Sunday, February 8, 2015

ሰበር ዜና- ህገ ወጥ የመሬት ቅርምት በእንጦጦ መ/ስብሀት ቅ/ስላሴ ቤተ ክርስቲያን !

የእንጦጦ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ንብረትነት በካርታና ፕላን ውስጥ ያላዉ ቦታ በህገ ወጥ መንገድ እየተቸበቸበ መሆኑን ምእመናን ገለጹ!! ምእመናኑ ህገ ወጥ የመሬት ቅርምቱን ሁሉም አውቆት እንዲያስቆመዉ ሁሉም ክርስቲያኖችና ኢትዮጵያዉያን መረባረብ እንዳለባቸዉ አስታውቀዋል፡፡ ዛሬ ከወደ ጠዋት አከባቢ በቤተ ክርስቲያኑ ከሚገለገል ምዕመን የደረሰኝን ጦማር እንዳለ እንደሚከተለዉ አቅርቤዋለሁ፡፡

‹‹በአዲስ አበባ ከተማ በተለየ ስሙና ቦታው እንጦጦ የሚገኝ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ውስጥ እተፈጸመ ያለ አስገራሚና በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና አማኝ ሊፈጸም የማይገባ ተግባር ስለተመለከትኩ ፍርዱን ለአንድ አምላክ በመተው እኔ ግን እንደ አንድ ምእመን ያየሁትንና የሰማሁትን ለእናንተ በማካፈል እውነታው ምን ይመስላል የሚለውን ከሚዛን እንድታደርሱ አደራውን ሰጠሁ በቅርቡ የተመረጡት የሰበካ ጉባዔ አባላት በቤተክርስትያን ስም ሁለት ማህተም በማሰራት የቤተክርስትያኑ ንብረት የሆነውን ቦታ በማጭበርበር እየሸጡት ነው፡፡ የቤተክርስትያኑ ሰንበቴ ቤት የነበረውን ክፍት ቦታ ለቤተክርስትያኑ ገቢ ማስገኛ በማለት ለግለሰብ ቢያከራዩትም ሰነዱን በማጥፋት ካርታ አስወጥተው እንደሸጡት ታውቋል አሁን ደግሞ የማቴዎስ ግቢ የሚለባለውን የቤተክርስትያኑን ቦታ አገልጋይ ካህናትን በማስወጣት ለግለሰብ ለ20 ዓመት ሊሸጡት እየተደራደሩ ነው ይህንንም ለማሳመን ሁለት ዓይነት የተጭበረበረ ሰነድ አቅርበዋል ስለዚህ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን የቤተክርስትያን ቦታ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር በህግ አምላክ ብለን እናስቁማቸው::


No comments:

Post a Comment