Tuesday, August 22, 2017

ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስገደድ ወይንም በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጥሪ አቀረበ።

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 16/2009) ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስገደድ ወይንም በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ ሕልውና ከምንጊዜውም በላይ በፈተና ውስጥ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅትም የተቃውሞ ሃይሎችም መተባበር እንደሚገባቸው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ከነሐሴ 12 እስከ 14/2009 በዩኤስ አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ባካሄደው 4ኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ባወጣው በዚህ መግለጫ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱና የቀጠሉ ችግሮችን በዝርዝር ተመልክቷል። ለሀገራችን ችግር ተመራጩ መንገድ እርቅ መሆኑን አመልክቶ ለዚህም ስርአቱን በመወጠር ወደ እርቅ ማምጣት ካልሆነም ከስልጣን በማስወገድ የስርአት ለውጥ ለማምጣት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝቧል። የሶስት ቀናት ጉባኤውን በቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ያካሄደው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ባወጣው ባለ 4 ገጽ መግለጫ ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጥሪ

ከሌብነት ጋር በተያያዘ እግድ በተጣለባቸው የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው ገንዘብ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 16/2009) ከሌብነት ጋር በተያያዘ እግድ በተጣለባቸው የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው ገንዘብ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በቢሊየን ብር የኮንስትራክሽን ስራዎችን በሚያንቀሳቅሱት በነዚህ ኩባንያዎች የባንክ አካውንት ውስጥ የተገኘው ከፍተኛው ገንዘብ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በታች እንደሆነም ተመልክቷል። ከ50 የሚበልጡ ዝቅተኛና መካከለኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ በፍርድ ቤት እግድ የወጣባቸው ከ200 የሚበልጡ ግለሰቦች ናቸው። አራት የኮንስትራክሽን ድርጅቶችም ንብረታቸው በአጠቃላይ ሀብታቸው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ መታገዱ ይታወሳል። እግድ ከተጣለባቸው ግዙፍ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ከፍተኛ ገንዘብ በባንክ ተቀማጩ የተገኘው ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆን ይህም 350 ሺህ ብር እንደሆነ ተመልክቷል። የበርካታ መቶ ሚሊየን ብሮችና የቢሊየን ብሮች ፕሮጀክቶችን በሚያንቀሳቅሱት

Friday, August 18, 2017

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉና በቀበሌ ቤት የሚገኙ የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ ከፍተኛ የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው።

(ኢሳት ዜና ነሐሴ 12/2009) በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉና በቀበሌ ቤት የሚገኙ የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ ከፍተኛ የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው። ለ30 እና 40 ዓመታት 5 ብር በወር ይከፍሉ የነበሩ በአዲሱ ተመን ከ200 እስከ 300 ብር እንዲከፍሉ እየተጠየቁ መሆናቸውን ከወሊሶ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ነዋሪው በወር በደመወዝ የማያገኘውን ብር ለቀበሌ ቤት እንዲከፍል በመወሰኑ ቁጣውን እየገለጸ መሆኑም ታውቋል። በወሊሶ ባለፈው ሳምንት የተጀመረው አድማ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ከመዲናዋ አዲስ አበባ በ114ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። ከ100ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረች፡ የቀደምትነቷን ያህል በስልጣኔው ብዙም ያልገፋች ከተማ ናት- ወሊሶ። ከአዲስ አበባ – ወደ ጂማ የሚወስደው መንገድ መሃል ለመሃል ሰንጥቆ የሚያልፍባት ወሊሶ በንግድ እንቅስቃሴ ሞቅ ያለች እንደሆነች ይነገርላታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳና የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትእዛዝ ሰጠ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 12/2009) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳና የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትእዛዝ ሰጠ። የሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ከጥቅምት 27-ጥቅምት 29/2010 ባለው ጊዜ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዙት ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አመራሮች ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጋር በተያያዘ የመከላከያ ምስክሮች እንዲሆኑ በመጠራታቸው ነው። በእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ለአራት ተከታታይ ቀናት

በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች በህቡዕ በመንቀሳቀስ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡእ ጀምሮ ለ5ቀናት የሚቆይ አድማ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በሌላ በኩል በአማራ ክልል በተለይም ባህርዳርን ጨምሮ በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ሌላ ዙር አድማና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊደረግ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ለነሃሴ 10 ተራዝሞ በነበረው የግብር መክፈያ ቀነ ገደብ አብዛኛው የንግዱ ማህብረሰብ ባለመክፈሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት መንገሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ። 

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ። በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሃት የተለየ ድጋፍ የሚደረግለት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አወዛጋቢ በተባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ግድያ፣ ድብደባና አስገድዶ መድፈር እየፈጸመ መሆኑንም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ለኢሳት እንዳስታወቀው የህወሃት መንግስት በሶማሌ ልዩ ሃይልና በስውር ባስታጠቃቸው የኦህዴድ ሚሊሺያዎች አማካኝነት የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ነው ብሏል። ከዚህ ግጭት ጀርባ የህወሃት እጅ እንዳለበት የጠቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ህወሃት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ግጭቱ መቀጠሉ አይቀርም ብሏል። ኦብነግ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉንና በህወሃት ሰራዊት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሱ ውጊያዎች መካሄዳቸውንም በመግለጪያው ጠቅሷል። የይገባኛል ጥያቄ የተነሳባቸውና ውዝግብ ያልተለያቸው 400 የሚሆኑና በሁለቱ ክልል

ከአሜሪካ ወደ ካናዳ አልበርታ አምርተው በጉብኝት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ሶስት ልጆቻቸው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ።

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 12/2009)ከአሜሪካ ወደ ካናዳ አልበርታ አምርተው በጉብኝት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ሶስት ልጆቻቸው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ። በአደጋው ከባድ የመቁስል አደጋ የደረሰባቸው የልጆቹ አባትና እናት ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን አንድ ሕጻንን ጭምሮ 3ቱ ልጆቻቸው ግን አደጋው በደረሰበት ስፍራ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ከአሜሪካ ወደ ካናዳ አልበርታ አምርተው በጉብኝት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት አንዲት የ16 አመት ታዳጊ ሴት፡የ11 አመት ወንድና የ10 ወር እድሜ ያላት ህጻን መሆናቸውን ግሎባል ኒውስ ዘግቧል። አደጋው የደረሰው ባለፈው ረቡእ አንድ ከባድ የጭነት መኪና በከፍተኛ የመተለለፊያ መንገድ ላይ የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩትን ኤስዩቪ መኪና በመግጨቱ ነው ተብሏል። ግጭቱ የደረሰው በምስራቅ ማእከላዊ አልበርታ ሐና አልታ በተባለ ስፍራ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህም 570ና 36 ተብለው በሚታወቁ ከፍተኛ የመተላለፊያ መንገድ መጋጠሚያ ላይ መሆኑም ታውቋል። የልጆቹ እናትና አባት ክፉኛ ቆስለው ፍትሒልስ በተባለ የሕክምና ተቋም እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ሁለቱም አደጋው ከደረሰበት ስፍራ በሔሊኮፕተር ተወስደው ሕክምና ላይ በመሆናቸውንና በሰመመን መስጫ ክፍል በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል። መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብም መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት መትረፉን የካናዳ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


Tuesday, August 8, 2017

It is just a matter of time before another protest flares up, says report by rights group

ESAT News (August 8, 2017)


The Human Rights Watch said on Monday that based on interviews conducted with protesters, including those who were detained during the state of emergency, it was just a matter of time before they took their grievances to the streets again.

Ethiopia: Number of people requiring relief food shot to 8.5 million


ESAT News (August 8, 2017)
Photo: Siegfried Modola/Reuters
Aid agencies and the Ethiopian regime say at least 8.5 million people will require relief food assistance in the second half of 2017, up from 5.6 million in January.
The new report by the UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs says the revised net requirements to address identified food and non-food needs for the remainder of the year is US$487.7 million.

Ethiopia: Strikes continue in Oromo and Amhara regions


ESAT News (August 8, 2017)
Strikes have continued in several towns in the Oromo and Amhara regions as regime security forces responded with arrests and intimidations.
Reports reaching ESAT say security forces arrested several people in the city of Bahir Dar following a stay at home strike on Monday that shuts down the entire city. Businesses and other services were shut down on

በደብረታቦር ከተማ የተጀመረው አድማ ቀጥሎ መዋሉ ታወቀ። በከተማዋ ሁሉም መደብሮች እንደተዘጉ ናቸው።

(ኢሳት ዜና– ነሐሴ 2/2009)በደብረታቦር ከተማ የተጀመረው አድማ ቀጥሎ መዋሉ ታወቀ። በከተማዋ ሁሉም መደብሮች እንደተዘጉ ናቸው። የአካባቢው ባለስልጣናት በከተማዋ እየዞሩ የንግድ ተቋማትን ማሸጋቸውንም ያገኘንው የምስልና የቪዲዮ ማስረጃ ያመለክታል። በደብረታቦር፣በወረታ፣በወልዲያና በተለያዩ አዋሳኝ አቅራቢያዎች የተመታው የህዝብ አድማ ሰበቡ ከግብር ጋር የተያያዘ ቢሆንም አጠቃላይ ምክንያቱ ግን በአገዛዙ መማረርና የአስተዳደር በደል ነው። በተለይ በደብረታቦር ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ችግር ከትእግስት በላይ እንደሆነበት የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ይህንኑ ተከትሎም በደብረታቦር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል።በደብረታቦር የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ እንደተዘጉ ናቸው። በህዝቡ አንድ መሆን ግራ የተጋቡት የአጋዛዙ ባለስልጣናትም የሚያደርጉት ቢያጡ እየዞሩ የንግድ መደብሮችን እያሸጉ መሆናቸው ተነግሯል። ሕብረተሰቡ ግን በካድሬ ባለስልጣናት ርምጃ አልተደናገጡም ነው የተባለው። አንድ አስተያየት ሰጪ እነሱ በራችን

በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ በምሽት መብራት በማጥፋት ወጣቶች እየታፈሱ መሆናቸው ተነገረ። የወጣቶቹ መታሰር በህዝብ ውስጥ ቁጣን ፈጥሯል

(ኢሳት ዜና —ነሐሴ 2/2009) በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ በምሽት መብራት በማጥፋት ወጣቶች እየታፈሱ መሆናቸው ተነገረ። የወጣቶቹ መታሰር በህዝብ ውስጥ ቁጣን ፈጥሯል። ከአድማው መመታት በኋላ ከፓፒረስ ሆቴል ወደ ቡና ባንክ መሄጃ ማንነቱ ያልታወቀ ወጣት ተገድሎ ተገኝቷል። በባህር ዳር የንግድ መደብሮችና ሆቴሎች ረፋዱ ላይ ተከፍተዋል።ይሁንና የአገዛዙ ባለስልጣናትና ታጣቂዎች አሁንም በስጋትና በፍርሃት ውስጥ መሆናቸው ነው የተነገረው። አድማ በታኝ ወታደሮችና የጸጥታ ሃይሎች የርእሰ መስተዳድሩን ቢሮ ጨምሮ በፓርቲ ጽህፈት ቤቶችና በአገዛዙ ተቋማት አሁንም ጥበቃ እያደረጉ መሆናቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል

በወልድያ አምቦ እና በሌሎችም ከተሞች የነጋዴዎች አድማ ለ2ኛ ቀን ሲቀጥል በባህርዳር ደግሞ ሱቆች ታሸጉ

ኢሳት ዜና ( ነሃሴ 2 ቀን 2009 ዓም)
ነጋዴዎች በዘፈቀደ የሚጣለውን የቀን ገቢ ግምትን ታሳቢ ያደረገውን ግብር በመቃወም የሚያደርጉት የስራ ማቆም አድማ እየተካሄደ ነው። በደብረታቦር፣ ወልድያ፣ አምቦ ፣ ጉዳርና ጎንጪ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም ሰናን ወረዳ የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው አድማዎች እየተካሄደ ነው። በአምቦ ለሚቀጥሉት 3 ቀናት የቆያል በተባለው አድማ፣ ከግብር ጥያቄ በተጨማሪ በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ ይጠይቃሉ። የአምቦ ህዝብ በአንድ ሃሳብ ሆኖ ተቃውሞውን በጽናት እያካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አገዛዙ በከተማው ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ከፍተኛ ጫና የአምቦን ህዝብ መንፈስ መስበር አለመቻሉንም እነዚህ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በኦሮምያና ሶማሊ ድንበር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን እንደሚገፉበት ገለጹ

ኢሳት ዜና ( ነሃሴ 2 ቀን 2009 ዓም) በኦሮምያና ሶማሊ ድንበር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን እንደሚገፉበት ገለጹ
በቅርቡ በኦሮምያና ሶማሊ ድንበር ከተማ በሆነው ጭናክሰን ከተማና አዋሳኝ ወረዳዎች የተካሄደው ተቃውሞ ሊቀጥል ይችላል በማለት ነዋሪዎች እያስጠነቀቁ ነው። ውጥረቱ አሁንም ድረስ መኖሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ቀደም ብሎ የኦሮምያና የሶማሊ ክልል መሪዎች ባደረጉት ስምምነት መሰረት ድንበር የመከለሉ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ የውዝግቡ መነሻ የሆነው ጭናክሰን ውስጥ የሚገኘው 5 መንደሮች ያሉት አንድ ቀበሌ ነው። ቀበሌው ከዚህ ቀደም ተካሂዶ በነበረው ማካለል ውሳኔ ሳይሰጥበት በሁለቱም ክልሎች ሲተዳደር ቆይቷል። የኦሮምያ ክልል ቀደም ብሎ በሶማሊ ክልል የነበሩና በክልሉ ውስጥ እንደልብ ለመገናኘት ይጠቅሙኛል ያላቸውን 3 መንደሮች እንዲሰጡት፣ በመልሱ በኦሮምያ ክልል ያሉ 3

በዲያስፖራ ቀን በአል ላይ የተገኙ የዲያስፖራ አባላት መሬት ሳያገኙ ወደ መጡበት ተመለሱ

ኢሳት ዜና ( ነሃሴ 2 ቀን 2009 ዓም) በዲያስፖራ ቀን በአል ላይ የተገኙ የዲያስፖራ አባላት መሬት ሳያገኙ ወደ መጡበት ተመለሱ
በቅርቡ በሃረር ከተማ የተከበረውን የዲያስፖራ ቀን በማስመልከት የክልሉ ፕሬዚዳንትና የኢህአዴግ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን፣ የ የዲያስፖራ አባላት በበአሉ ላይ የሚገኙ ከሆነ መሬት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የተገባላቸው ቃል ባለመከበሩ ዝግጅቱን አቋርጠው ወደ መጡበት በኪሳራ ተመልሰዋል፡፡ 

ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ።

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 2/2009)የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ዳኞች አልተሟሉም፣ዳኞች ታመዋል በሚል በማራዘም ላይ መሆኑም ታውቋል። የተመሰረተባቸው የአሸባሪነት ክስ ዝቅ ብሎ ጉዳያቸው በወንጀል ክስ እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈው ከሶስት ሳምንት በፊት ቢሆንም የዋስትና ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ ለ6ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ከ20 ወራት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ መታሰራቸው ይታወቃል። አመጹን በማነሳሳትም በአሸባሪነት ተወንጅለው ከሌሎች የኦፌኮ አመራሮች ጋር ወደ ወህኒ የተጋዙት አቶ በቀለ ገርባ ሐምሌ 6/2009 የቀረበባቸው ክስ ከአሸባሪነት ወደ ወንጀል ክስ ዝቅ እንዲል በፍርድ ቤት ተወስኗል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በተሰጠው ብይን መሰረትም የተሻሻለው ክስ ዋስትና የማይከለክል በመሆኑ አቶ በቀለ ገርባ በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡት ወዲያውኑ ቢሆንም ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት 5 ጊዜ የሰጠው ቀጠሮ የተለያዩ ምክንያቶች እየቀረቡበት ተስተጓጉሏል። ዳኞች አልተሟሉም ፣ወይንም ከዳኞቹ አንዱ ታሟል በሚል ለአምስት ጊዜ ሲገፋ የቆየው ውሳኔ ዛሬ ነሀሴ 2/2009 ደግሞ ተመሳሳይ ምክንያት ተሰጥቶት ለ 6ኛ ግዜ ለቀጣዩ ሳምንት ተቀጥሯል። ፍርድ ቤቱ ወይንም ማረሚያ ቤቱ አልያም ሁለቱም በጋራ የተለየ ምክንያት ካልሰጡ የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ በቀጣዩ ሳምንት ሀሙስ ነሀሴ 11/2009 ውሳኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በቅድሚያ በ2003 በተመሳሳይ በቀረበባቸው ክስ ለ5 አመታት ያህል ወህኒ ቆይተው በተፈቱ በወራት ልዩነት ተመልሰው መታሰራቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋው ተረጅዎች ቁጥር ወደ 8.5 ሚሊዮን አሻቀበ

ኢሳት ዜና ( ነሃሴ 2 ቀን 2009 ዓም) በኢትዮጵያ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋው ተረጅዎች ቁጥር ወደ 8.5 ሚሊዮን አሻቀበ
ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ድርቅ ምክንያት እለታዊ አፋጣኝ የምግብ ረድኤት ያስፈልጋቸው ከነበሩ 7.8 ሚሊዮን ተረጅዎች ወደ 8.5 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን የብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ከተመድ እና ሌሎች ዓለምአቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የጋራ ጥናት አስታውቋል። እንደ ግብረሰናይ ድርጅቶቹ ጥናት በኢትዮጵያ የተከሰተው የኢሊኖ የዓየር መዛባትን ተከትሎ የርሃብ ተጠቂዎች ቁጥር ከዚህ በላይም ሊጨምር እንደሚችል የጥናት ቡድኑ ስጋቱን አመላክቷል።

የወህኒ ቤት ሃላፊዎች በዶክተር መራራ ላይ የሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ያስቆጣቸው የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 2/2009) የወህኒ ቤት ሃላፊዎች በዶክተር መራራ ላይ የሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ያስቆጣቸው የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልላዊ አመጽ በህዳር 2008 የተቀሰቀሰባት ጊንጪ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 2/2009 አድማውን መቀላቀሏ ይፋ ሆኗል። ዶክተር መራራ ጉዲናን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በነጋዴዎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ ግብር እንዲነሳ በመጠየቅ የተጀመረው አድማ በአምቦ ለሁለተኛ ጊዜ ሲቀጥል በተመሳሳይ መስመር ላይ ያሉት ጊንጪና ጉደር ዛሬ አድማውን ተቀላቅለዋል።

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከሚባክንባቸውና ዘረፋ ከሚፈጸምባቸው መስኮች አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 2/2009) በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከሚባክንባቸውና ዘረፋ ከሚፈጸምባቸው መስኮች አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በተለይ ለባለስልጣናት የውጭ ሀገር ጉዞ በሚል ንግድ ባንክ የሚሰጠው ቪዛ ካርድ ሒሳቡ የማይወራረድ በመሆኑ ለከፍተኛ ብክነት ተጋልጧል። ለአንድ ጉዞ ለአንዳንዶች ከህግ ውጪ እስከ አንድ መቶ ሺ ዶላር እንድሚሰጣቸውም ምንጮች ገልጸዋል። በቪዛ ካርድ ከፍተኛ ገንዘብ በመውሰድ ከሚጠቀሙ ባለስልጣናት አንዱና ግንባር ቀደሙ ዶክተር አርከበ እቁባይ መሆናቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮች የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ለሒደቱ ዋና ተባባሪ መሆናቸውንም ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባለስልጣናቱ የሚያዘጋጀውን ቪዛ ካርድ ይዘው ከሀገር የሚወጡት ባለስልጣናት ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ከማረፍ ጀምሮ በልዩ ልዩ አላስፈላጊ ወጪ ገንዘቡን በማባከን በሳምንት ጊዜ ውስጥ ጨረስን ብለው እንደገና የውጭ ምንዛሪ እያስሞሉ እንደሚጠቀሙም ተመልክቷል።

Thursday, August 3, 2017

የአገሪቱን ከባድ ሚስጢር ለኢሳት አሳልፎ ሰጥቷል በተባለው የኢንሳ ሰራተኛ ላይ የቀረበው የክስ ቻርጅ አገዛዙ ለሳተላይት አፈና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያወጣ አረጋገጠ

በዝግ ችሎት የታየው የክስ ሂደት እልባት አግኝቷል።
ጸጋዬ ተክሉ ይባላል። በመከላከያ ዩኒቨርስቲ ከ1992 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተምሮ፣ በዚሁ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ ሰርቷል። ምርጫ 97ትን ተከትሎ በከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ የወደቀው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ከውጭ አገር ወደ አገሪቱ የሚተላለፉ ሚዲያዎችን ማፈን አስፈላጊ ነው ብሎ በማመኑ የተለያዩ የማፈኛ መሳሪያዎችን ለመግዛት የውጭ ገበያዎችን ማሰስ ጀመረ። ለስራው ያስፈልጋሉ ያላቸውን ታማኝ ኢንጂነሮች እያፈላለገ ቀጠረ። የአፈናውን ስራ እንዲሰራ ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የተባለ ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 130/1999 መሠረት አቋቋመ፡፡ የኤጀንሲውን ተግባር እና ኃላፊነት እንደገና ለማሻሻል ደግሞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 250/2003 እንዲሁም በድጋሚ በ2006 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 808/2006 የኤጀንሲው ተግባሮች እና ኃላፊነቶች ተሻሽለው እንዲቋቋሙ አደረገ። በርካታ በሳይንስና በሌሎችም የትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ ሰራተኞች ሲቀጠሩ ጸጋዬም በ1998 ዓም ተቀጠረ።

የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ። 

የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ። አቶ አዲሱ ለገሰ በይፋ የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት በመሆን ከሚታወቁትና አሁን በሕይወት ከሌሉት አቶ ጠብቀው ባሌ ጋር የንግድ ግንኙነት የጀመሩት የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶችን እንዲያከፋፍሉ ያለጨረታ በመስጠት እንደነበር የደህንነት አባሉ ገልጸዋል። አቶ ጠብቀው ባሌ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር የተገናኙት በወቅቱ ስልጣን የያዙት የሕወሃት መራሹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፋብሪካው ሰራተኞች የሚከፍሉት ደሞዝ ሲያጡ እኚሁ ነጋዴ ደሞዝ በመክፈላቸው ነበር።


አርዱፍ የትጥቅ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር -አርዱፍ፣የአፋር ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን እስኪቀዳጅ ድረስ የህወኃት አገዛዝን ለማስወገድ የጀመረውን የትጥቅ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ድርጅቱ በላከው መግለጫ በአሁኑ ወቅት የሙስና ዘመቻ የሚል ድራማ የጀመረው የህወኃት አገዛዝ በሌላ በኩል የብሄር ብሄረስቦችን ቀንን በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ለማክበር በሚል በርሀብ፣ በድህነትና በችግር ላይ የሚገኘውን የአፋር ሕዝብ ለበዓሉ የሚሆን ገንዘብ አዋጣ በማለት እንሥሶቹን እንዲሸጥ እያስገደደው እንደሆነ አመልክቷል።
በአፋር ክልል ጨርሶ መልካም አስተዳደርና ማህበራዊ ፍትህ የሚባል ነገር እንደማይታወቅ የጠቀሰው አርዱፍ፣ክልሉ እየተመራና እየተዳደረ ያለው መቀመጫውን አዲስ አበባ ባደረገው በፌዴራል መንግስቱ ሳይሆን መቀሌ በሚገኘው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ነው ብሏል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 በአዲስ አበባ ከተካሄደው የአፋር ብሄራዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ኮንግረስ በኋላ፣ ህወኃት የክልሉን ሥልጣን በስዩም አወል ለሚመራው ቡድን ለመስጠት እንደወሰነ ያወሳው አርዱፍ፣ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአፋር ክልል የሚተዳደረው በትግራይ ክልል መሆኑን ጠቁሟል።
ወዲያውኑ በስድስተኛው የኤ ኤን ዲ ፒ ጉባኤ ያለ አፋር ህዝብ ውክልና እና ይሁንታ ስዩም አወል የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ መሾሙን መግለጫው አውስቷል።
ስዩም ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጡን ተከትሎ በዙሪያው ዘመዶቹን በማሰባሰብ በህወኃት የተሰጠውን ተልዕኮ እየፈጸመ እንደሚገኝ የጠቀሰው መግለጫው፣ የቀድሞው ኢስማኤል አሊ ሴሮም ሆነ ስዩም አወል የአፋርን ህዝብ ከማገልገል ይልቅ ለህወኃት አለቆቻቸው እየሰገዱ መኖርን የመረጡ መሆናቸውን አትቷል።
እንደ አርዱፍ መግለጫ በአፋር ክልል ለሚካሄዱ ነገሮች በሙሉ አዋጅ፣መመሪያና ውሳኔ የሚተላለፈው በትግራይ ክልል ምክር ቤት ሲሆን፤ የአፋር ክልል ምክር ቤት ምንም ዓይነት ውሳኔ በራሱ ለማሳለፍም ሆነ ለመሥራት ሥልጣን የለውም።
“የአፋር ሕዝብ ያለ ነጻነት በፍርሃት እየኖረ ነው፤የአፋር ክልል በረሃብና በጠኔ እየተሰቃዬ ነው” ያለው አርዱፍ፤ የህወኃትን አጀንዳ ለማስፈጸም ፍቃደኛ ያልሆኑ አፋሮች ከአርዱፍ ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉ ከህግ አግባብ ውጪ እንደሚታሰሩ፣እንደሚደበደቡና እንደሚወገዱ አመልክቷል።
በስዩም አወል አመራር ጎሰኝነት የክልሉን ፖለቲካ ተቆጣጥሮታል የሚለው አርዱፍ፤ የአፋር ሕዝብ ሌላው ቀርቶ እንዴት መናገርና ማሰብ እንዳለበት እየተወሰነለት ነው ብሏል።
በኢትዮጵያ የአድሎ አገዛዝ ተወግዶ የተሻለ ፍትሀዊ ስርዓት ለማምጣት የሚታገሉ ተቃዋሚዎች የህዝብን ፍላጎን ባማከለ መልኩ ትግላቸውን እንዲያደርጉ የመከረው መግለጫው፤” እኛ አርዱፎች የራሳችንን ድርሻ ለማድረግ ከመቼውም በላይ ዝግጁ ነን” ብሏል።
አርዱፍ አክሎም ሆነ ብሎ የአፋርንና አጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ እያሸበረና እያተራመሰ ያለውን የህወኃት አገዛዝ ለማስወገድና በምትኩ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎቱን በራሱ የሚወስንበትና ዋስተኛ የሚሆነው እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማስፈን የጀመረውን የትጥቅ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።


የኦነግን አላማ ስታራምዱ ነበር የተባሉ 31 ተከሳሾች ተከላከሉ ተባሉ

የማርያም ፀበል እድርን በሽፋንነት በመጠቀም የኦነግ ወጣቶች ክንፍ የሆነውን ቄሮ ቢልሱማ በማደራጀት፣ አባላትን በመመልመል፣ የመሰብሰቢያ ቦታዎችን በመለየት እና በማዘጋጀት የኦነግን አላማ ስታራምዱ ነበር የተባሉ በእነ ሀብታሙ ሚልኬሳ የክስ መዝገብ የተከሰሱ 31 ግለሰቦች እንዲከላከሉ ብይን እንደተሰጠባቸው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ አካውንቱ ላይ ዘግቧል፡፡ በመዝገቡ ላይ ሁለት ክሶች የቀረቡ ሲሆን 1ኛ ክስ በ1ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ ሚልኬሳ እና 2ኛ ተከሳሽ ረዳት ሳጅን ጫላ ፈቃዱ ላይ የቀረበ ነው፡፡
ሁለቱ ተከሳሾች ‹‹የቄሮ ቢሉስማ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር በመሆን አባላት የኦነግን ባንዲራ እንዲይዙ በማድረግ ለድርጅቱ ታማኝ እንዲሆኑ፣ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የድርጅቱን አላማ ማጠናከር እንዳለባቸው ቃል በማስገባት፣ ድርጅቱን ለማጠናከር አባላት መዋጮ እንዲያወጡ በማድረግ፣ ለገቢ ማሰባሰቢያ የመፅሃፍና የኦነግ ባንዲራ ሽያጭ እንዲያከናውኑ እና ሌሎች ትዕዛዞችንም በአመራርነት በማስተላለፍ›› ተሳትፈዋል የሚል ዝርዝር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀፅ 32 (1/ሀ) እና የፀረሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652 /2001 አንቀፅ ሁለት ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በአመራርነት ወይንም በውሳኔ ሰጭነት ተላልፈዋል በሚል ተጠቅሶባቸው የነበረውን ክስ እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል፡፡ ይህ አንቀፅ ከ20 አመት እስከ እድሜ ልክ እንደሚያስቀጣ በአዋጁ ላይ ተቀምጦአል፡፡
ሁለተኛ ክስ ከ3ኛ እስከ 32ኛ ባሉት ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን ተከሰሾቹ ቀድሞ ተከሰውበት የነበረውን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 32/1ሀ እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የቄሮ ቢሉሱማ አባል በመሆን፣ስብሰባዎች ላይ በመገኘት እና አባላትን በመመልመል በማንኛውም መንገድ በአባልነት ተሳትፋችኋል ተብለው የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል 18ኛ ተከሳሽ ካሳሁን ሙሊሳ በህመም ምክንያት ሆስፒታል ስለገባና ፍርድ ቤት መምጣት ስላልቻለ ብይኑ በማረሚያ ቤት እንዲደርሰው ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል 22ኛ ተከሳሽ አብዲሳ ቦካ ቱጅባ በቃጠሎው ወቅት በመገደሉ ክሱ እንደተቋረጠ ተግለፆአል፡፡ የ26 አመት እድሜ የነበረው ወጣት አብዲሳ ደቡብ ክልል ውስጥ ሶዶ ከተማ በመምህርነት ሙያ ተሰማርቶ የነበር ሲሆን አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ተይዞ እንደታሰረ ተዘግቧል። ሟች አብዲሳ ቦካ ህዳር 9/2008 ዓ.ም በቦሌ ቡልቡላ ላይ ተካሂዷል ተብሎ በክሱ ላይ በተጠቀሰው ስብሰባ ላይ ተገኝቷል፣ የፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር አድርጓል እና የድርጅቱ ገቢ ማስገኛ የሚሆን ገንዘብ አሰባስቧል የሚል ክስ ቀርቦበት እንደነበር የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሀምሌ 27/209 ዓ.ም ብይኑን ከሰጠ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽን ጨምሮ 20 ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር እናቀርባለን በማለታቸው ከህዳር 11- 15 /2010 ዓ.ም መከላከያ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀሪዎቹ ተከሳሾች እንደማይከላከሉ በማሳወቃቸው ለፍርድ ነሃሴ 4/2009 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡ ህዳር 19/2008 ዓ.ም ተይዘው ማዕከላዊ ታስረው ከነበሩት 58 ግለሰቦች መካከል 26ቱ ማዕከላዊ ታስረው ከቆዩ በኋላ ከእስር ተፈትተዋል፡፡