(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 24/2011)የኢትዮጵያ ችግር ከስረ መሰረቱ እንዲነቀል የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንዳለበት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ።
በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የአማራ ክልል የልኡካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ካለው የአማራ ተወላጆችና የአማራ ጉዳይ ያገባናል ካሉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ምክክር አድርገዋል።
ከስብሰባው ተዳሚዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ችግር ከስረ መሰረቱ እንዲነቀል የእነዚህ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች በትንሹ መገናኘት ሲጀምሩ፥መቻቻል ሲጀምሩ በሀገሪቱ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ማምጣት እንደሚችሉ አሳይተውናል።
ምናልባትም የኢትዮጵያ ችግር ከስረ መሰረቱ እንዲነቀል የእነዚህ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ ጠንካራ መሆን አለበት የሚል ጽኑ ዕምነት ነው ያለን።
ከ65% በላይ የሚሆኑ ናቸው። ኦሮሞና አማራ በባህል፥በሃይማኖት በቋንቋ በታሪክ በተለያየ መንገድ የተሳሰሩ ናቸው።
እነዚህ ሕዝቦች እሳትና ጭድ ስለተባሉ፤እሳትና ጭድ አለመሆናቸውን፥ሰምና ፈትል መሆናቸው ማሳየት በሚል ነው ከኦዴፓ ጋር የተስማማነው።
ምናልባት በደምብ ቢጠና እንደ ሁለቱ ህዝቦች የተቀላቀለ ህዝብ አለ ብዬ አልገምትም።
ነገር ግን ታሪካችንን በተዛባም ሆነ በእውነት ወይም በመፍጠር ግንኙነታቸውን በጥርጣሬ ላይ የተሞላ እንዲሆን ብዙ የተሰራ ስለነበር ይሄን አፍርሰን፥ሁለቱን ህዝቦች አንድ አድርገን በበነጋታው ሞትም የሚመጣ ከሆነ በጸጋ እንቀበለው የሚል ነበር ስምምነታችን።
ከህዝብ ላይ ተጭኖ ለመኖር የሚፈልገውና አሸንፋለሁ ያለው ቡድን መሸነፉን ሳያውቅ እኛም እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ሳንሆን ዶክተር አብይን ስንመርጥ አሸነፍ።
በለውጡ በዋናነት ነጻ የወጣነው እኛ የኢህአዴግ አባላት ነን ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን እያየን ያለነው የድሉን ውጤት ነው፤ ምን እናግዝ ያላችሁን እስከ ድሉ ፍጻሜ ድረስ አብራችሁን ሁኑ” ለውጡ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ገና አልደረሰምና ብለዋል ዶክተር አምባቸው።
እናም አሁን እያየን ያለነው የድሉን ውጤት ነው ሲሉም ዶክተር አምባቸው ገልጸዋል።
ለውጡ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ገና አልደረሰምና ድሉ ፍጻሜ እስኪያገኝ ድረስም አብራችሁን ሁኑ ሲሉ ለመድረኩ ታዳሚዎች ጥሪ አቅርበዋል።
የአዴፓ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ በበኩላቸው ወደ ኋላ መመልከት ትተን ወደፊት እንጓዝ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከልኡካን ቡድኑ አባላት መካካል በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ መላኩ አለበል ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በአማራ ክልል ኢንቨስት በማድረግ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
No comments:
Post a Comment