Saturday, April 4, 2015

Ethiopian Brutality, British Apathy

by GRAHAM PEEBLES

On 23rd June 2014 Andergachew Tsige was illegally detained at Sana’a airport in Yemen whilst travelling from Dubai to Eritrea on his British passport. He was swiftly handed over to the Ethiopian authorities, who had for years posted his name at the top of the regime’s most wanted list. Since then he has been detained incommunicado in a secret location inside Ethiopia. His ‘crime’ is the same as hundreds, perhaps thousands of other’s, publicly criticising the ruling party of Ethiopia, and their brutal form of governance.

Born in Ethiopia in 1955, Andergachew arrived in Britain aged 24, as a political refugee. He is a British citizen, a black working class British citizen with a wife and three children. Despite repeated efforts by his family and the wider Ethiopian community – including demonstrations, petitions and a legal challenge – the British government (which is the third biggest donor to Ethiopia, giving around £376 million a year in aid), have done little or nothing to secure this innocent man’s release, or ensure his safe treatment whilst in detention.

የወያኔ አገልጋዮች ፕ/ መስፍን ላይ ጥቃት አደረሱ!!! 

የት ሂዱ ነው?

ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላላን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞትን ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡

Friday, April 3, 2015

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈፀመበት

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈፀመበት በየመን ሰንዓ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለትናንት አጥቢያ ጥቃት እንደተፈጸመበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት በጦር መሳሪያ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት ኢትዮጵያዊ የለም።

አምባሳደሩም ሆኑ ሌሎች ዲፕሎማቶች በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው ያስታወቁት። ኢምባሲ በየመን ያላቸው አብዛኛዎቹ አገራት ኢምባሲዎቻቸውን ከዘጉ ሳምንታት ተቆጥረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ “ከዜጐቻችን በፊት አንወጣም ብለው ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ላሉ ዲፕሎማቶችእና የአስተዳደር ሰራተኞች ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

በሌላ ዜና ከየመን ተመላሽ የሆኑ የመጀመሪያዎቹ 30 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ደርሰዋል። እስካሁን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተመዝግበዋል። የተመዘገቡትን ዜጎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አገራቸው ለመመለስም መንግስት የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

በየመን የሆቲ አማፂያን እና የአልቃይዳ ክንፍ ሰፊ ግዛት እየተቆጣጠሩ በመምጣት የአገሪቱ መዲና ሰነዓን ይዘዋል። በአገሪቱ መንግስት ደጋፊዎች እና በአማፂያኑ መካከል የሚደረገው ግጭት የቀጠለ ሲሆን፥ በተለይም በባህር ዳርቻዋ ከተማ ኤደን ጦርነቱ ተባብሷል ነው የተባለው። በህጋዊ መንገድ የተቀመጠውን የአገሪቱን መንግስት ወደ መንበሩ ለመመለስም በሳዑዲ አረቢያ መሪነት የአከባቢው አገራት ተጣምረው የዓየር ጥቃት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።




ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።

Thursday, April 2, 2015

ሕወሓት የብአዴን እና ኦሕዴድ ሰዎችን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል

የብአዴን አባላት አሁንም ፈዘው የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ ራሳቸውን እና ሕሊናቸውን ለመጠየቅ ያልቻሉበት ደረጃ ላይ ናቸው:የመሻሻል ምልክቶች ቢታዩም መልሰው ይከስማሉ ያሉት የዚህ መረጃ አድራሾች ብኣዴንን አዳክሞ በአማርኛ ተናጋሪ ሌሎች ብሄሮች በተሻሻለ መልኩ ለመተካት በሕወሓት በኩል እየተሸረበ ያለው ሴራ በውስጡ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ እንዲነቅዝ አድርገዋል ያላቸውን አባላቱን ሁሉ ነቅሰው በማውጣት በብልሃት መዋጥ የሚሉ ስልቶች በብአዴን ካድሬዎች ዘንድ ጥያቄዎችን አጭሯል::ሕወሓት ኢሕኣዴግ ላይ እንከን ይፈጥሩ ይሆናል ለማሸነፍም ይሁን ለማጭበርበር እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን የብኣዴን በማግለል የጀመረውን ጉዞ መቀጠሉ ሲታወቅ ኦሕዴድ በበኩሉ ከተለያዩ ጸረ ልማት የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የበላይ የወረደ ትእዛዝ ሊፈጽሙ አልቻሉም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሰንሰለት ሰርተዋል የተባሉትን አባላቱን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል::

የአገዛዝ እድሜውን ለማስረዘም የማይቧጥጠው ነገር ያሌለው ሕወሓት በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል የተስፋፋው የውስጥ ሰላም ማጣት እና አለመተማመን ስላሰጋው በመጀመሪያ በብኣዴን ውስጥ ያሉትን እና ያሰጋሉ የተባሉ ባለልጣናትን እና ካድሬዎች ማስወገድ ስለሆነ ይህንኑ ስራውን በወያኔ ሚዲያ ላይ ባሰማራቸው ሰዎች ላይ እንደሚጀምር ታውቋል::በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ የብኣዴን ሰዎች በእረፍት ስም እቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ ሲሆን ካድሬዎችም እንዲሁ እረፍት እንዲወስዱ ፎርም እንዲሞሉ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል::ከእረፍት ከመመለሳቸው በፊት ለእያንዳንዱ በግል አርፎ እንዲቀመጥ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ የደህነንት አካል መዘጋጀቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::


Wednesday, April 1, 2015

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ ቤትፈላጊዎችን አስመርሯል


መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመጪውን ምርጫ መቃረብ ተከትሎ በአዲስአበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ 32ሺ ያህል ብዛት ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሳምንት በፊት ቢወጣም

ቅድሚያ ክፍያው የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በላይ ሆኗል።

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ ካለፈው ዘጠነኛ ዙር ጋር ሲነጻጸር እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ ራሱ አስተዳደሩ የጠቀሰ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎም አንድ መኝታ ያለው ቤት በካሬ 3ሺ 438 ብር ሲከፈልበት፣

ለ48 ነጥብ 34 ካሬሜትር ቤት 166ሺ ብር ገደማ ይሸጣል። የ20 በመቶ ቅድመ ክፍያው ደግሞ 32ሺ 238 ብር ይሆናል።

ባለሁለት መኝታ ክፍል ኮንዶሚኒየም የ20 በመቶ ቅድመ ክፍያ ወደ 64ሺ ገደማ ሲሆን፣ ይህን ያህል ብር በአንድ ጊዜ ከፍሎ ከባንክ ጋር ለመዋዋልና ተጨማሪ የቤቱን ማጠናቀቂያ ወጪ ለማውጣት በወር ገቢ ለሚተዳደሩ

በርካታ ሰዎች አስቸጋሪ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ቤት ፈላጊ ተናግረዋል ፡፡

አንድ ቤት ፈላጊ ባለአንድ መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት በዕጣ እንደደረሳቸውና በቅድሚያ የሚከፈለው የቤቱ ጠቅላላ ግምት 20 በመቶ ማለትም ወደ 32ሺ ብር ገንዘብ በአንዴ ለመክፈል መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል መንግስት የመኖሪያ ቤትን ችግር ለመቅረፍ በተመጣጣኝ ዋጋ በመስራት ዝቅተኛውን ሕብረተሰብ ጭምር የቤት ባለቤት አደርጋለሁ ብሎ ቃል ገብቶ እንደነበር ያስታወሱት አስተያየት ሰጪው፣ በአሁኑ ሰኣት

ግን ቤት ባለቤት መሆን የሚችለው 20 በመቶ ክፍያ ያጠናቀቀና ከባንክ ጋር መዋዋል የሚችል ብቻ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች ቤታቸውን ሳይረከቡ የሚቀሩ ሲሆን ፣ ብዙዎች ደግሞ ከአቅም በላይ ለሆነ ብድር በመዳረግ የኑሮ ቀውስ ውስጥ እየገቡ መሆኑን በመጠቆም ይህ ሁኔታ የግንባታውን ዓላማ የሳተ ነው ሲል ተችተውታል።


ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አበበ ገላው አጋለጠ

አዲስ ቮይስ– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) ተብሎ የተፈረጀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።


“ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ ከኦክቶበር 2010 ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ ሆነው በመንግስት የተሾሙ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩ ወቅት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ በአሁኑ ግዜ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ክፍል የበላይ ሃላፈ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።