።
የሳውዲ ኣረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን 2009 አ/ም ጀምሮ በነበሩበት ተከታታይ ሶስት ወራት ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው የማንኛውም ሀገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው አንዲወጡ የሰጠው ቀነ ገደብ ያበቃው ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2009 ቢሆንም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ኣነስተኛ መሆናቸውን የመንግስት ቃል ኣቀባይ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ገልጸዋል።
የታዋቂው ገጣሚ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር አራተኛው የስነ-ግጥም መጽሃፉ ተመረቀ
ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)
“ሚስጥሯን-ያልገለጠልን” በሚል ርእስ በ175 ገጽ እና 61 የግጥም መድብሎችን የያዘው የስነ-ግጥም መጽሃፍ ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2017 በቨርጂኒያ አርሊንግተን የተመረቀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የደራሲው ወዳጆችና አድናቂዎች እንዲሁም በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።
በምረቃው ዝግጅት ላይ “ትላንትን ማስታወስ፣ ነገን ማሰብ ካልተቻለ የዛሬ ፈተና አይተላለፍም” በማለት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ያደረገው የመጽሃፉ ደራሲ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር ለሀገረ- ኢትዮጵያ ክብር “ሀገሬ” ላሏት የሀገር ፍቅር ሲሉ የአካል ፈተናና የህይወት መስዋእትነት ለከፈሉ ዛሬም እንደ ትላንቱ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት፣ ሰንደቅ አላማ፣ ለዜጎች መብትና ነጻነት ለሚሟገቱ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ይሄ መጽሃፍ የጽናታቸው መሰረት እንዲሆን ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና በካናዳ ቶሮንቶ በተዘጋጀ ስነ-ስርአት የተወሰኑ የምክር ቤት አባላት ለድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሽልማት ሰጥተዋል። በእለቱ በካናዳ የኢትዮጵያውያን ማህበር የቤተሰብ ምሽት በማዘጋጀት ለድምጻዊው የክብር ሽልማት መስጠታቸው ታውቋል።
በሶማሌ ክልል ህጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ይፋ አደረገ
ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን በያዝነው ሰኔ ወር ብቻ 67 ሕጻናት በረሃብ መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰኞ ይፋ አደረገ። 51 ህጻናት የሞቱት ወሩ በገባ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሆነም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ሶማሌ ዞን ያለው የረሃብ ሁኔታ አስደንጋጭ ሆኖ መቀጠሉን ያስታወቀው የፈረንሳይው ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን 27 የመመገቢያ እንዲሁም አራት የህክምና እና የመመገቢያ ጣቢያ በማቋቋም ከመንግስት ጋር በትብብር መስራቱን ቢቀጥልም ችግሩን መቆጣጠር አለመቻሉን አስታውቋል።
በዚህ በዶሎ ዞን ገላዲ እና ዲኖትን ጨምሮ በ50 ወረዳዎች ከጥር ወር ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 አመታት በታች ለሆኑ 6ሺህ 136 በረሃብ ለተጎዱና ለሞት የተጋለጡ ህጻናት ህክምና እና የተመጣጠነ ምግብ ማቅረቡን ገልጾ ይህ አሃዝ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ10 እጥፍ መጨመሩን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። የአምናው የተመሳሳይ ወቅት አሃዝ 491 ብቻ እንደነበርም አስታውቋል።
አድርባይነት በታደሰ ብሩ
1. ትርጓሜ
አድርባይነት ለገዛ ራስ ጥቅም እንጂ ለህሊና ዳኝነት፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት ላላቸው የሥነ ምግባር መርሆዎች፣ ለሌሎች ሰዎች፣ ቡድኖች፣ ትውልድና ሀገር ግድየለሽ መሆን ነው። የግል ዝናውን፣ የግል ሀብቱን ወይም የግል ምቾቱን ለመጨመር ሲል ማድረግ የነበረበትን ማድረግ እየተቻለ ሳያደርግ የቀረ፤ ወይም ማድረግ ያልነበረበትን ያደረገ ሰው፣ ቡድን ወይም ድርጅት አድርባይ ይሰኛል።
አድርባይ የሆነ ሰው ወይ ድርጅት የሥነ ምግባር ልጓም የለውም፤ የሚናገረውን ሆኖ አይገኝም፤ ዋዣቂና ወላዋይ ነው፤ ለምንም ነገር መታመን አይችልም፤ ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ ማዶ ነው፤ ከፍ ያለ ዋጋ ላቀረበ ሁሉ ሊገዛ የሚችል ሸቀጥ ነው። አድርባይ ሰው ወይም ድርጅት ነገሮችን ሁሉ የሚመዝነው ከራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ ነው። አድርባይነት በመልካም ማኅበረሰብ የተጠላ፣ የተናቀ፣ የማይፈለግ ብቻ ሳይሆን በህገወጥነት የሚያስቀጣም ባህርይ ነው።
2. አድርባይነትን የት እንፈልገው?
Thursday, June 22, 2017
የአቶ አለምነው መኮንን የግል አጃቢ በሆቴል ውስጥ መገደላቸው ታወቀ
የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣንና የብአዴን ፅ/ቤት ሃላፊ የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ ሆቴል ውስጥ መገደላቸው ታወቀ። በሌላ ሰው ሥም በተያዘ ሆቴል ውስጥ አጃቢው መገደላቸውና ሆቴሉን የያዘው ሰው አለመታወቁ አነጋጋሪ ሆኗል። ግድያውንም ተከትሎ በብአዴን አመራር በተለይም በአቶ ዓለምነው መኮንን ዘንድ ሥጋት መፈጠሩ ተመልክቷል።
የኣቶ ዓለምነው መኮንን አጃቢ አቶ አንዋር መሐመድ የተገደለው ሰኞ ሰኔ 12/ 2009 በባህርዳር ቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ሲሆን ይህ ሆቴል በብአዴን ባለስልጣናት የሚዘወተር መሆኑም ታውቋል። ይህ ሆቴል ከዚህ ቀደም የቦንብ ጥቃት እንደተፈፀመበትም ማስታወስ ተችሏል።
ግድያው በዋናነት የተነጣጠርው በአቶ ዓለምንው መኮንን ላይ እንደነበር የሚገልፁት ምንጮች አጃቢያቸው ተባባሪ ሆኖ ባለመገኘቱ ሣይገደል እንዳልቀረ አመልክተዋል። ሟች ከአቶ ዓለምነህ ጋር የአንድ አካባቢ ሰዎች እንደሆኑም መረዳት ተችሏል። ከግድያው ጋር ተያይዞ የአማራ ክልል ወንጀል መከላከል ሃላፊ ኮማንደር አሠፋ ስንታየሁ ሥራቸውን መልቀቃቸውም ታውቋል።
የቀን ገቢ ግምት በማስላት በነጋዴዎች ላይ የሚጣለው ግብር ከፍተኛ ተቃውሞ አስከተለ
የቀን ገቢ ግምትን በማስላት በነጋዴዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተቃውሞና ውጥረት ማስከተሉን የኢሣት ምንጮች ከአዲስ አበባ ገለፁ። በተለይ በዋናው የገበያ ማዕከል መርካቶ ነጋዴዎች እየተዋከቡ ሲሆን እርምጃው ነባር ነጋዴዎችን እየገፋ እዚህ መድረሱንም መረዳት ተችሏል።
ድንገት በገበያ ሥፍራዎች የሚሰማሩትና በኢሕአዴግ የተለያዩ መዋቅር የተሰለፉት የቀን ግምት ገማቾች ግዢ ፈፅመው የሚሄዱ ሸማቾችን ጭምር በማዋከብ ላይ መሆናቸውን የሚገልፁት የኢሣት ምንጮች ፌደራል ፖሊስም በማዋከቡ ሂደት ተሣታፊ መሆኑን ገልፀዋል።
Monday, June 19, 2017
Ethiopia: Global warming threatens coffee growing regions
ESAT News (June 19, 2017)
Rising temperatures is threatening to make half of the coffee growing regions in Ethiopia unsuitable for coffee with some areas already destroyed by the global warming phenomenon.
የአርበኞች ግንቦት7 ልዩ ኮማንዶ በእብናት ከተማ ወታደራዊ ጊዚያዊ ጣቢያ ላይ ሰፍሮ በሚገኙ ወታደሮች ላይ በወሰዱት ጥቃት የጦሩ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር አወቀን ጨምሮ በርካታ ወታደሮችን መግደላቸውን አስታውቀዋል
የአርበኞች ግንቦት7 ልዩ ኮማንዶ በእብናት ከተማ ወታደራዊ ጊዚያዊ ጣቢያ ላይ ሰፍሮ በሚገኙ ወታደሮች ላይ በወሰዱት ጥቃት የጦሩ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር አወቀን ጨምሮ በርካታ ወታደሮችን መግደላቸውን አስታውቀዋል። ኮማንደሩ በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ወታደራዊ አመራሮች፣ የክልል ባለስልጣናት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አርማጭሆ ላይ መቀበሩን የገለጸው ድርጅቱ፣ አዛዡ አስቀድሞ የአርበኞች ግንቦት7 አባላትን እንደሚደመስሳቸው ለአለቆቹ ቃል ገብቶ ነበር ብሎአል። ንቅናቄው በራሱ በኩል ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና ታጋዮቹ በሰላም ወደ መጡበት መመለሱን ገልጿል። ጥቃቱ በሌሊት በመካሄዱ የሟቾቹን ቁጥር በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ድርጅቱ ገልጾ፣ በአሁኑ ሰዓት በደቡብ ጎንደር ዞን በደብረታቦር፣አዲስ ዘመን፣እብናት፣ወረታ፣ ልማትበርና ወደ ባህርዳር መግቢያ ቦታዎች ድረስ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሰራዊት ተሰማርቶ በመንገደኞች እና በተሽከርካሪዎች ተጭነው በሚሄዱ መንገደኞች ላይ ድንገተኛ ፍተሻዎችን በማድረግ ላይ መሆኑም አክሎ ገልጿል። ገዢው ፓርቲ አርበኞች ግንቦት 7 አገኘሁት ባለው ድል ዙሪያ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጠም። አርበኞች ግንቦት7 በተደጋጋሚ ለሚያወጣቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች ገዢው ፓርቲ መልስ ሰጥቶ አያውቅም። የአካባቢውን ሰዎች ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።
Friday, June 16, 2017
የሽብር ወንጀል ፈጽማችኋል በሚል በተከሰሱት ኢትዮጵያውያን ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈ
ሰኔ 9 ፥ 2009
የሽብር ወንጀል ፈጽማችኋል በሚል በተለያዩ የክስ መዝገቦች በወህኒ ቤት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የጥፋተኘነት ውሳኔ ተሰጠ። ከ13ቱ ተከሳሾች 7ቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተለለፍባቸው፣ 6ቱ በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሰሩ ዳንዔል ሺበሺና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እንዲከላከሉ ፍ/ቤት ወሰነ።
ከግንቦት 7 ጋር በተየያዘ ክስ የተመሰረተባቸውና በአሸባሪነት ተወንጅለው ለአመታት ወህኒ ከቆዩት 13 ተከሳሾች 7ቱን ማለትም በላይነህ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞ፣ ቢሆነኝ አለነ፣ ፈረጃ ሙሉ፣ አትርሳው አስቻለው፣ አንጋው ተገኝና፣ አባይ ዘውዱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠትና የእስራት ዘመኑን ለመወሰን ለሰኔ 16 ፥ 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከመቼው በላይ ዝቅተኛ ነው ተባለ
ሰኔ 9 ፥ 2009
የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከመቼው ጊዜ እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ዘርፉ እያበረከተ ያለው አስተዋጽዖም ባለፉት 40 በላይ አመታት እጅግ ዝቀተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።
ጋዜጣው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ለአገሪቷ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት እጅግ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የአለም ባንክን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል። በመሆኑም፣ መስኩ እኤአ በ2015 ከአገሪቱ አጠቃላይ ገቢ 4.5 በመቶ የሆነውን ያስመዘገበ ሲሆን፣ እኤአ በ 1997 ከነበረው ከ7.8 ፐርሰንት አሽቆልቁሎ ታይቷል።
በምስራቅ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የንግድ ማዕከል ተገኘ
ሰኔ 9 ፥ 2009
በምስራቅ ኢትዮጵያ ሃርላ በሚባል አካባቢ በመሰማራት ቁፋሮ ሲያደርጉ የነበሩ የስነ ምድር ተመራማሪዎች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ10ኛው ክፍለ ዘመን የንግድ ማዕከል የነበረ አንድ ከተማ ማግኘታቸውን ገለጹ። ከግብጽ፣ ከህንድና፣ ከቻይና ወደ ከተማው የገቡ የተለያዩ ቁሳቁሶችም መገኘታቸው ተገልጿል። ከማዳጋስካር፣ ከማልዲቭስ እና ከየመን ጭምር የመጡ የተለያዩ ጌጣጌቶች በአካባቢው ተቀብረው መገኘታቸው ቢቢሲ በድረገጹ አስነብቧል።

Wednesday, June 14, 2017
Ethiopians among missing in London’s Grenfell Tower blaze
ESAT News (June 14, 2017)
At least 12 people have been killed in the west London’s Grenfell Tower as fire turned the 24-storey apartment building into an inferno in the early hours of Wednesday morning.
Information gathered by ESAT’S London Bureau shows at least 40 Ethiopians and Eritreans live in the tower and some are feared to be among the missing .
Ethiopia: Widespread contraband trade crippling economy
ESAT News (June 14, 2017)
High level contraband trade by government officials has become a threat to the country’s economy as foreign exchange trade is in downward spiral, according to Ethiopia’s Ministry of Trade.
በለንደን ከተማ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ አደጋ 12 ሰዎች ሞተው 68 ሌሎች ቆሰሉ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)
በእንግሊዝ አገር በምዕራብ ለንደን ከተማ በአንድ ህንጻ ላይ በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ 12 ሰዎች መሞታቸውንና 68 ሌሎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገለጸ። በአደጋው የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።
በለንደን የ24 ፎቅ ርዝመት ባለው ግሬንፈል ታወር መኖሪያ ህንጻ ላይ የእሳት ቃጠሎ የተከሰተው ነዋሪዎቹ ተኝተው በነበረበት ረቡዕ እኩለ ሌሊት ላይ መሆኑን የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በህንጻው ላይ ቃጠሎው በተከሰተበት ሰዓት ብዛት ያላቸው ነዋሪዎች በመስኮት በመሆን እርዳታ እየጠየቁ እንደነበር የአልጀዚራ የዜና ወኪል ከስፍራው ዘግቧል።

የ2010 አጠቃላይ በጀት ውስጥ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መ/ቤት የ2010 ጠቅላላ የበጀት ወጪ 321 ቢሊዮን ብር አቀረበ። በጀቱ 54 ቢሊዮን ብር ጉድለት የታየበት ሲሆን፣ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ አገር እና በአገር ውስጥ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገልጿል።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የ2010 የበጀት ዕቅዱን ለፓርላማ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከተያዘው አመት ጋር ያሉትን ልዩነቶች አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ከቀጣዩ አመት በጀት ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ በያዝነው የ2009 አመት 12 ቢሊዮን ብር የነበረው በ2010 ወደ 7 ቢሊዮን ብር እንዲቀንስ የተደረገ ሲሆን፣ በተቃራነው የመከላከያ በጀት ከ11 ቢሊዮን ወደ 12 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉ ተገልጿል።
የልማት በጀት ተቀንሶ ወደ መከላከያ መጨመሩ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሃገሪቷ የገባችበት የጸጥታ ስጋት እየጨመረ መሄዱን እንደሚያመለክት የዘርፉ ሙያተኞች ይገልጻሉ።

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ (ሜይቴክ) ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)
በህወሃት የጦር መኮንንኖች የሚመራው የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ (ሜይቴክ) ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት።
በህወሃት የጦር ጄኔራሎች የበላይ አዛዥኘት ክፍያውን የወሰደው ሜቴክ ከ 3 አመት በፊት ግንባታውን አጠናቅቆ ለማስረከብ ውል ስለተፈረመበት ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሆኑ ከዋና ኤዲተሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ሜቴክ ማዳበሪያ ፋብሪካውን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስረከብ የነበረበት በ 2006 አ’ም ቢሆንም አስከ አሁን ድረስ ሰርቶ ያጠናቀቀው ከግማሽ በታች (42 በመቶ ) ብቻ መሆኑን የኦዲት ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል’።
የዋናው ኤዲተር ሪፖርት አንዳመላከተው ሜቴክ ምንም አንኳን የአፈጻጻም ደረጃው ክፍያ ሊያስገኝለት የሚችለው 3.7 ቢሊዮን ብር ያህል ቢሆንም የተከፈለው 5.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን እና ላልተከናወነ ስራ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መከፈሉን አረጋግጧል። ዋና ኦዲተሩ አያይዞ አንደገለጸው ሜቴክ በገባው ውል መሰረት ከ 3 አመት በፊት አጠናቅቆ ማስረከብ ያለበትን የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በማንጓተቱ ምክንያት ኮርፖሬሽኑ ከባንክ ለተበደረው ብድር ወለድ ብቻ ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን አስታውቀዋል።
በቀጣይም ሜቴክ በገባው ውል መሰረት ፕሮጀክቱ በተራዘመ ቁጥር የማዳበሪያ ፋብሪካው የሚያመነጨው ገቢ ስለማይኖር ለባንክ የሚከፈለው ወለድ በከፍተኛ መጠን ሊያድግ እንደሚችልና የፋብሪካው ዘላቂነት አደጋ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል አመላክተዋል።
በህወሐት የጦር መኮንንኖች የበላይ አዛዥነት የሚንቀሳቀሰው ሜቴክ በርካታ ፕሮጀክቶች ያለአቅሙ በመውሰድ በህዝብ ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አያደረሰ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚገልጽ መሆኑ የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ የኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቷል ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱንና የሃገሪቱም የውጭ ንግድ እያሽቆለቆለ መገኘቱን የንግድ ሚኒስትሩ ገለጹ። የመንግስት ባለስልጣናት ከፍተኛ የስልጣን መዋቅር እስከታችኛው ዕርከን በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው ተዋናይ መሆናቸውም ከንግድ ሚኒስትሩ መግለጫ መረዳት ተችሏል።
በሳምንቱ አጋማሽ የመስሪያ ቤታቸው የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ማክሰኞ ዕለት ለፓርላማ ያቀርቡት አዲሱ የንግድ ሚኒስትር ዶ/ር በቀለ ቡላዶ ችግሩ ስር የሰደደ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እንደማይፈታ ማመልከታቸውን አዲስ አበባ ከሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ መረዳት ተችሏል።

የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ፈረሰ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)
የታዋቂው የህክምና ባለሙያ፣ የመአህድ መስራችና ፕሬዚደንት የነበሩት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ፈረሰ።
አፅማቸው ወዴት እንደሚወሰድ የታወቀ ነገር የለም። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ አቡነ ሳዊሮስ ስለጉዳዩ እንደማያውቁ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከሳምንታት በፊት የመካነ መቃብሩን አጥር በማፍረስ የተጀመረው እንቅስቃሴ ማክሰኞ ሰኔ 6 ፥ 2009 ሙሉ በሙሉ ሃውልቱን በማፍረስ ተጠናቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ፣ አጽማቸው ከመካነ መቃብር ያልወጣ ሲሆን፣ በቅርፅ የተሰራው ሃውልትም የተወሰደበት አልታወቀም።

Tuesday, June 13, 2017
የባህርዳርና የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለብአዴኑ ጥረት ድርጅት ተላለፉ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009)
የባህርዳርና የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለብአዴኑ ጥረት ድርጅት መተላለፋቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።
የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በጣሊያን ወረራ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት በደም ካሳነት ለህዝብ ሲባል የተሰራ እንደነበር ይገለጻል።
በቅርቡ 5 መቶ ሚሊዮን ወጪ ተደርጎ ማስፋፊያ የተሰራለትን የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የኮምቦልቻውን ጨምሮ ጥረት መጠኑ ባልታወቀ ርካሽ ዋጋ እንደተረከበው ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል ከዳሸን ቢራ ፋብሪካ ውጪ የረባ ነገር አልሰራም የሚባለው ጥረት ሁለቱን ነባር ፋብሪካዎች ገዝቶ ከኤፈርት ጋር በዕኩል ደረጃ ለመታየት የሚያደርገው ጥረት ነው በማለት ህብረተሰቡ እየተቃወመ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009)
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ። ሚኒስቴሩ ማክሰኞ ባወጣው ማሳሰቢያ እንዳለው አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀበት ከመስከረም 2009 በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጿል።
ሚኒስትሩ በድጋሚ በድረገጹ ያወጣው የጉዞ ጥንቃቄ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጣይ ከተደረገበት እኤአ ከ ማርች 2017 ጀምሮ በአማራ ክልል በባህርዳርና በጎንደር አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አብራርቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማወኩና የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጡ፣ የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አሜሪካውያን ጋር ግንኙነት እንዳያደርጉ ማስተጓጎሉን ገልጾ፣ የኢትዮጵያ መንግስት አገልግሎት ሲያቋርጥም ለአሜሪካ እንደማያሳውቅም በድረገጹ አስፍሯል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ዜጎች ሲታሰሩ ለአሜሪካ መንግስት እንደማያሳውቅ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብራርቷል።
“ዶክመንተሪው” እና አንሙት አብርሃ (ታደሰ ብሩ)
የፀረ-ሽብርና የፌደራል ፓሊስ ጥምር ግብረኃይል ከEBC (የድሮዉ ኢቲቪ) እና ENN ጋር በመተባበር “ታላቅ” የተባለ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ) እያዘጋጀ ነው። [መቸም፤ EBCን እና ENNን በእንግሊዝኛ መጥራት ግዴታችን ሆኗል]
የዚህ ዶክመንታሪ ስክሪፕት ፀሐፊ አቶ አንሙት አብርሃም ነው። አቶ አንሙት የፃፈው ስክሪፕት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኩራል:- ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ እና በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ አሉባልታዎችን መንዛት።
ትኩረት አንድ
ትኩረት አንድ የሚያጠነጥነው ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ ላይ ነው። ለዚህ እንዲረዳ ኦብነግ ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተነሳ ድርጅት መሆኑን ያሳምናሉ የተባሉ የቪዲዮ ማስረጃዎች ተሰባስበዋል። “ኢህአዴግ ከኦብነግ ጋር እየተነጋገረ ነው” “የኦብነግ መሪዎች አመጽን አውግዘው ህገመንግስቱን ተቀብለው በህጋዊ መንገድ ለመታገል ምህረት ጠይቀው ገቡ” “ኦብነግ የሚባል ድርጅት የለም” በሚል እና መሰል ርዕሶች ቀደም ሲል የተሠሩ ዜናዎችና ዶክመንተሪዎች በስህተት ተደባልቀው እንዳይገቡ ጥንቃቄ ተደርጓል። የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች በዶክመንተሪው ይሳተፉሉ፤ የሶማሌ ክልል ሕዝብ በፌደራሊዝም ምን ያህል እንደተጠቀመ ይናገራሉ፤ ይህን ወደ ገነት በር ያቀረባቸውን ፌደራሊዝም ሊነጥቅ የመጣን ብርሃኑንና ድርጅቱን አምርረው እንደሚታገሉት ይናገራሉ።
ህወሓት ፕ/ር ብርሃኑን አገር በማስገንጠል ፈርጆ ሲከስ በአድማጮች ጭንቅላት ውስጥ የትኛው ትዝታ ብቅ ሊል እንደሚችል መገመት ለብዙዎቻችን ከባድ ባይሆንም ለስፕሪፕት ፀሐፊውና ለአለቆቹ ግን የሮኬት ሳይንስ ያህል ከባድ ነው። “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ይሏል ይህ ነው።
ትኩረት ሁለት
Monday, June 12, 2017
ጊዜው የሕዝባዊ አሻጥር ነው !!!
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ “ሴፍ ሀውስ” እያሉ የሚያቆላምጧቸው ከ50 በላይ ድብቅ የማሰቃያ ቦታዎች አሉ። ከፊሎቹ የምድር ውስጥ ዋሻዎች አሏቸው። ብዙዎቹ መሀል ከተማ ውስጥ ሲገኙ ጥቂቶቹ በከተማው ዳርቻዎች ይገኛሉ። በማዕከላዊና በሌሎች እስር ቤቶች ውስጥም የማሰቃያ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም ወገኖቻችን ከፍተኛ ፍዳ እንዲደርስባቸው የሚደረገው በእነዚህ ከእይታ በተሰወሩ የማሰቃያ ቦታዎች ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ በናዚ ፋሽስቶች ይፈፀሙ ከነበሩ ሰቆቃዎችን የባሱ አስነዋሪና ኢሰብዓዊ ግፎች በእነዚህ የማሰቃያ ቦታዎች ውስጥ ይፈፀማሉ።
ልብስን አስወልቆ ራቁት መግረፍ፤ እግርን አስሮ መዘቅዘቅ፤ በተገመደ የፕላስቲክ ቀበቶና የኤሌክትሪክ ገመድ መግረፍ፤ ጭንቅላትን በቀዘቀዘ ውሃ ውስጥ መንከር፤ በተራቆተ ገላ ላይ የተለኮሰ ሲጋራ መተርኮስ፤ በፊት ላይ መትፋት፤ በኤሌክትሪክ ንዝረት መጥበስ፤ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ መክተት፤ ጥፍርና ፀጉርን መንቀል፤ በሽንት ቤት ዝቃጭና ውሃ በተሞላ ክፍል ውስጥ ማስገባት፤ እንቅልፍ መከልከል፤ ምግብ፣ መጠጥና ህክምና መከልከል፤ የወንዶች ሽንት መሽኚያ አካልን በሲባጎ አጥብቆ በማሰር ማሰቃየት፤ በወንድ ተመርማሪዎችን የዘር ፍሬዎችን በፒንሳ መጨፍለቅ፤ በወንድ ተመርማሪዎች የዘር ፍሬ ላይ ባዕድ እቃዎችን ማንጠልጠል፤ በሴት ተመርማሪዎች ማህፀን ዉስጥ ባዕድ ነገር ከቶ ማሰቃየት፤ የሴት ተመርማሪዎችን ጡትን በብረት መምታት፤ ሴት ተመርማሪዎችን በቡድን አስገድዶ መድፈር እና ከእነዚህ የባሱ ክፋቶች በእነዚህ የማሰቃያ ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ ይደርሳል።
የህወሓት ፋሽስቶች የማሰቃያ ቦታዎቻቸው ከሕዝብ ዓይንና ጆሮ የተሰወሩ ይመስላቸዋል። እነሱ “ሴፍ ሀውስ” ብለው ስለጠሯቸው በእርግጥ “ሴፍ” የሆኑላቸው ይመስላቸዋል። ይህ እውነት አለመሆኑ ግን በተጨባጭ እንዲያዩ ተደርጓል።
Ethiopia: Group claims responsibility for arson at ammunition depot
ESAT News (June 12, 2017)
An armed group has claimed responsibility for an arson attack at an ammunition depot in Ethiopia’s capital Addis Ababa on Saturday.
Patriotic Ginbot 7, an armed group fighting the Ethiopian regime from its base in Eritrea, said Saturday’s attack is part of the resistance movement carried out by its cells everywhere in Ethiopia.
The fire at the Federal Police ammunition depot in the capital went for hours and caused extensive damage to the depot before the city’s fire department was able to put it under control.
Ethiopia: Fuel truck ambushed in northern Gondar
ESAT News (June 12, 2017)
A fuel truck traveling from Sudan to Metema, northern Ethiopia came under attack on Monday 2 kms outside Addis Zemen, according to sources.
The driver of the fuel truck was taken to Bahir Dar Hospital, the sources added.
Ethiopia: Regime denies emergency food aid will run out within weeks
ESAT News (June 12, 2017)
The Ethiopian regime has denied suggestions by UN officials that it will run out of emergency food aid for millions of people by the end of this month, the BBC reported quoting officials.
The UN’s World Food Programme said 7.8 million people affected by drought would be left without food assistance.
But Ethiopian officials put the number of those affected at 1.7 million and said they would receive new help either from donors or the government.
Ethiopia has been struggling following successive failed rains.
በቆሼ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009)
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ደርሶ ከነበረው የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ጋር በተገናኘ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ከ20 በላይ ሰዎች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።
የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ 23 የሚሆኑት ሰዎች በስፍራው ይኖሩ ስለመሆናቸው አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው እንዲመጡ መታዘዛቸውን ገልጿል።
ከአደጋው የተረፉት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች ጉዳቱ ከደረሰና የተለያዩ አካላት ገንዘብ ከለገሱ ሶስት ወራት ቢያልፍም፣ የተገባላቸው ድጋፍ ሊሰጣቸው አለመቻሉን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
በቅርቡ ተጎጂዎቹ የተገባልን የድጋፍ ቃል ተግባራዊ አልተደረገም ሲሉ ቅሬታን ማቅረባቸው ይታወሳል።
የከተማዋ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች መረጃ 94.5 ሚሊዮን ብር ከተለያዩ አካላት መሰብሰቡን እሁድ አስታውቋል። ህጋዊ ይዞታ ለነበራቸው 13 ሰዎች መሬትን ጨምሮ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ሲሉ የቢሮው ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ተመድ የእርዳታ ምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009)
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የተጋለጡ ወደ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች።
አለም አቀፍ ተቋማትና የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም ተረጂዎች ከሰኔ ወር መገባደጃ ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ እንደማይኖር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሲያሳስቡ ቆይተዋል።
ይሁንና በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽን የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት በችግሩ ምክንያት 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ብቻ ጉዳት እንደሚደርስባቸው መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የአደጋ መከላከል አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ምትኩ ካሳ ለተረጂዎች የሚሆን የምግብ አቅርቦት ለሁሉም ተረጂዎች ያልቃል መባሉ ትክክለኛ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
ይሁንና በተወሰኑ አካባቢዎች ለተረጂዎች የሚቀርብ የምግብ አቅርቦት እንደማይኖርና 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ለችግር እንደሚጋለጡ አቶ ምትኩ ለዜና አውታሩ ገልጸዋል። የተፈጠረውን የምግብ አቅርቦት ክፍተት ለመሙላት የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍን እንዲያደርግለት ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የቂሊንጦ እስር ቤት አቃጥለዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች የክስ ቻርጁን ወደ ዳኞችና አቃቢያነ ህጎች ወረወሩ
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009)
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በማቃጠል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የታደላቸውን ክስ ቻርጅ ወደ ጃኞቹና አቃቢያነ ህጎቹ በመወርወር እንዲሁም በድምፅ ተቃውሟቸውን ማቅረባቸው ተገለጸ። ፍ/ቤቱም ሁኔታውን ተከትሎ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል።
የፍርድ ውሳኔው የተላለፈባቸው ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ ተደራራቢ ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩ 121 እስረኞች መካከል መሆናቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
ሰሞኑን ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት 21ዱ ተከሻሾች የተመሰረተባቸው ክስ ሊነበብላቸው ሲል “ክሱ አይነበብም” በማለት በችሎቱ ከፍተኛ ተቃውሞን አቅርበዋል።
የተወሰኑ ተከሳሾች የተሰጣቸውን ክስ ግልባጭ ወደ አቃቤ ህግና ወደ ዳኞች የወረወሩ ሲሆን፣ “ዳኞችና አቃቤ ህጎች ጅቦች፣ ውሾች፣ ቆሻሾች፣ ሆዳሞች ናችሁ” የሚሉ ቃላትን መሰንዘራቸው ተመልክቷል።

ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃጠለ
ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና
በኮልፈ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ካራቆሬ በሚባለው አካባቢ ዘይት ቤት በመባል በሚጠራው ግቢ የሚገኘው ‹‹ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ›› ከጥቅምት 05/09 ጀምሮ እስከ ሰኔ 3 ቀን 20099 ዓ.ም ድረስ ባሉት 9 ወራት ለሦስተኛ ጊዜ መቃጠሉን ዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት ተኩል ባልታወቀ ምክንያት የተነሳው እሳት የፋብሪካውን የምርት መጋዝን ሙሉ በሙሉ አጋይቶ ከፋብሪካው ድንበርተኛ የሆነ ወፍጮ ቤት አውድሞ በራሱ ጊዜ እየጠፋ ባለበት ሰአት ፣ የእሳት አደጋ መኪና 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ ደርሷል፡፡ ባለፈው በተነሳው ቃጠሎ ከምርት መጋዝኑ በተጨማሪ የፋብሪካው ጄኔረተርና በድንበር የሚገኝ ወፍጮ ቤት ከመውደማቸው ሌላ፣ እሳቱ እንደከዚህ በፊቱ የጥቅምት 5 ቃጠሎ

Thursday, June 8, 2017
Ethiopia: Ambo students say protest against regime will continue
ESAT News (June 8, 2017)
Students and residents of Ambo who spoke to News 24 say they expect protest against the regime will continue.
“It’s a fire under ashes,” a judge in a district near Ambo told News 24. He believes the lull in protests against the government is just temporary and could be reignited like a fire covered with ashes for later use.
Ambo, west of the capital Addis Ababa, was the center of the anti-government protests that began in 2015 which spread to the Oromo and Amhara regions forcing the regime to declare a state of emergency last October.
Forty Ethiopian rounded up in Kenya for illegal entry
ESAT News (June 8, 2017)
Kenyan media reported that forty Ethiopians were rounded up in a house in Kayole on Thursday for being in the country illegally.
The Star reported that the Ethiopians aged between 10 and 25 , could not speak English or Kiswahili, but told police through a translator that they were headed for South Africa.
በኬንያ ህወገጥ የተባሉ 40 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009)
የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 40 ኢትዮጵያውያን ሃሙስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።
የኒጅሩ አስተዳደር ኮማንደር ፓርቲክ ምዋምባ ኢትዮጵያውያኑ በአስተዳደሩ ስር በምትገኘው የቃዬሌ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ በነዋሪዎች በተደረገ ጥቆማ ሊያዙ መቻላቸውን እንደገለጹ ዘስታር የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧልል።
በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከ10 እስከ 25 አመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ በአንድ ወኪል አማካኝነት ሰኞ ከኢትዮጵያ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ የማቅናት ዕቅድ እንደነበራቸው በአስተርጓሚ በኩል ቃል እንደሰጡ የንጅሩ አስተዳደር ሃላፊ አስረድተዋል።
ብሪታኒያ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው አለም አቀፍ ድጋፍ በተፎካካሪ በፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ ቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009)
በብሪታኒያ ሃሙስ የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በተካሄደ ምርጫ ሃገሪቱ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው አለም አቀፍ ድጋፍ በፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ ቀረበ።
የብሪታኒያ መንግስት ለበርካታ ደሃ ሃገራት ሲሰጥ የነበረው ይኸው ድጋፍ የሰብዓዊ መብትን ቅድሚያ አልሰጠም እንዲሁም ድጋፍ ለታለመለት አላማ አልዋለም የሚል ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወሳል።
ይኸው የሃገሪቱ አለም አቀፍ ዕርዳታ ሃሙስ ሲካሄድ በዋለው ምርጫ በኮንሰርቫቲቭ፣ በሌቨርና በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ መዋሉን ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ ፓርቲ የሆነው የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሃገሪቱ ስትሰጥ የቆየችው አለም አቀፍ ድጋፍ በአተገባበሩና በትርጓሜው ዙሪያ ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት አቋምን ይዟል።
የሌቨርና ሌሎች ፓርቲዎች ድጋፍ መቀጠል እንዳለበት ቢስማሙም የሃገሪቱ መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ ዳግም መጤን እና ድህነት ለቅረፍ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ማተኮር እንዳለበት መከራከርያ ሃሳብን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው አመት ከቀረበው በጀት የ54 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳጋጠማት ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009)
ለ2010 አም በጀት ከቀረበው የ321 ቢሊዮን ብር ውስጥ የ54 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሃሙስ ገለጸ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተያዘው ሳምንት በሃምሌ ወር ለሚጀምረው ቀጣዩ በጀት 321 ቢሊዮን ብር በጀት ማቅረቡ ይታወሳል።
በዚሁ በጀት ዙሪያ ለፓርላማ ማብራሪያ ያቀረበቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ለበጀቱ ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ የ54 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት መኖሩን አስታውቀዋል።
የባህርዳር ከነማ ከትግራይ ዎልዋሎ ክለብ ጋር ግጥሚያ እንዲያደርግ በግዳጅ ወደ አዲግራት መወሰዱ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009)
የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ያለ ፍላጎታቸው ከትግራይ ውልዋሎ ክለብ ጋር ግጥሚያ እንዲያደርጉ በግዳጅ ወደ አዲግራት መወሰዳቸው ተገለጸ።
የባህርዳር ከነማ ክለብ ከመቀሌው አቻው ጋር ሲጫወት ከዚህ ቀደም በደጋፊዎች በደል ቢደርስበትም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፍርደግምድል ውሳኔ ተወስኖብኛል በሚል ሲቃወም ቆይቷል።
ይህንኑ ውሳኔ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ አጥብቀው በመቃወም ይግባኝ ቢጠይቁም ውሳኔው በመጽናቱ በአካባቢው ውጥረት እንዲነግስ ምክንያት ሆኖ ነበር።
ግንቦት 29/ 2009 ከመቀሌው ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ከዚህ ቀደም የተቋረጠው ቀሪ ጨዋታ በሁለቱ ቡድኖች መካከል እንዲካሄድ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ ቢሰጥበትም፣ የባህርዳር ከነማ ክለብና ደጋፊዎቹ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
Subscribe to:
Posts (Atom)