Wednesday, February 25, 2015

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን ገለጸ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ከምንም በላይ ግን በዕጩዎች ስረዛና ወከባ በርካታ ጊዜ አጥፍቶብናል፡፡›› ሲሉም ሰልፉ የተራዘመበትን ምክንያት ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ዕጩዎች በዝርዝር ባለማሳወቁ፣ አባል ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ እያቀረቡ በመሆኑና አሁንም ድረስ ከምርጫ ቦርድ ጋር ያሉት ችግሮች ያልተፈቱ በመሆናቸው ትብብሩ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀን ወደፊት ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡


No comments:

Post a Comment