የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ። አቶ አዲሱ ለገሰ በይፋ የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት በመሆን ከሚታወቁትና አሁን በሕይወት ከሌሉት አቶ ጠብቀው ባሌ ጋር የንግድ ግንኙነት የጀመሩት የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶችን እንዲያከፋፍሉ ያለጨረታ በመስጠት እንደነበር የደህንነት አባሉ ገልጸዋል። አቶ ጠብቀው ባሌ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር የተገናኙት በወቅቱ ስልጣን የያዙት የሕወሃት መራሹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፋብሪካው ሰራተኞች የሚከፍሉት ደሞዝ ሲያጡ እኚሁ ነጋዴ ደሞዝ በመክፈላቸው ነበር።
No comments:
Post a Comment