Thursday, December 8, 2016

Ethiopia: Dozens desert army, join resistance forces patriotic-g7 File photo of PG7 fighters

ESAT News (December 8, 2016)

Patriotic Ginbot 7, a group fighting the Ethiopian government, said 46 soldiers have deserted the regime army and joined the resistance movement.
The soldiers, who defected after a marathon negotiations and joined Patriotic Ginbot 7, have defected with various weapons including 9 artilleries, 6 snipers and RPGs among others, according to a source on the ground with the fighters.

የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ሰሜን ጎንደር እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ

ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009)
በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና በግንቦት ሰባት ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ።
ተደጋጋሚ የጉዞ ማሳሰቢያን ሲያወጡ የነበሩት የጀርመንና የቤልጅየም መንግስታት በኢትዮጵያ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ መሻሻልን ቢያሳይም በአማራ ክልል ስር በሚገኙ ሶስት ዞኖች የጸጥታ ስጋት መኖሩን ይፋ አድርገዋል።
ለዜጎቻቸው አዲስ የጉዞ ማሳሰቢያን ያሰራጩት ሁለቱ የአውሮፓ ሃገራት በጸገዴ፣ ምዕራብና የታች አርማጭሆ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ዜጎቻቸው ጉዞን ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
የፈረንጆች አዲስ አመት መግቢያን ምክንያት በማድረግ የጀርመንና የቤልጂየም ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ በብዛት የሚጓዙ ሲሆን፣ የሁለቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማሰራጨታቸውን ዘቮይስ (The Voice) የተሰኘ መፅሄት ዘግቧል።
በቅርቡ የግንቦት 7 ሃይሎች እንዲሁም ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች በሰሜን ጎንደር ዞን ስር ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም ሃገር ተብላ ተፈረጀች

ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009)
ኢትዮጵያ በተያዘው 2016 የፈረንጆች አም በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም ሃገር ተብላ ተፈረጀች።
በቴክኖሎጂው አጠቃቀምና ተደራሽነት እንዲሁም ቁጥጥር ዙሪያ አመታዊ ጥናቱን ይፋ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ ተቋም ቻይና፣ ሶሪያና ኢትዮጵያ የከፋ የተባለ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ዋነኛ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
ካለፈው አመት ጀምሮ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እገዳንና ቁጥጥርን ተግባራዊ አድርጋ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ 54 ሃገራት መካከል የቴክኖሎጂው ጠላት ተደርጋ ተፈርጃለች።
በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ መንግስት በመደበኛውና በተጓዳኝ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እገዳን ጥሎ የሚገኝ ሲሆን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱን ምክንያት በማድረግም አገልግሎቱ ታግዶ ይገኛል።

በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ የደረሰበት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ተነገረ

ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009)
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሬትን ለማቅረብ ሊያካሄድ ከነበረው ስራ ጋር በተገናኘ ያጋጠመው በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ አዲስ ውዝግብ መቀስቀሱ ተግለጸ።
የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ለደረሰው ኪሳራ ሃላፊነቱን ማን መውሰድ እንዳለበት ለአንድ አመት ያህል ምክክርን ሲያካሄዱ ቢቆዩም ጉዳዩ ዕልባት አለማግኘቱ ታውቋል።
በጋምቤላ ክልል ብቻ ከ100 የሚበልጡ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት የሚሆን ሰፊ የእርሻ መሬት ቢሰጣቸውም የፌዴድራል ባለስልጣናት የመሬት ርክክቡ ህገወጥ ነው በማለት ባለሃብቶቹ ስራቸውን እንዲያቆሙ መወሰኑ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበኩሉ በዚሁ ክልል ተመሳሳይ ይዞታ ላይ በርካታ ባለሃብቶች በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ብድር በመውሰድ ኪሳራ ማጋጠሙ በቅርቡ ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ የተከሰተው የዋጋ ግሽበት ከ5.6 ወደ 7 በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ አጋጥሟል የተባለን የኢኮኖሚ መዳከም ተከትሎ የሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት በተያዘው ወር ከአምስት ነጥብ ስድስት ወደሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃሙስ አስታወቀ።
የአለም ባንክ ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ማሽቆልቆል በኢትዮጵያ ዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል ሲል ማሳሰቡ ይታወሳል።
ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን ትንበያ ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበትን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ ምክንያት የዋጋ ግሽበቱ ከፍ ሊል መቻሉን በሪፖርቱ አመልክቷል።

ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው።

ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው። እስሩ እርሳቸው በተያዙ ማግስት የጀመረ ሲሆን፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮምያ ወረዳዎች እንዲሁም በአምቦና አጎራባች ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች በአዲሱ ወታደራዊ እዝ አማካኝነት መሰታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። እስካሁን በደረሰን መረጃ ከ50 ያላነሱ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሌላ በኩል በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በዘበኝነት ተቀጥረው ስራ የሚሰሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደገና መታዋቂያ እንዲያወጡና እንዲመዘገቡ እየተደረገ ነው። ሰራተኞቹ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ጋር አዲስ ውል እንዲፈርሙ እየተደረገ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰሩ ሰራተኞች የጦር መሳሪያ እንዳይዙ ፣ በስራ ወቅትም ወታደሮች ካልሆኑት ጋር ተመድበው እንዲሰሩ መመሪያ ተላልፏል።

Thursday, December 1, 2016

ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ታችኛው ዕርከን ድረስ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን አንድ የኤምባሲ ባልደርባ ተናገሩ

ኢሳት (ኅዳር 22 ፥ 2009)
አሁን በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ውስጥ ከሚኒስትር ጀምሮ እስከታችኛው ዕርከን የሚሰሩ በሙሉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አገልጋዮች መሆናቸውን በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደርባ የነበሩ ገለጹ። ከስርዓቱ ጋር በመቆየታቸው መጸጸታቸውንም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ከህዝብ ጎን በመሰለፍ ለለውጥ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።