Saturday, February 28, 2015

ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!

ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያ

በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። 

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።

የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።

Friday, February 27, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ እንደ አልቤርጎ እየተከራየ ነው

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2 ሺ 700 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ አልጋዎች ለተመላላሽ ተማሪዎችና ለማይታወቁ ሰዎች እየተከራዩ መሆኑ ታውቓል።በቅርቡ በአክሱም ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ለውጥ ምክርቤት ጉባዔ ላይጉዳዩ በይፋ የተነሳ ሲሆን በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ከ750 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ከ2ሺ 700 በላይ አልጋዎች በድብቅ ሲከራዩ ቆይተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተመላላሽ ተማሪነታቸው
የሚያውቃቸው ተማሪዎችና ማንነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች በወር ለአንድ አልጋ 400 ብር ሒሳብ እየከፈሉ እንደሚጠቀሙባቸው መረጋገጡን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ መሰረት በወር ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በሙስና ይበላል። በውይይቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው አንዳንድ አመራሮች ነገሩን ክደው የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን እውነታውን ለመግለጽ ተገደዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የተገኘው የማደሪያ ክፍሎች ቁጥር፤ ማደሪያ የለም ተብለው ከሚመላለሱ ተማሪዎች ቁጥር ጋር ተቀራራቢ ሆኖ መገኘቱም በዚሁ መድረክ ይፋ ሆኖአል፡፡
ይህ ዓይነቱ ሙስና በሌሎችም የመንግስት
ዩኒቨርሲዎች ከመለመዱ የተነሳ እንደሕጋዊ አሰራር እየታየ መምጣቱንም በውይቱ ወቅት ተነስቷ


ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ 

የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆታ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።
ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው። ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።


Thursday, February 26, 2015

ምርጫ ለኢትዮጵያ ወታደርና ፓሊስ: – ለህወሓት ባርነት ወይስ ለኢትዮጵያ ነፃነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውትድርና ከፍተኛ ክብር አለው። ውትድርና ከሙያና ሥራ በላይ የነፃነትና የክብር መገለጫ፤ ሀገርን ከባዕድ ወረራ መከላከያ ጋሻ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህግና ሥርዓት አክባሪ በመሆኑ ለፓሊስም ከፍተኛ አክብሮት አለው። የፓሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ መሆኑ በኢትዮጵያ ባህል የተከበረ ቦታና እውቅና አለው።

በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ግን ይህ እየተቀየረ ነው። የህወሓት አዛዦች እየመሩት ያለው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ሀገርን ከባዕድ ጠላት ከመከላከል ጋር ምንም ዝምድና በሌላቸው ሁለት አበይት ተግባራት ላይ ተጠምዷል። በህወሓት አዛዦች የሚመራው ሠራዊት ዋነኛ ተግባር ለሰብዓዊ መብቶቻቸው መከበር እና ለፍትህ መስፈን የሚታገሉ ዜጎችን ማጥቃት ሆኗል። የጦሩ ሁለተኛው አቢይ ተግባር ደግሞ ለአዛዦች የግል ጥቅም ማካበቻ ገቢዎችን በሚያስገኙ ሥራ ላይ መሠማራት ነው።

አብዛኞቹ የመንግሰት ጋዜጠኞች የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን መረጃዎች አመለከቱ

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጋዜጠኞች አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን ኢሳት በደረሰው የአባላት ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ ሰነድ ለማረጋገጥ ችሎአል።
በቀድሞው ኢቲቪ በአዲሱ አጠራሩ ኢቢሲ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ስር የሚሰሩ ዳይሬክተሮች፣ የዜና አዘጋጆች፣ የወቅታዊ ዘገባ አቀናባሪዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞች ፣ የካሜራ ባለሙያዎች፣ ቴክኒሻኖችና የተለያዩ የድጋፍ ሰራተኞች የህወሃት፣ የብአዴን፣ ኢህዴድ ወይም የደህዴግ አባላት መሆናቸው በሰነዱ ላይ በዝርዝር ተቀምቷል። ጋዜጠኞቹ የኢህአዴግን ፖሊስ ለህዝብ ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ በየጊዜው በተደራጁበት ህዋስ ስር ግምገማ እንደሚደረግባቸውና ከኤ እስከ ዲ የሚደርስ ውጤት እንደሚሰጣቸው ከሰነዱ ለመራዳት ይቻላል።
የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በህዝብ ንብረት የሚተዳዳሩ ቢሆንም፣ የአንድ ፓርቲ አገልጋይ ለመሆናቸው ከዚህ በላይ ማስረጃ እንደሌለ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የሚዲያ ባለሙያ ተናግረዋል።
ጋዜጠኞች የኢህአዴግ አባላት የሚሆኑት ጥቅማቸውን አስበው እንጅ በድርጅቱ አምነውበት ላይሆን እንደሚችል፣ ከሚሰሩት ስራ መናገር ይቻላል የሚሉት አስተያየት ሰጪው፣ አብዛኞቹ አጋጣሚውን ሲያገኙ ወደ ውጭ ወጥተው መቅረታቸው አባልነቱ ለጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ህዳሴ የሚባለውን የኢህአዴግ አዲስ ልሳን ስፖንሰር እንዲያደርጉ እየታዘዙ ነው።
ኢሳት ከአዲስ አበባ ኢህአዴግ ኮሚቴ ጽ/ቤት በአስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ላይ ለማረጋገጥ እንደቻለው፣ በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ታትሞ የሚወጣው ህዳሴ የተሰኘው የኢህአዴግ የፖለቲካ ልሳን ጋዜጣ በስፖንሰር ሺፕ ሰበብ በመንግስት መ/ቤቶች ባጀት ወጪ እንዲታተም እየተደረገ ነው።
ከጽ/ቤቱ የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከ5 በላይ ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር መ/ቤቶች በአድራሻቸው ተጽፎ የተሰራጨው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው እያንዳንዱ መ/ቤት ስፖንሰር ለማድረግ የተስማማበትን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድነት ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ኮሚቴ ጽ/ቤት ስም ወደሚታወቀው ባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ሲሆን ለአንድ ጊዜ ማሳተሚያ እስከ 300,000 ብር እንዲከፍሉ ታዘወዋል።


ድል የአላማ ጽናት እንጂ የመሳሪያ ጋጋታ ዉጤት አይደለም

ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ዉስጥ ዋና ከተማዋን ከተለያዩ የጣሊያን ከተሞችና ጣሊያንን ከፓሪስ፤ከሙኒክ፤ከጄኔቫና ከቪዬና ጋር የሚያገናዉና በአመት ከ 150 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ አንድ ትልቅ የባቡር መስመር አለ። ይህ የባቡር መስመር የሚጠራዉ ሮማ ተርሚኒ እየተባለ ሲሆን የባቡር መስመሩ አድራሻ ደግሞ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ በመባል ይታወቃል። ወደዘህ ትልቅ ባቡር መስመር ሲገባ አንድ እጅግ በጣም ትልቅ ሀዉልት ወለል ብሎ ይታያል፤ ይህም ሀዉልት የአምስት መቶዎቹ አደባባይ ወይም ፒያዛ ዴ ቺንኮቼንቶ በመባል የታወቃል። የፒያሳ ዴ ቺንኮቼንቶ መታሰቢያ ሀዉልት የተሰራዉ ወራሪዉ የጣሊያን ጦር አገራችንን ለመወረር ሲመጣ ዶጋሌ ላይ በራስ አሉላ ጦር የተገደሉትን አምስት መቶ የጣሊያን ወታደሮች ለማስታወስ ነዉ። በ1877 ዓም ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ጦርና ጎራዴ በታጠቀዉ የራስ አሉላ ጦር ዉርደት የተከናነበዉ የጣሊያን ወራሪ ሠራዊት ብድሩን ለመመለስ በ1888 ዓ.ም ብዛት ያለዉ ካባድ መሳሪያ፤ መድፍና መትረየስ ታጥቆ አድዋ ድረስ ቢመጣም በዳግማዊ ሚኒሊክ የተመራዉ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደገና ዉርደት አከናንቦት በጥቁር ህዝብ ታሪክ ዉስጥ ትዝታዉ ምንግዜም የማይደበዝዝ ድል አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ ሠራዊት ዶጋሌና አድዋ ላይ እስካፍንጫዉ የታጠቀዉን የጣሊያን ወራሪ ጦር ደጋግሞ ያሸነፈዉ በመሳሪያ በልጦ ወይም የተሻለ የዉትድርና ችሎታ ስለነበረዉ ሳይሆን ከወራሪዉ ጦር የበለጠ ቆራጥነትና የአለማ ጽናት ሰለነበረዉ ነዉ።

በወላይታ ዞን 30 የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ታሰሩ

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን 30 የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ አስታወቁ፡፡

ከዞኑ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ታደመ ፍቃዱ እና ፓርቲውን በመወከል ለተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት መምህር አለማየሁ አዴ እንደገለጹት በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ልዩ ስሙ ዋቺጋ አሼ በተባለ ቀበሌ 30 የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከትናንት በስቲያ (የካቲት 17/2007 ዓ.ም) ለእስር ተዳርገዋል፡፡

አቶ ታደመ ፍቃዱ እንዳስረዱት አባላቱና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን ለምን ትደግፋላችሁ፣ ለምን አባል ትሆናላችሁ…ፓርቲው እኮ ከምርጫ ታግዷል፣ ህገ-ወጥ ነው›› በሚል ሰበብ ስሙን እንኳን ‹‹ሰማያዊ ብላችሁ አትጥሩ›› ተብለው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከታሳሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን የሚገልጹት መምህር አለማየሁ በበኩላቸው እስረኞችን እንዳነጋገሯቸው በመጥቀስ፣ ‹‹የምትመርጡት ማንን እንደሆነ እናውቃለን፣ ሌላ ፓርቲ መምረጥ የለባችሁም….ኢህአዴግን ነው መምረጥ የሚኖርባችሁ›› እያሉ እንደሚያስፈራሯቸው አስረድተዋል፡፡

መምህር አለማየሁ አዴ ‹‹አንተ ለምን ልትጠይቃቸው መጣህ›› ተብለው እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውሰው፣ እስረኞቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንም ገልጸዋል፡፡ አባላትና ደጋፊዎቹ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡


Wednesday, February 25, 2015

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ


የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን ገለጸ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ከምንም በላይ ግን በዕጩዎች ስረዛና ወከባ በርካታ ጊዜ አጥፍቶብናል፡፡›› ሲሉም ሰልፉ የተራዘመበትን ምክንያት ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ዕጩዎች በዝርዝር ባለማሳወቁ፣ አባል ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ እያቀረቡ በመሆኑና አሁንም ድረስ ከምርጫ ቦርድ ጋር ያሉት ችግሮች ያልተፈቱ በመሆናቸው ትብብሩ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀን ወደፊት ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡


የአቶ አባይ ጸሃየ ንግግር ተጨማሪ ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ሊግ አስታወቀ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አባይ ጸሃየ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል እንደሚተገበር በድብቅ ሲናገሩ መደመጣቸው ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አመጽን የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን ፣ ከዚህ ቀደም የደረሰው ደም መፋሰስ ሳይበቃ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዲኖር የሚጋብዝና የሰው ህይወት እንዲጠፋ የሚያደርግ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ሊጉ ባወጣው መግለቻ ጠቅሷል።
የባለስልጣኑ እብሪት የተሞላበት ንግግር ለውይይት፣ ለምክክር እንዲሁም ለዜጎች ይሁንታ ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ አደኛ ነው ሲልም አትቷል።
ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ታጣቂ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 70 የኦሮሞ ተወላጆች መሞታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸውን ያስታወሰው መግለጫው፣ የህወሃት አገዛዝ ባለፉት 24 አመታት በኦጋዴን፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸማቸው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሆን ተብሎ ታቅዶ የተፈጸሙ ናቸው።
አገዛዙ በሚፈጽመው ድርጊት በዘር ማጥፋትና በሰው ልጆች ላይ በሚፈጸም ወንጀል እንደሚያስጠይቀው የሰብአዊ መብት ሊጉ አክሎ ገልጿል። አቶ አባይ ጸሃየ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በሚቃወሙ ላይ ሁሉ ፣የኦህዴድ ባለስልጣኖችን ጨምሮ ፣የሃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዝተዋል።


የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጨለማ ቤት መታሰራቸውን አስታወቁ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡
ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ‹‹መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ›› እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ ክፍል እንዳሰሯቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ አሁንም መረጃየን ሰብስቤ አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ 8 ቀናት ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡
ተጠርጣዎቹ በማዕከላዊ እየደረሰባቸው የሚገኘውን ሰቆቃ አስመልክተው ለፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የቀረበበትን አቤቱታ እንዲያስተካክል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በጎንደርና ጎጃም አካባቢዎች የዛሬ አራት ወር ገደማ በፖሊስ ታስረው ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲዛወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ ጠበቃቸው በተደረገባቸው ክልከላ ምክንያት ተጠርጣሪዎቹን ካገኟቸው 2 ወር እንደሞላቸው ተናግረዋል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አቶ አግባው ሰጠኝ እየተፈጸመበት ያለውን የመብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አድማውን ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መሰረት አመራሮቹ የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


Tuesday, February 24, 2015

የዚህ ሁሉ እልቂት “ኩሹፍ” ሲገለጥ( አርአያ ተስፋማሪያም)

ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም፣ ባለቤታቸውና ሌሎች አንገታቸው ላይ ስላጠለቁት በተመለከተ አንድ የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱ ታጋይ በግል ያደረሱኝ መልእክት እንዲህ ሲል ይጀምራል « በታጋዮች ዘንድ “ኩሹፍ” ተብሎ ይጠራል። ታጋዩ ከሞተ በኋላ የሚገነዝበት ጨርቅ ነው። ድርጅቱ አላማ ያለው የመሰለው አብዛኛው ታጋይ ያን ጨርቅ አንገቱ ላይ በማጥለቅ ለመሰዋት (ለመሞት) ቁርጠኝነቱን የሚያሳይበት ነበር። 98 በመቶ የሚሆነው ተዋጊ ያልተማረ ስለነበረ የድርጅቱ አላማና አካሄድ ሊያውቅበት የሚችል አንድም መንገድ አልነበረም። በእሱ ደምና አጥንት ተረማምደው ሲያበቁ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስፈፀሙ። 36 ሺህ የህወሀት ታጋዮችን ገና በጠዋቱ አባረው ለአስከፊ የጐዳና ህይወት ዳረጓቸው። ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን በብሄር ፖለቲካ እርስ በርስ እንዲናቆሩ እነመለስ የጥፋት ወጥመድ ዘረጉ። “ፓርቲው ወዴት እየሄደ ነው?..ግምገማ መካሄድ አለበት፤ ሙስና ተቀጣጥሏል..” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱና ከጋንታ እስከ ሬጅመንት አዛዥነት (ኋላ መኮንኖች) ቦታ የነበራቸው 5 ሺህ ታጋዮች ሆለታና ታጠቅ እስር ቤቶች ታጐሩ። አቶ መለስ 36 ሺህ ታጋይ በ84 ዓ.ም ሲያባርሩ «ጓሃፍ ፅረጉለይ..» ማለትም “እነዚህን ቁሻሻ ጥራጊዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡

ሽመልስ ከማል አሜሪካ ጥገኝነት ሊጠይቁ ነው ? አርአያ ተስፋማሪያም

የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል። በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።



ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።


Monday, February 23, 2015

ድል የአላማ ጽናት እንጂ የመሳሪያ ጋጋታ ዉጤት አይደለም

ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ዉስጥ ዋና ከተማዋን ከተለያዩ የጣሊያን ከተሞችና ጣሊያንን ከፓሪስ፤ከሙኒክ፤ከጄኔቫና ከቪዬና ጋር የሚያገናዉና በአመት ከ 150 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ አንድ ትልቅ የባቡር መስመር አለ። ይህ የባቡር መስመር የሚጠራዉ ሮማ ተርሚኒ እየተባለ ሲሆን የባቡር መስመሩ አድራሻ ደግሞ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ በመባል ይታወቃል። ወደዘህ ትልቅ ባቡር መስመር ሲገባ አንድ እጅግ በጣም ትልቅ ሀዉልት ወለል ብሎ ይታያል፤ ይህም ሀዉልት የአምስት መቶዎቹ አደባባይ ወይም ፒያዛ ዴ ቺንኮቼንቶ በመባል የታወቃል። የፒያሳ ዴ ቺንኮቼንቶ መታሰቢያ ሀዉልት የተሰራዉ ወራሪዉ የጣሊያን ጦር አገራችንን ለመወረር ሲመጣ ዶጋሌ ላይ በራስ አሉላ ጦር የተገደሉትን አምስት መቶ የጣሊያን ወታደሮች ለማስታወስ ነዉ። በ1877 ዓም ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ጦርና ጎራዴ በታጠቀዉ የራስ አሉላ ጦር ዉርደት የተከናነበዉ የጣሊያን ወራሪ ሠራዊት ብድሩን ለመመለስ በ1888 ዓ.ም ብዛት ያለዉ ካባድ መሳሪያ፤ መድፍና መትረየስ ታጥቆ አድዋ ድረስ ቢመጣም በዳግማዊ ሚኒሊክ የተመራዉ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደገና ዉርደት አከናንቦት በጥቁር ህዝብ ታሪክ ዉስጥ ትዝታዉ ምንግዜም የማይደበዝዝ ድል አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ ሠራዊት ዶጋሌና አድዋ ላይ እስካፍንጫዉ የታጠቀዉን የጣሊያን ወራሪ ጦር ደጋግሞ ያሸነፈዉ በመሳሪያ በልጦ ወይም የተሻለ የዉትድርና ችሎታ ስለነበረዉ ሳይሆን ከወራሪዉ ጦር የበለጠ ቆራጥነትና የአለማ ጽናት ሰለነበረዉ ነዉ።

Sunday, February 22, 2015

«አፋን ኦሮሞ ስለማትናገሩ በኦሮሚያ መወዳደር አትችሉም» – ምርጫ ቦርድ

አቶ ምርቱ ጉታ ዋቅጅራ የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ቀጠና አደራጅ ነበሩ። የአዳማ ናዝሬት አንድነት ሊቀመንበርም ሆነው ሰርቷል። አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ የአዳማ አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ነበሩ።

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት ፣ የአንድነትን ፓርቲ ሕጋዊነት ላደራጀው የተለጣፊው የትግስቱ ቡድን ሲሰጥ ፣ አቶ ምርቱ፣ አቶ ተስፋዬና በርካታ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ማሊያ ለብሰው ትግሉን ቀጠሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ለመወዳደር፣ አቶ ምርቱና እና አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ በአዳማ አንድ ምርጫ ጣቢያ ለመመዝገብ ይሄዳሉ። ከብሔራዊ ቋንቋው ውጪ የክልሉን ቋንቋ ካልተናገራችሁ መመዝገብና ለምርጫ መወዳደር አትችሉም በመባላቸው ፣ በአገራቸው ለምርጫ የመመዝገብ መብታቸው ተነፈገ።

Saturday, February 21, 2015

ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ

መድረክ 218 ኢዴፓ 127 መቀመጫዎች ብቻ ነው ያሰመዘገቡት
የምዝገባ ጊዜ ሳይጀምር፣ የአንድነት ፓርቲ ከሶማሌ ክልል በስተቀር በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ለፓርላማና ለክልል ምክር ቤቶች ተወዳዳሪዎች አዘጋጅቶ እንደነበረ ይታወቃል። የአንድነት ጥንካሬ ከወዲሁ የተረዳሁ የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ለምርጫ ቢርድ መመሪያ በመስጠት፣ ተለጣፊ ቡድን በማደራጀት አንድነት ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል።

የአንድነት አባላታ ለድርጅት ሳይሆን ለነጻነት የሚታገሉ እንደመሆናቸው ማሊያ ቀይረው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ለመንቀሳቀስ ተነሱ። የሰማያዊውች እና የአንድነቶች መያያዝ ትግሉን የበለጠ አጠናከረው። ሳምንታ ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ አንድነቶ ተነቃነቁ። ወደ ሰማያዎ ጎረፉ። በፊትም ጠንካራ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ አንድነቶች ሲመጡ የበለጠ ተጠናክሮ ከአራት በላይ ለፓርላማ፣ ከሰባት መቶ በላይ ለክልልተወዳዳሪዎች አስመዘገበ። ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ቦርድ የሌላ ፓርቲ አባል ናችሁ በሚል ተሰረዙ።

የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ

ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡

የቃሊቲ እና የቂሊንጦ ጸሐይ ከረር ያለች ብትሆንም በቦታው ደርሰን ወደፖሊሶች ለምዝገባ ተጠጋን፡፡ ጠያቂና ተጠያቂ መዝጋቢ የሆነችው ሴት ፖሊስ ‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?›› ብላ አቤልን ጠየቀችው፡፡ በፍቃዱን እና አጥናፍን መሆንኑ ነገራት፡፡ መዘገበችውና ሂድ አለችው፡፡ ‹‹አንተስ ማንን ነው?›› ስትል ጠየቀችኝ፤ ‹‹አብርሃ ደስታን›› አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝና ‹‹ቆይ፣ ቁጭ በል›› የሚል መልስ መለሰች፡፡ ሌሎች ሰዎችን መመዝገቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሰዓት እየሄደ ነው፣ ችግር አለ ወይ?›› አልኳት፡፡ ‹‹አይ ችግር የለም›› ካለች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሌላ መዝገብ አምጥታ ፓስፖርቴን መዘገበችው፡፡ (መታወቂያዬ አልታደሰም) ከመዘገበች በኋላም ሌላ የፎርም መሙያ አውጥጣ በድጋሚ መዘገበች፡፡ ይሄንን ስትመዘግብ እኔ እንዳይባት ስላልፈለገች ስትደብቀው አስተውያታለሁ፡፡ …ከሌላ ወንድ ፖሊስ ጋር ከተነጋገረች በኋላ ግባ አለችኝ፡፡

ሰበር ዜና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


Friday, February 20, 2015

ለቅሶ በራፍ ፍርድ ቤት ( የልጅና የአባት መተያየት) – ለገሰ ወልደሃና

ዘመነ ምህረት እና መለሰ መንገሻ ከተያዙ አንድ ወር ከአንድ ቀን ሆናቸው በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ የመኢአድ አባላት እና ይህ በፎቶ የምታዩት አንድነት ዘመነ ከእናቱ ጋር ከሰሜን ጎንደር ሌሎችም የዘመነ ቤተሰብም ተገኝተዋል ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ ተካፍሎ ከተመለሰ በኋላ አላገኘነውም አይኑን ለማየት ጉጉተናል የተባለው ሰአት 8:00 ደረሰና ከእሱ ጋር የታሰረው መለሰ መንገሻም አብረው በጋቴና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በፓሊስ ታጅበው ገቡ በእርቀት እጃችን በማወዛወዝ ሰላም አልናቸው እነሱ ባልታሰረው እጃቸው መለሱልን ። በጣም ተጎሳቁለዋል በተለይ መለሰ ግርጥት ብሏል፤ተአምረኛው አንድነት ።

አንድነት የዘመነ የበኩር ልጅ ነው። እድሜውም 3 አመት ከአራት ወር ነው። ሲበዛ ያሳዝናል ። አባቱ ዘመነ፣ ከበርካታ ታሳሪዎች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ሲገባ አባቱን ያየው አንድነት፣ ከእጄ አምልጦ ወደ አባቱ ሮጠ። አባቱን ግን አላገኘም። አባቱን ለማቀፍ የሮጠው ልጅ፣ ከፓሊሱ አልፎ አባቱን ሊያቅፍ አልቻለም። ቀድሞም ይህ ህጻን አይኑ እያየ አባቱን እየደበደቡ የወሰዱት ፓሊሶች ነበሩና የማይጋፋው ጉልበተኛ እንደገጠመው አውቋል።

በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አከባቢ ከባድ ውጊያ ተካሄደ:: ምንሊክ ሳልሳዊ

በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ደቡባዊ አቅጣጫ ቶንጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በታጣቂ ሃይሎች እና በወያኔ ወታደሮች መካከል ለሊቱን ከባድ ውጊያ መደረጉን ለታጣቂ ሃይሎቹ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ከማላካል አስታውቀዋል::

ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ተነስተው በምእራብ የኢትዮጵያ ድንበር ከሚገኙት የወያኔ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙት ታጣቂ ሃይሎች በስርአቱ በደል ደርሶባቸው የሸፈቱ እንደሆነ ምንጮቹ ሲገልጹ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ያካሄዱ ሲሆን ከታጣቂ ሃይሎቹ 26 ሰውች መሰዋቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

በጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስርአቱ ከባድ በደል እየደረሰባቸው ሲሆን ምንም አይነት የልማት መዋቅር ካለመዘርጋቱም በላይ ከየአከባቢያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብት እንዲሁም ከትግራይ መጥተው ለሰፈሩ አልሚዎች ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች እየተሰጣብቸው ለስደት ለስራ አጥነት እና ለድህነት ተዳርገዋል::እነዚህ የስርአቱ በደል አንገሽግሿቸው ደቡብ ሱዳን ጫካ በመግባት ራሳቸውን ያደራጁ ታጣቂ ሃይሎች የወያኔን ወታደሮች መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል::የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነጻነቱ እና ለመብቱ በሚያደርገው ትግል በአንድነት መነሳት አለበት አለበት ያሉት ምንጮቹ ራሳችንን ክበደል እና ከብዝበዛ ለማዳን ጠንክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል::



Thursday, February 19, 2015

የቤተክርስቲያን ነዋየ -ቅድሳት ለዓባይ ግድብ ተብሎ መሰጠቱ ተዘገበ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል።
ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች-በጋራ በመሆን የደብሩ አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ አስደግፈው ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ አስገብተዋል፡፡
የደብሩ ካህናት፣ የተለያዩ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በቤተ ክርስቲያኗ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም ውስጥ፤ የአፄ ምኒልክ የወርቅ ጫማ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የተለያዩ አልባሳት፣ አልጋና በተለያዩ ምክንያቶች ለቤተ ክርስቲያኗ የገቡ በርካታ የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ፣ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችና ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
በማንና በምን ሁኔታ እንደተወሰዱ ባይታወቅም፣ በቱሪስቶች በመጎብኘትም ከፍተኛ ገቢ ሲያስገኙ ከቆዩት ከእነኚህ ቅርሶች መካከል ጥቂት የማይባሉ ቅርሶች መጥፋታቸውን ካህናቱ ተናግረዋል።
የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ መኮንን ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሙዚየሙ ቁልፍ ያዥ ለመምሬ አስፋው ገብረ ማርያም በጻፉት ደብዳቤ ፦ በቅርሶች መመዝገቢያ (መረካከቢያ) ቁጥር 170 ላይ የሚገኙትን ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የአንገት ወርቅ ሐብል ወጪ አድርገው ለሊቀ ህሩያን ቃለጽድቅ ኃይሌ እንዲሰጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተመልክቷል፡፡
ከቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየሙ ወጥተዋል የተባሉት ወርቆች የት እንደደረሱ ባለመታወቁ ካህናቱ፣ ሠራተኞቹና ምዕመናን ግራ ተጋብተው ባለበት ሁኔታ፣ አስተዳዳሪው መልዓከ ጸሀይ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ሠራተኞችን ሰብስበው ለዓባይ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በሙዚየሙ ውስጥ ያሉ ወርቆች መሸጥ እንዳለባቸው ሐሳብ ማቅረባቸውን ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡
‹‹ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሠራም፤›› በማለት የአስተዳዳሪውን ሐሳብ በአንድ ድምጽ መቃወማቸውን የገለጹት ሰራተኞቹ ፣ ደመወዛቸውን በማዋጣት ለህዳሴ ግድብ ቦንድ እንደሚገዙ የተናገሩ ቢሆንም፣ አስተዳዳሪው ግን እንዳስፈራሩዋቸው አስረድተዋል፡፡
ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን፣ ‹‹የተባለው ሁሉ በተለይ ቦንድ የተባለው ጉዳይ ውሸትና ሐሰት ነው፤›› በማለት አስተባብለዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ከወሰነበት ውጪ የተደረገ ነገር እንደሌለም አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡ ጸሐፊው መጋቤ ሐዲስ ዲበኩሉ ገብረዋህድ ግን፣ “ተሰጠ የሚባለው ወርቅ የአንገት ሐብልና የጣት ቀለበት ከምዕመናኑ በስለት የሚገባና ሀገረ ስብከቱ የወሰነበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ጉዳዩን ያውቀዋል የተባለውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን <<ምእመናኑና ካህናቱ ወርቅ ጠፍቷል በሚል ያቀረቡት ተቃውሞ ዝም ተብሎ የሚታይ ሳይሆን መጀመርያ ማጣራት ተገቢ ነው” ብለዋል።
ሀገረ ስብከቱ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባዔ አድርጎ አጣሪ ኮሚቴ መሰየሙን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ፤ ከቅርስ ጥበቃና ባላደራ ባለሥልጣን፣ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት፣ ከሀገረ ስብከቱ ካህናት አስተዳዳሪ መምርያ፣ ከቅርሳ ቅርስና ከክፍለ ከተማው ሀገረ ስብከት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተሰይሞ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብሩ በመገኘትና ኃላፊዎቹ ባሉበት እንደሚያጣራም አስታውቀዋል


የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

Wednesday, February 18, 2015

ሚኒስትሮችንና አፈ-ጉባኤዎችን ጨምሮ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቤተ መንግስት የተገመገሙበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ
በማድረግ ነው።
በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣”ሳሞራን ትፈራዋለህ”ተብለው የተገመገሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣”ኮምፒዩተርና ሞባይል ላይ ጥብቅ ትላለህ” የተባሉት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣”ከባልደረቦችሽ ጋር ትጋጫለሽ”የተባሉት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣”ፈሪ ነህ” የተባሉት ዶፐክተር ካሱ ይላላ፣ “ከደባል ሱስ የጸዳህ አይደለህም”የተባሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፊያን አህመድ እና ሌሎች በርካታ ባለስልጣናት ” ሲ” አግኝተዋል።
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ፣ የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ጸጋይ በርሄ፣ የ አማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዓለምነው መኮንን፣አቶ ስዩም መስፍን፣አቶ አርከበ እቁባይ እና ሌሎች በርካታ ሹመኞች “ቢ” ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
እስካሁን ለ ኢሳት በደረሰው ሰነድ በግምገማው “ኤ”ውጤት የተሰጣቸው የ ኢህአዴግ አመራር የህወሀቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ብቻ ናቸው። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም “በሶሻል ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለራስህ ገፅታ ግንባታ አውለሀል፣ ስራ ታዘገያለህ” የሚሉና ሌሎችም ደከማ ነጥቦች የተነሱባቸው ቢሆንም፤ ከሌሎቹ አመራሮች በተለየ ሁኔታ “የቀረበብኝን ድክመት”አልቀበልም በማለት ነው ውድቅ ያደረጉት። ሌሎቹ አመራሮች በሙሉ፤ ከግምገማቸው በሁዋላ፦ “ድክመታችንን ተቀብለናል፤እናሻሽላለን”
ማለታቸውን ተከትሎ ነው “ቢ” እና “ሲ” የተሰጣቸው። “ሲ”ከተሰጣቸው የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ” ኢህአዴግ ገለልተኛ ነው” እያለ የሚናገርለትን ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት የሚመሩት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ይገኙበታል። በኢህአዴግ ውስጥ ቀደም ሲል አንድን ነገር “ድርጅቱ ነው ያለው” ሲባል፤ “መለስ ነው ያለው”ማለት እንደሆነ የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ገሠሰ “የመለስ ትሩፋቶች” በተሰኘው መጽሐፋቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ኢሳት እጅ የገባው የግምገማ ሰነድ እንደሚያመለክተው፤ የመለስን ቦታ-አቶ በረከት ስምኦን መያዛቸውን ነው።
አቶ ሬድዋን፤”የሀገሪቱን ገጽታ ለውጪ ሚዲያ ዝግ አድርገኸዋል” ተብለው ሲገመገሙ <<ዝግ ያደረኩት እኔ ሳልሆን ድርጅቱ ነው” ብለው መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ <<ድርጅቱ ማን ነው?>>ተብለው በአቶ ሀይለማርያም ሲጠየቅ፦<<በረከት>> በማለት መልሰዋል።


ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

‪‪#‎MinilikSalsawi‬

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡


ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አቤቱታ ላይ ቀጠሮ ሰጠ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘው ክስ መዝገብ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዛሬው ችሎት የተከሳሾቹ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ‹‹ህዳር 12 ለ 13/2007 ዓ.ም አጥቢያ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የተጠርጣሪዎቹ ንብረት ተወስዶባቸዋል፣ የሰብአዊ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል፣ ድንገተኛ ፍተሻው ህገ ወጥ ነው›› በሚል በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ላቀረቡት አቤቱታዎች ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን መልስ ሰምቷል፡፡

Tuesday, February 17, 2015

የተመላሽ ሰራዊት አባላት የቀረበላቸውን የድጋፍ ጥሪ ወድቅ አደረጉት

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኮምቦልቻ ከተማ በቡራሮ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው የተመላሽ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመንግስት ደግፋቸውንና ታማኝነታቸውን እንዲገለጹ በተጠየቁበት ወቅት እስካዘሬ የት እንደወደቅን ሳትጠይቁን፣ አሁን ምን ስለተገኘ ነው በማለት ውድቅ አድርገዋል።
ያለፈው አልፏል ለወደፊቱ እንደጋገፍ በሚል ካድሬዎች የማግባባት ስራ ቢሰሩም ፣ የተመላሽ ሰራዊት አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
አቶ መለስ ጽፈውታል የተባለውን ማንዋል ለማስተማር በሚዘጋጁበት ወቅት ፣ የ ቀድሞ የመከላከያ አባሎቹ በመቃወማቸው ሳይካሄድ ቀርቷል።
መንግስት በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተመላሽ የሰራዊት አባላትን እየጠራ በማነጋገር ላይ ነው


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች በተደረገ የሰንደቅ አላማ መቀየር ምክንያት በርካታ ዜጎች እንደታሰሩ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች በተደረገ የሰንደቅ አላማ መቀየር ምክንያት በርካታ ዜጎች እንደታሰሩ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣

በክልሉ ከማሽ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በክልላችን የሚደረገው የሌሎች ክልሎች ጣልቃገብነት ይቁም ህዝባችን የመረጠው እንጂ ሌሎች ክልሎች የመረጡት መሪ አያስተዳድረንም በማለት አቤቱታና ሰላማዊ ሰልፍ ያቀረቡ ቢሆንም ምንም ሰሚ አካል ባለማግኘታቸው የተነሳ ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ ነጭና ጥቁር መካከሉ ደግሞ ቀይ የV ቅርፅ ያለው ሰንደቅ አላማ ማውለብለባቸውን የገለፀው መረጃው፤ የክልሉ ተወላጂ የሆኑ የቀድሞ ባለስልጣናት የነበሩ በርካታ ዜጎች በመንግስት ፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረድቷል፣

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ኢንቨስተሮች በክልሉ ባጋጠመው ግርግር ምክንያት እለታዊ ስራችንን መስራት አልቻልንም በዚህ ከቀጠለ ለደህንነታችን አስጊ ነውና ባለፈው የምርት ዘመንም ለኪሳራ ተጋልጠናል ሲሉ ከስፍራው እየለቀቁ ኣንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፣


የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡

ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

Monday, February 16, 2015

ኣቶ ገብሩ ኣስራት የምርጫ ካርድ ተከለከሉ..!

ዓረና-መድረክ ወክለው በመቐለ ምርጫ ክልል ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ኣቶ ገብሩ ኣስራት የመራጭነት ካርድ ተጨርሰዋል በሚል ምክንያት ተከልክለዋል።

ይህ የሆነው እሁድ 01 / 06 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 10 ስዓት በመቐለ ኣስራ 15 ቀበሌ እንዳባ ኣነንያ ምርጫ ጣብያ በኣካል ተገኝተው በጠየቁበት ወቅት ነው።

የምርጫ ካርድ በመቐለ ምርጫ ጣብያዎች ከሓሙስ 28 / 05 / 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን ከዚህ ቀን በሗላ የመራጭነት ካርድ ማግኘት ኣልተቻለም።
የትግራይ ምርጫ ፅህፈት ቤት ችግሩ እንዳጋጠመ ያመነ ሲሆን ለችግሩ መፍትሄ ግን ሊያበጅ ኣልቻለው።

ይህ ችግር ያጋጠመው በየምርጫ ጣብያው “ከእቅድ በላይ በመቶዎች ካርድ በመወሰዳቸው መሆኑ” ያስረዳሉ የጣብያዎቹ ሰዎች።
ይህ የህወሓት ወጣትና ሴቶች ሊግ ኣባላት እስከ 3 የመራጭነት ካርድች በተለያዩ ቦታዎች እያውጡ መሆኑ ታውቋል።

የህወሓት መንግስት የትግራይ ሰዎች A.B.C.D ብሎ በመመደብ ካርዱ ለ A.B ቅድምያ በመስጠት እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ C ለተሰጣቸው ሰዎች ካርዱ ይሰጣቸዋል።
የተመደበው ዜጋ የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ካርድ እንዳይ ደርቸው እየተደረገ ነው።

በዚህ ለሚመርጥህ ሰው ለይተህ ካርድ በመስጠትና ለታማኝ የሊግ ኣባላት ከ3 በላይ ካርድ በማደል ከወዲሁ የምርጫው ውጤት ለመወሰን ጥረት እየተደረገ ነው ያለው።
ማንኛውም ሰው በኣቅራብያው ያለው የምርጫ ጣብያ ጠይቆ ካርድ መኖሩ ኣለመነሩ ማረጋግጥ ይችላል።
ይህ ማጭበርበርያ ዘዴ ለማውጣት የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የትግራይ ህዝብ እንደማይመርጣቸው በማረጋገጣቸው ነው።

ኣሁንም ምርጫ ቦርድ የመራጭነት ካርድ እንዲልክና የህዝቡን ፍላጎት እንዲያከብር እንመክራለን።

ኣቶ ገብሩ ኣስርትም የመራጭነት ካርድ ሊሰጣቸው ይገባል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!


Gagging the media in Ethiopia – MWC News

Nobody trusts politicians, but some governments are more despicable than others. The brutal gang ruling Ethiopia is especially nasty. They claim to govern in a democratic pluralistic manner, they say they observe human rights and the rule of law, that the judiciary is independent, the media open and free and public assembly permitted as laid out in the constitution. But the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) systematically violates fundamental human rights, silence all dissenting voices and rules the country in a suppressive violent fashion, that is causing untold suffering to millions of people throughout the country.

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፓርቲው ከትግራይ፣ እስከ ሞያሌ ጫፍ ዕጩ ማቅረቡ ለገዥው ፓርቲ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኖበታል ያሉት ኢ/ር ይልቃል በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረጉት ጫናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ሰይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ 23 ዕጩዎችን አቅርበናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ሳይቀር በሚዲያ ሲነገርላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት በቴሊቪዥን ቀርበው ‹ሰማያዊ በተደጋጋሚ ብንነግረው አልሰማም፣ በመሆኑም ሰኞ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል› ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰማያዊ በምርጫው እንዳይሳተፍ ችግር መፍጠር እንደሚፈልጉ ነው፡፡›› ሲሉ ፓርቲው ላይ እየተፈጠረበት ያለውን ጫና ገልጸዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በዛሬው ዕለት በኢቢሲ ቀርበው ሰማያዊ ይቅርታ ባለመጠየቁና ማስጠንቀቂያዎችን ባለመቀበሉ ነገ ሰኞ ጥር 9/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያስተላልፋል ብለዋል፡፡ ከሌሎች ፓርቲዎች ሰማያዊን በመቀላቀል በፓርቲው ምልክት ለመወዳደር የወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ መደረጉና በሌሎች ዕጩዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡


Sunday, February 15, 2015

ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው

ናትናኤል መኮንን

ከተመሰረተ 40 አመት ሊያስቆጥር ቀናት የቀረውና አሁንም በገንጣይነት ተግባሩ የቀጠለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከወሎ ተጨማሪ መሬት ለመከለል ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ ለደሴ ሆስፒታል ባዛር በተደረገበት ወቅት ህወሓት አገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች በባዛሩ እንዲገኙ ያደረገ ሲሆን በወቅቱም ወሎ ውስጥ ሰፊ መሬት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ በተለይም ከቆቦ ወደ ወልደያ በኩል 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አላውሃ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥም ‹‹የትግራይ ድንበር አላውሃ ምላሽ ነው›› በሚል እያስወራ እንደሚገኝ የአካባቢው ነ…ዋሪዎች ገልጸዋል፡፡አላውሃን ጨምሮ ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ አርሶ አደሮቹን እያፈናቀሉ ለህወሓት ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ለመስጠት ሰፊ እቅድ እንደተያዘና በሂደት በአካባቢው በርከት ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች እንዲኖሩ በማድረግ ቦታውን ወደ ትግራይ ለመከለል ሴራ እየተሸረበእንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል፡፡የቆቦና ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሰጥተው የአካባቢው ተወላጆቹ መሬት አልባ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህም ተከትሎ ሰሞኑን ወሎ ውስጥ ተጨማሪ መሬቶች ወደ ትግራይ ሊከለሉ ነው በሚል ህዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሯል፡፡ ህወሓት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የጎንደርና የወሎ መሬቶችን ወደ ትግራይ መከለሉ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በስፋት የጀመረው መሬትን ለትግራይ ባለሀብቶች የመስጠት እቅድም ወደፊትም ሰፋፊ መሬቶችን ወደ ትግራይ ሊከልል እንደሚችል አመላክቷል፡፡


በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ለሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች መታወቂያ እድሳት ያደረገው የሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ማህተምና ሌሎች ዶክሜንቶችን እንዲያስረክብ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡

በደቡብ ወሎ የቃሉ ወረዳ የክልልና የፌደራል እጩዎች ለምርጫ ቦርድ ማስረጃቸውን ሊያስገቡና ለማሳወቅ ወደምርጫ ቦርድ በሄዱበት ወቅት የመታወቂያ እድሳት እንደሚያስፈልጋቸው በተገለፀላቸው መሰረት ወደሚኖሩበት ሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ በመሄድ መታወቂያቸውን አሳድሰው ይመለሳሉ፡፡ ይህ በተደረገ በሁለተኛው ቀን መታወቂያውን ያደሰውን ቴድሮስ የተባለ የቀበሌው ስራ አስኪያጅ በቀበሌው ካድሬዎች ተጠርቶ ‹‹መታወቂያ ለተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች አድሰሀል፤ …..አንተ ባታድስላቸው ኖሮ እጩ ማሳወቂያው ቀን ሊጠናቀቅ የቀረው አንድ ቀን በመሆኑ ላይመዘገቡ ይችሉ ነበር፤ …..ስለዚህ ተቃዋሚዎችን በመርዳትህና በመተባበርህ፤ በቀጣይነትም በሀላፊነት ለመስራት እምነት ስለማይጣልብህ ማህተምና ሌሎች ሰነዶችን ባስቸኳይእንድታስረክብ ›› መባሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህን ተከትሎ እርምጃው የተወሰደበት ስራ አስኪያጅ ‹‹ ግለሰቦቹ መታወቂያ የማግኘት የዜግነት መብት አላቸው፤ ከአሁን በፊት ደግሞ የሰጣችኋቸውን ነው ያደስኩት፤ …..ይህ እኔን ሊያስጠይቀኝ የሚገባ ድርጊት አይደለም፤ህግን አክብሬ ነው የሰራሁት›› ሲል የተከራከራቸው ቢሆንም፤ ካድሬዎች አሻፈረኝ ብለዋል፡፡ ካድሬዎች በቃል የሰጡትን ምክንያት ግን በፅሁፉ ላይ ሳያሰፍሩ ለግለሰቡ በፅሁፍ በደረሰው ማስጠንቀቂያ ላይ ‹‹ …..ሀላፊነትህን በሚገባ ለመወጣት ባለመቻልህ፤ማህተምና ሌሎች በእጅህ የሚገኙ መረጃዎችን እንድታስረክብ፤……›› የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ይህም ካድሬዎች ለሽፋንነት የተጠቀሙበት ሴራ መሆኑን የእርምጃው ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ በመሆኑ ብቻ መረዳት ይቻላል፡፡ ግለሰቡ በአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ በሰራተኛው ዘንድ ተወዳጅና ህግን አክብሮ የሚሰራ መሆኑን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በመስሪያ ቤት በኩልም ምንም አይነት የፅሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት የማያውቅ ምስጉን ሰራተኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑ፤ ስራ አስኪያጁ እስካሁን ድረስ…… ‹‹ማህተምም ሆነ ምንም ነገር አላስረክብም፤በህግ የሚጠይቀኝ አካል ካለ ይጠይቀኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን እኔ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት አደርሰዋለሁ›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ለግለሰቡ የተሰጠው የፅሁፍ ማስረጃ በእጃችን እንደገባ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡


Friday, February 13, 2015

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ  የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

በትግራይ ቀንደኛ የህወሃት ካድሬ ተገደለ

መረጃ ለነፃነት

ኮረም ከተማ ውስጥ ህዝቡን እያሰቃየ የቆየው አንድ የስርዓቱ ካድሬ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ማደሩን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።

ከተማው ውስጥ የሚገኙ ምንጮች አንደ ገለፁት በትግራይ ደቡባዊ ዞን የኮሮም ከተማ ነዋሪ የሆነው የዋግነህ በለጠ የተባለው ካድሬ ጥር 21/2007 ዓ/ም ሌሊት ላይ ከኮረም ወደ አላማጣ በሚወስዶው መንገድ ላይ በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፎ ማደሩ ታውቋል።

የሞተው ሚልሻ የስርዓቱ ዋንኛ ታማኝ እንደነበረና ህዝቡን እያሰቃየ መቆየቱን የገለፀው መረጃው የአካባቢው ተወላጆች የበቀል እርምጃ እነደሚወስዱበት እየዛቱ መቆየታቸው ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊት ሚልሻው ሞቶ ባገኙበት ሰዓት እስከሬኑን ለምርመራ መቐለ ድረስ መውሰዳቸውና በተጨማሪም የከተማው ፖሊስ ከሟቹ ጠብ ነበራቸው ያላቸውን ንፁሃን ወገኖች በጥርጣሬ እያሰሯቸው መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።


ለሳምንታት ክትትል ሲደረግባቸው የነበረው መምህር ጥጋቡ ሃብቴ ታፍነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የጎንደር ሰብሳቢና የመኢአድ መስራች የሆኑት መምህር ጥጋቡ ሃብቴ ለሳምንታት ማስፈራሪያ ሲደርሳቸውና ክትትል ሲደረግባቸው ከቆዩ በሁዋላ የካቲት 4/2007 ዓም ደህነቶች ሌሊት ወደ ቤታቸው በመግባት ፍተሻ ካካሄዱ በሁዋላ ወደ አልታወቀ ቦታ አፍነው ወስደዋቸዋል።
የቀድሞው የመኢአድ አዲስ አበባ ህዝብ ግንኑነት ሃለፊ አቶ አወቀ አባተ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ መምህር ጥጋቡ የጎንደሩን ጽ/ቤት ለአዲሱ መኢአድ እንዲያስረክቡ ቢታዘዙም፣ አላስረክብም ብለው እንደነበርና ከራሳቸው ጽ/ቤት እንደሚታሰሩ ተነግሯቸው ነበር።
የመምህር ጥጋቡ ባለቤት ” ባለቤታቸው ታፍነው መወሰዳቸውን በመቃወም ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ “ለምርመራ ይፈለጋል” የሚል መልስ ከማግኘት ውጭ ሌላ የተነገራቸው አሳማኝ ምክንያት የለም።
አቶ አወቀ እንደገለጹት መምህር ጥጋቡ የታሰሩበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት ቢደረግም እስካሁን አልተሳካም።
በሌላ በኩል ደግሞ የአንድነትፓርቲምክትልአፈጉባኤየነበሩትናበቅርቡየሰማያዊፓርቲንየተቀላቀሉትአቶጸጋዬአላምረውመሰደዳቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

Thursday, February 12, 2015

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ካድሬዎች ፣የደህንነት ሰዎች እና የመከላከያ አባላት፤አዲስአበባ የተለያዩ አካባቢዎች እየዞሩ፦‹‹ለህወሓት በዓል ማክበሪያ ገንዘብ አዋጡ›› በማለት እየቀሰቀሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የካቲት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሀት 40ኛ ዓመት የፊታችን የካቲት 11 የሚከበርሲሆን፤ ለበዓሉ ማክበሪያ በግዳጅና በጫና ከባለሀብቶች ብቻ 45 ሚሊዮን ብር እንደተገኘ መመዘገባችን ይታወሳል።
ህወሀት ከመንግስት ካዝና የሚጨምረውን ሳያካትት ለአንድ ጊዜ በዓል ማክበሪያ ብቻ ይህን ያህል ብር የሰበሰበ ቢሆንም፤ ከነዋሪዎች ተጨማሪ ገንዘብ ለማሰባሰብበ ካድሬዎች አማካይነት ቅስቀሳ መጀመሩን የአዲስአበባው ዘጋቢያችን ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል።
ከዚህ ባሻገር በአዲስአበባ፣ መቀሌ እና በየክልሎቹ የሚደረገው የበዓል ዝግጅት ላይ ካድሬዎች ደምቀው እንዲገኙ የልብስ መግዣ ገንዘብ እየተሰጣቸው እንደሆነ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ለሴቶች የሀበሻ ቀሚስ መግዣ 4 ሺህ ብር ፣ ለወንዶች ደግሞ ለቁምጣና ለሌሎች ባህላዊ አልባሳት ተብሎ 2 ሺህ ብር እየተሰጠ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።


ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ክስ ቀረበበት • በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

(ነገረ ኢትዮጵያ) ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው …በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚፈልግባቸው ጊዜያት የቀበሌ ካድሬዎች አከራዮቹና ደላሎቹ ለፓርቲው እንዳያከራዩ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ሲሆን በተለይ በጥር ወር 2007 ዓ.ም ይህ ጽ/ቤት እንዳይከራይ ግፊት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ

የአንድነት ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑትና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀሉት አቶ ጸጋዬ አላምረው፣ ከወያኔ የፀረ-ሽብር ግብረ ኅይል እንዲታሰሩ የማዘዣ ወረቀት በመዉጣቱ፣ ለተወሰነ ቀናት አገር ቤት ራሳቸውን ሰዉረውከቆዩ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ጸጋዬ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከታሰሩ በኋላ የመኢአድ አመቻች ኮሚቴ ዋሃ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።፣ ሕወሃቶች መሰናክል ፈጠርበት እንጂ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ ጫፍፍ እንዲደርስ፣ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ የአመራር አባላት መካከል አንዱ ነበሩ። የአንድነት ፓርቲ ያደርግ በነበረው የምርጫ ዘመቻም፣ የምርጫ ኮሚቴ አባል በመሆን ትልቅድርጅታዊ ሥራ ይሰሩም ነበር።

World Bank and the International Monetary Fund showed that Ethiopia had lost 11.7 billion dollars in illegal financial out flow between 2000 and 2009

By Lucy Kassa

African Union’s (AU) high level panel on illicit financial flows (IFF) from Africa ranked Ethiopia ninth from the top 10 African countries with high illicit financial flows from 1970 to 2008 next to Côte d’Ivoire and Sudan.

The panel, which was chaired by Thabo Mbeki, former South African president and comprised nine other members, released its report at Hilton Hotel on February 1, 2015.

The high level panel is the first African initiative mandated to be established after the fourth joint annual meeting of the AU/ECA conference of ministers of finance, planning and economic development adopted a resolution to establish the level of IFF from the continent, to asses its long term impacts and to propose policies in reversing the illegal outflows.

Wednesday, February 11, 2015

በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ

በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ዘገበ::

እንደ ኢሳት ዘገባ ከሆነ ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል።

ማንነታቸው ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው በመሄድ፣ አቶ ተሙሻን አሸባሪዎችን አስጠግተህ ትቀልባለህ ብለው በጥይት እንደመቱዋቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሆ ብለው ሲወጡ፣ በመጡበት መኪና ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አሸባሪ የተባሉት ሃይሎች እንማን እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ነዋሪዎች ግን ምናልባትም ለምርጫ ቅስቀሳ የመጡ የተቃዋሚ አባላትን ሊሆን ይችላል ይላሉ። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።


Tuesday, February 10, 2015

አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ የሃሰት ዲግሪዎችን ሸምተው መጠቀማቸው ተረጋገጠ

(አዲስ ቮይስ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ በኢንተርኔት ያለምንም ትምህርት ዲግሪ በመሸጥ ከሚታወቅ አንድ የዲፕሎማ ወፍጮ ቤት (diploma mill) የሃሰት ዲግሪዎችን ገዝተው መጠቀማቸውን አዲስ ቮይስ አረጋገጠ።

አፈጉባኤው የባችለርስ ዲግሪ እ.ኤ.ኤ በ2001 እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪ በ2004 አሜሪካን አገር በሚኖረውና አሊ ሚርዛኢ በሚባል ኢራናዊ ከሚንቀሳቀሰው “አሜሪካን ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ” (ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ) ያለምንም ትምህርት መግዛታቸው በመረጃ ተረጋግጧል። አባዱላ ሁለቱንም ዲግሪዎች የህዝብ አስተዳደር ትምህርት ተምረው አንዳገኟቸው ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን ይህንንም በፓርላማ ድረገጽ፣በፌስቡክ፣ ዊኪፔድያ፣ በመንግስትና በግል የመገናኛ ተቋማት በይፋ ታትሞ እንዲሰራጭ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቻይና መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የባችለርስ ዲግሪ እንዳገኙ በህይወት ታሪካቸው ላይ በይፋ ያሰፈሩ አባዱላ እንዲህ አይነት ዲግሪም ይሁን ትምህርት ከቻይና የትምህርት ተቋም አለማግኘታቸው ታውቋል።

ጓዶች ሆይ፦ ምርጫውን እርሱት! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ -ዝዋይ እስር ቤት )

(መልዕክት-አብዬታዊያን)

ተመስገን ደሳለኝ

ከዝዋይ እስር ቤት



“ባለወር ተተካ

ተቀበለኝ ትግሌን እንካ”

(ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን)



…ሲያሻው እየጋመ፤ ሲያሻው እንደበረዶ እየቀዘቀዘ በመካሄድ ላይ ያለው የፀረ-ጭቆና ትግል እንደዋዛ ግማሽ ክፍለ ዘመን አስቆጠረ፡፡ የሂደቱ ክፉ ጎን ደግሞ የአያሌ ብርቱ ወንድም-እህቶቻችንን የህይወት ግብር እየጠየቀ ዛሬ ድረስ ተጉዟል፡፡ በተለይም ሁለቱ ቀደምት አብዮቶች (የ1966ቱ እና የ1983ቱ) ብረት-ነከስ ናቸውና የትውልድ ክፍተት እስከመፍጠር የደረሰ ዕልቂት ስለመሸከማቸው በደም የተፃፉት ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ከመዓቱ የተረፉት የዓይን እማኞችም ለወቅቱ መከራ ምስክሮች ናቸው፡፡ እነዚህ አብዮቶች፣ አነሰም በዛም፣ የየራሳቸውን በጎ አበርክቶ ትተውልን ማለፋቸው ባይካድም፤ የተከፈለው መራራ ዋጋ ግን ለውጤታቸው በዝቶባቸዋል፡፡ ህይወት የተማገደላቸው እኒህ የለውጥ ንቅናቄዎች፣ የተነሱለትን ምክኒያት የዘነጉ ዋጋ-ቢስ አገዛዞችን በማዋለድ ተጠናቀዋል፡፡ እኔና የትውልድ ተጋሪዎቼም ቀሪውን የለውጥ ጥያቄ በድል ለማጀብ የቀለም አብዮትን ወደ መምረጡ ጠርዝ የመጣንበት መግፍኤ ይኅው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ወያኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት ለጠየቁ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትን ፈቃድ ከለከለ::

የወያኔ ባለስልጣናት የእንግሊዝ የፓርላማ ቡድን ልኡካን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንዳይጎበኙ ፈቃድ መከልከላቸውን ከሎንዶን ተሰማ::አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከየመን ሰንአ አየር መንገድ ታፍነው በአዲስ አበባ የተለያዩ የማሰቃያ ቦታዎች ከፍተኛ ቶርች ሲፈጸምባቸው ቆይቶ በዚህ ሳምንት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንደተዘዋወሩ ተጠቁሞ ነበር::

በጀርሚ ኮርቢን የሚመራው የእንግሊዝ የፓርላማ ቡድን ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ አቶ አንዳርጋቸው የሚለቀቅበትን ጉዳይ ለመነጋገር እቅድ አድርገው የነበረ ቢሆንም በእንግሊዝ የወያኔ ኤምባሲ አምባሳደር ብርሃኑ ከበደ ከሎንዶን ከልኡኩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ጉዞው እንደተሰረዘ ታውቋል::

ወደ አዲስ አበባ ሄደን አንዲን ለመጎብኘት በሚቀጥለው ሳምንት ያሰብነው ጉዞ በባለስልጣናት እውቅናና ፍቃድ ባለማግኘቱ ልንሰርዘው ተገደናል ሲሉ የልኡኩ መሪ ተናግረዋል::ሎርድ ዶላኪያ በእንግሊዝ ፓርላማ የፓርቲዎች ሕብረት የኢትዮጵያ ጉዳይ ምክትል ሊቀመንበር ከሚስተር ኮርቢን ጋር ሊያደርጉት ያሰቡት ጉዞን አስመልክቶ አለመፈቀዱን ተቃውመውት ግልጽ የሆነ ሂደት እንዲኖር የጠየቁ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ጠበቃ ክሊቭ ስታፎርድ ስሚዝ አንዳርጋቸውን እንዲጎበኙ እንዲፈቀድ አጥብቀው የጠየኡ ሲሆን በዚህ ሳምንት ጉዳዩን በፓርላማ እንደሚያነሱት ገልጸዋል::

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉብኝት ይመለከታል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአብራኬ የወጣ ሁለተኛ ልጄ ነው፡፡ ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለሰው አሣቢ፣ ሀገር ወዳድና ታታሪ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡ ልጄ ተመስገን ለወገኔ አሰብኩ ባለ በእስር ቤት ያለጎብኚ እየተሰቃየብኝ ይገኛል፡፡ መቼም፣ የእናት ሆድ አያስችልምና እባካችሁ ልጄን ታደጉት፡፡ እባካችሁ ቢያንስ ካለበት እየሄድኩ የልጄን አይን እንዳይ እንዲፈቀድልኝ ተባበሩኝ፡፡ የልጄን ድምጽ ከሠማሁ ይኸዉ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለወንድሙ ብሎ የቋጠረዉን ምሣ ይዞ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢሄድም በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድቦ የያዘውን ምግብ እንኳ ሣያደርስ ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል፡፡ መቼም እናንተም ልጆች ይኖራችኋል፤ ደግሞም የልጅን ነገር ታውቁታላችሁ፡፡ እኔ አሁን በእርጅና ዕድሜዬ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ብቆይም ለትንሽ ጊዜያት ነው፡፡ በዚህች ጊዜ ውስጥ ልጄን እየተመላለስኩ እየጠየኩ፣ ድምፁን እያሰማሁ፣ አይዞህ እያልኩ ብኖር ለእኔ መታደል ነበር፡፡ እባካችሁ እርዱኝ የልጄ ድምጽ ናፈቀኝ፡፡ እሱን መጎብኘት የተከለከለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንኳን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ከወንድሙ ድብደባ በኋላም ጥር 10 ወደ ጠዋት አካባቢ የሄዱት ጓደኞቹ እና ወንድሞቹ ሳያዩት ተመልሰዋል፡፡

Sunday, February 8, 2015

ሰበር ዜና- ህገ ወጥ የመሬት ቅርምት በእንጦጦ መ/ስብሀት ቅ/ስላሴ ቤተ ክርስቲያን !

የእንጦጦ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ንብረትነት በካርታና ፕላን ውስጥ ያላዉ ቦታ በህገ ወጥ መንገድ እየተቸበቸበ መሆኑን ምእመናን ገለጹ!! ምእመናኑ ህገ ወጥ የመሬት ቅርምቱን ሁሉም አውቆት እንዲያስቆመዉ ሁሉም ክርስቲያኖችና ኢትዮጵያዉያን መረባረብ እንዳለባቸዉ አስታውቀዋል፡፡ ዛሬ ከወደ ጠዋት አከባቢ በቤተ ክርስቲያኑ ከሚገለገል ምዕመን የደረሰኝን ጦማር እንዳለ እንደሚከተለዉ አቅርቤዋለሁ፡፡

‹‹በአዲስ አበባ ከተማ በተለየ ስሙና ቦታው እንጦጦ የሚገኝ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ውስጥ እተፈጸመ ያለ አስገራሚና በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና አማኝ ሊፈጸም የማይገባ ተግባር ስለተመለከትኩ ፍርዱን ለአንድ አምላክ በመተው እኔ ግን እንደ አንድ ምእመን ያየሁትንና የሰማሁትን ለእናንተ በማካፈል እውነታው ምን ይመስላል የሚለውን ከሚዛን እንድታደርሱ አደራውን ሰጠሁ በቅርቡ የተመረጡት የሰበካ ጉባዔ አባላት በቤተክርስትያን ስም ሁለት ማህተም በማሰራት የቤተክርስትያኑ ንብረት የሆነውን ቦታ በማጭበርበር እየሸጡት ነው፡፡ የቤተክርስትያኑ ሰንበቴ ቤት የነበረውን ክፍት ቦታ ለቤተክርስትያኑ ገቢ ማስገኛ በማለት ለግለሰብ ቢያከራዩትም ሰነዱን በማጥፋት ካርታ አስወጥተው እንደሸጡት ታውቋል አሁን ደግሞ የማቴዎስ ግቢ የሚለባለውን የቤተክርስትያኑን ቦታ አገልጋይ ካህናትን በማስወጣት ለግለሰብ ለ20 ዓመት ሊሸጡት እየተደራደሩ ነው ይህንንም ለማሳመን ሁለት ዓይነት የተጭበረበረ ሰነድ አቅርበዋል ስለዚህ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን የቤተክርስትያን ቦታ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር በህግ አምላክ ብለን እናስቁማቸው::


በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።

ምንሊክ ሳልሳዊ

ወያኔ ራሱን ለማንገስ ከሚጠራው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ጦርነት ሊካሄድ ይችላል ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።በተለያዩ አጋጣሚዎች የተነሱ የሳተላይት ፍቶዎች በማስረጃነት በመጥቀስ ይህን ሰሞን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአፍሪካ ህብረት ሰዎች እና ከአከባቢው የፖለቲካ አዋቂዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያካሂዱት ዋናው የዚሁ ጦርነት ስጋትና አከባቢው ላይ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን በመገምገም ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካ መንግስት የሲአይኤን ሪፖርት ተከትሎ በትራንስፖርት ቢሮአቸው አማካኝነት በሰሜ

ለወያኔ ዉንብድና መልሱ ህዝባዊ እምቢተኝነትና ህዝባዊ አመጽ ነዉ!

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎ የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ጨብጠዉ በኖሩባቸዉ ባለፉት ሃያ አራት አመታት የአገራችን የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ በጣም ከዘቀጠና ከረከሰ የወያኔ ድራማ ዉጭ ሌላ ምንም ነገር የማይታይበት አለባሌ መድረክ አድረገዉት ቆይተዋል አሁንም እያደረጉት ነዉ። አንድ ቋንቋ የሚናገሩትና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸዉ የወያኔ መሪዎች ኢህአዴግ የሚባል አጋሰስ የሽፋን ድርጅት ፈጥረዉ በኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊ መብትና ነጻነትና ላይ ተነግሮም ተጽፎም የማያልቅ ግዙፍ ግፍና በደል ፈጽመዋል። ህጻን፤አዛዉንት፤ ወንድና ሴት ሳይለዩ መብቴን አትንኩ ያለቸዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለምንም ርህራሄ በጥይት ጨፍጭፈዋል። ሴቶች እሀቶቻችንን እጅና እግራቸዉን አስረዉ ጡታቸዉን በመቆንጠጫ እየቆነጠጡ በሴትነታቸዉ ላይ የዉርደት ተግባር ፈጽመዋል። ወንዶች ወንድሞቻችንን ደግሞ ዉስጥ እግራቸዉን ገልብጠዉ እየገረፉ ጥፍራቸዉን አይናቸዉ እያየ በጉጠት እየሳቡ ነቅለዋል። ባጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች በዛሬዉ ዘመን አንኳን ወገን በወገኑ ላይ የዉጭ ጠላትም በህዝብ ላይ የማይፈጽመዉ በደል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፍጽመዋል።

Friday, February 6, 2015

5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላትና 2 ፓይለቶች ጠፉ!!

ጥር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት ሳምንት በፊት 5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንዲሁም 2 ፓይለቶች ከድሬዳዋ አየር ሃይል ጠፍተዋል። የጥበቃ አባላቱም ሆነ ፓይለቶቹ ያሉበትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ይህንን ተከትሎ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከመቶ አለቃ ማእረግ በላይ ያላቸውን አየር ሃይል አባላት ሰብስበው ግምገማ አካሂደው ነበር።
ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።
የአየር ሃይል አባላት ሞራል ( ስሜት) መዳከም ገዢው ፓርቲ በሩሲያ ቅጥር አብራሪዎች ላይ እምነቱን እንዲጥል አድርጎታል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ እና ቴክኒሻን ብርሃን ግደይ ከመቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ጋር በመሆን ስርአቱን አናገለግልም ብለው ሄሊኮፕተር ይዘው መጥፋታቸው፣ የህወሃትን የዘር ፖለቲካ መሰረት እንዳናጋው ምንጮች ይገልጻሉ። ለወትሮው ይታመኑ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የአየር ሃይል አባላት ሳይቀሩ የሚታመኑ ሆነው ባለመገኘታቸው፣ባለስልጣናቱ አይናቸውን የውጭ ቅጥረኞች ላይ እያዞሩ ነው።
ስርዓቱን አናገለግልም ብለው የጠፉት የአየር ሃይል አባላት የተቃዋሚ ድርጅቶችን ተቀላቅለው እየታገሉ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአፍሪካ መሪዎችም ሆነ የሌሎች አገራት መንግስታት ለስብሰባ ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ጊዜ ለደህንነት ስራም ሆነ ለልዩ ጥበቃ የሚመደቡት የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው በማለት የሌሎች ክልሎች የደህንነት አባላት ቅሬታ ማሰማታቸው ታውቋል።
የ24ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ከተካሄደ በሁዋላ ለግምገማ ከተጠሩት ምድብተኛ የደህንነት ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት መካከል አንዳንዶች፣ ” ለመሪዎችና ለእንግዶች ደህንነት የሚመደቡት ጠባቂዎች የአንድ አካባቢ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው፣ “ስርአቱ የእናንተ አይደለም፣ አናምናችሁም” የሚል መልክት አለው በማለት በድፍረት ለገምጋሚዎች ተናግረዋል።

“በብሄራችን ምክንያት ተበድለናል” ያሉት የደህንነት ሰራተኞችና ጠባቂዎች፣ ደረሱብን ያሉዋቸውን በርካታ ችግሮች ዘርዝረው አቅረበዋል። ” በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪዎች ራሳቸውን እያደራጁና መረባቸውን እየዘረጉ በመጡበት ሁኔታ የምናምነውን ሰው እንመድባለን” የሚል መልስ ግምገማውን ከሚመሩ መሪዎች የተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በተሰጠው መልስ ማዘናቸውን በግምገማው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።


Thursday, February 5, 2015

መንግስት በፌስ ቡክና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰማራቸው ሰዎች የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አልቻሉም ተባለ።

ጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማህበራዊ ድረገጾች ላይ የመንግስትን መልካም ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊደርጉ ይችላሉ በሚል ተከታታይ ስልጠና ተሰጥቷቸው የነበሩት የህዝብ ግንኑነት ባለሙያዎች (ኮምኒኬተሮች) እና የመንግስት ባለስልጣናት፤የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልቻሉም መባላቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖ ጠቆሙ፡፡
ለመንግስት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችና ለካድሬዎች በአቶ ሬድዋን ሁሴን በሚመራው የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት አማካይነት ከአራት ወር በፊት በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀምና በመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ተከታታይ ስልጠና መሰጠቱ ይታወቃል።

ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑን የሚዳኙት የመሐል ዳኛ በራሳቸው ፈቃድ ከችሎቱ ራሳቸውን አገለሉ

#‎Miniliksalsawi‬
ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ለ የካቲት 11 ተቀጠሩ፡፡ በ26/05/2007 ዓ.ም. የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ ይቀየሩልን ሲሉ በፅሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ የግራና የቀኝ ደኛው ውድቅ ሲያደርጉት የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ በራሴ ፈቃድ ከችሎቱ እራሴን አንስቻለሁ ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ታዳሚ ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ሰባተኛ ተከሳሽ ጦማሪ አቤል ዋቤላ ትላንት ከፍርድ ቤት ወደ ማረሚያ ቤት በሚመለስበት ወቅት እጅህ በካቴና ለምን አልታሰረም ብለው የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች እጄን በውሻ ሰንሰለት አስረው አሳድረውኛል ብሎም ዛቻና ዘለፋ ደርሶብኛል እንደዲሁም ማአከላዊ ታስሬ እያለሁ በደረሰብኝ ድብደባ ጀሮዬ ላይ ጉዳት ስለደረሰ ለማደዳመጥ ጀሮዌ ላይ የማረገውን ድምፅ ማዳመጫ መሣሪያ በማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ተነጥቂያለሁ ሲል እንባ በተናነቀው ንግግር ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ለምን ይህ እንደተደረገ እና ያደረገውን ሰው በፅሁፍ እንዲያቀርብ ለየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲያቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ሦስቱ ጋዜጠኞች እና ስድስቱ ጦማሪያን ደኛው ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ አግባብ አይደለም ያለው ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 2519 መሠረት የ500 ብር ቅጣት ይቀጡ የነበረው በስሜታዊነት ነው በማለት መቀጫውን ውድቅ አድርጓል፡፡ በየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃል በአዲስ የመሀል ዳኛ መሠረት ይሰማል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡


የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

ህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ መጠን እና ባካሄደው የግለሰብ ንብረቶች ዝርፊያ የሥርዓቱ ባህርይ ፈጽሞ ከሰውኛ ተፈጥሮ እየወጣ እንደሆነ አመላካች ነው። በእነዚህ ድብደባዎች ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል። በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት የተደረገው በደብዳቢዎቹ የግል ውሳኔ ሳይሆን ከበላዮቻቸው በተሰጠ ትዕዛዝ ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል።

በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መከረ

ጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህብረቱ ጥር 27፣2007 ዓም በብራሰልስ ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ውስጥ ለ3 ሰአታት ባደረገው የኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ግምገማ በኦጋዴን ክልል እና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታት በዝምታ መመልከታቸውን ማብቃት አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ስብሰባውን ያዘጋጁት የህብረቱ የሶሻሊስትና የዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ጥምር ህብረት ፣ ውክልና አልባ ህዝቦች ተቆርቋሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።
በስብሰባው ላይ የኦጋዴን ክልል ፕ/ት አማካሪ የነበረና በክልሉ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመረጃ በማጋለጥ ላይ የሚገኘው ወጣት አብዱላሂ ሃሰን፣ ተቀማጭነቱ በጄኔቫ የሆነ የአፍሪካ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባልደረባ፣ አቶ አብዱላሂ ሙሃመድ፣ የኦጋዴን ሴቶች ተወካይ ፣ ጋዜጠኛና የክሬት ትረስ ዳይሬክተር ግርሃም ፌብልስ፣ እንዲሁም በኦሮሞ ሴቶች ላይ የሚደረሰውን ሰቆቃ በማስመልከት ጥናት ያካሄዱት፣ ዶ/ርባሮ ቀኖ በቪዲዮ የተደገፈ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
እንግሊዛዊው ግራሃም ፌብልስ በኢትዮጵያ 2 አመታት ቆይታቸው የታዘቡትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በኦጋዴን ክልል በሴቶች ላይ ተፈጽሟል ያሉትን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የታዳሚውን ስሜት በነካ መልኩ አቅርበዋል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎች ላይ ሽብርን እያኬደ ነው ያሉት ሚ/ር ፌብልስ የዚህ ሶቆቃ ፈጻሚዎች፣ ከአውሮፓ ህበረትና መንግስታት በእያመቱ ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙ መሆናቸው እጅግ የሚያሳዝነው ነው ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ተወካይ ዶ/ር ባዳል አህመድ እና አርበኞች ግንቦት7 ተወካይ አቶ አበበ ቦጋለ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ነው የሚሉትን የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች እረገጣና አስከፊ ሰቆቃ በእየተራ አቅርበዋል።
የአውሮፓ ህብረትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና ጎሜዝና የእንግሊዝ የፓርላማ ተወካይ ወ/ሮ ጁሊ ዋርድ በየተራ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ከ60 በመቶ በላይ በጀቱን ከአውሮፓ ህበረት እየተቀበለ ዜጎች ላይ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ ሰቆቃዎችን አውሮፓ ካሁን በሁዋላ በዝምታ ማየት የለባትም ካሉ በሁዋላ፣ ኢትዮጵያኖች በአገራቸው እየተፈጸመ ያለውን አፈናና ጭቆና የውች ማህበረሰብ ያስቆምልናል ብለው ከመጠባበቅ ለራሳቸው ነጻነት ልዩነቶቻቸውን በማቻቻልና መለስተኛ ፕሮግራም በማዘጋጀት ህብረት ፈጥረው በአንድነት መታገልና ለለውጥ መነሳት አለባቸው ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት በዘንድሮው ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን እንዳይልክ የወሰነው የኢህአዴግ መንግስት በየ5 አመቱ የሚያደርገውን የተሳሳተ ምርጫ በማጀብ ህጋዊነት ለማሰጠት እንደከዚህ በፊቱ ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆኑን ለመግለጽ ሆኖ ሳለ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ህበረቱ በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት ታዛቢ አልክም ብሎአል ብሎ የጀመረው ቅስቀሳ መሰረተ ቢስና የተለመደ ህዝብን የማዘናጊያ ወሬ እንደሆነ ገልጸዋል። የአመቱን 60 በመቶ የሚሸፍን በጀት የሚሰጠው ህብረቱ፣ ኢትዮጵያን የመሰለ ስትራቴጂክ አገር፣ ህብረቱ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ብሎ ማሰብ ራስን እንደማታለል ይቆጠራል ብለዋል።
ህብረቱ ምርጫው ከመደረጉ ከሚቀጥለው ወር በፊት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችንና ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን በስፋት የሚያሳትፍ ትልቅ ጉባኤ በሚያዚያ ወር ላይ ለመጥራት በዝግጅት ላይ እንዳለ በዚህ ስብሰባ ላይ ተገልጿል።
አንዳንድ የፓርላማ አባላት በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደግብጽ ህዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ከመዒው ግንቦት ምርጫ በፊት አምባገነንነትን ከራሱ ትከሻ ላይ ለማውረድ መነሳት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀርብበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ አቋሙን እንዲገልጽ ቢጋበዝም ፣ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆነ ቤልጂየማዊ ዜጋ የሆነ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የተገኘ ሲሆን ስራውም መረጃ መሰብሰብ እንጅ አስተያየት መስጠት አለመሆኑን ገልጾ፣ ምንም ንግግር ሳያደርግ ወጥቷል።


የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነ

• ‹‹ከምርጫው በኋላ ይመለስላችኋል ተብለናል›› አርሶ አደሮቹ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን እንዲመልሱ እያሳሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ከወራት በፊት ጀምሮ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ሲጠይቁ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሮቹ፤ አሁን ምርጫው መቃረቡን ተክትሎ ካድሬዎች ቤት ለቤትና ስብሰባ ላይ ከሚናገሩት በተጨማሪ በየ ቤተክርስቲያኑም አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል፡፡ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ የሚጠይቁት ካድሬዎች ‹‹የእርሻ መሬት ካርታ ውስጥ ሊካተት ስለሆነ ነው፣ በህገ ወጥ መንገድ የግጦሽ መሬት የሚያርሱ ስላሉ ነው፣ መሬት ይዞታ ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች አሉ….›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እንደሚሰጡ የገለጹት አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን የማስረከብ ግዴታ እንዳለባቸውና ከምርጫ በኋላ እንደሚመለስ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ ምርጫ በተቃረበበት ወቅት የመሬት ይዞታ ደብተር መሰብሰቡና ከምርጫ በኋላ ይመለስላችኋል መባሉ በመጭው ምርጫ ኢህአዴግን አይመርጡም ተብለው በሚታሰቡት አርሶ አደሮች ላይ ፍርሓትና ጫና ለመፍጠር ሳይሆን እንዳልቀረም አርሶ አደሮቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡


Tuesday, February 3, 2015

የዞን ዘጠኟ ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን ተላጭታ ፍርድ ቤት ቀረበች – “የእምነት ክህደት ቃላችንን ከመስጠታችን በፊት ዳኛው ይነሱልን” – ዞን ዘጠኞች

ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን በመላጨት ኢፍትሃዊነት እና ዘረኝነት መስፋፋቱን በይፋ ተቃውማለች:: – የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ዳኛ እንዲቀየርላቸው ማመልከቻ አቅርበዋል:: ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:- በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ዞን ዘጠኝ ጦማርያን ጋዜጠኞች እንዲሁም የዲብርሃን አዘጋጅ የሆነው ዘላለም ወርቃለማሁ እና ከጋምቤላ በአሸባሪነት የተፈረጁ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል::በኢትዮጵያ የሆላንድ ኤምባሲና ሌሎች ዲፕሎማቶች በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመከታተል ተገኝተዋል:: በዛሬው እለት ጋዜጠኛ ኢዶም ጸጉሯን በመላጨት በወያኔ መንግስት እና በእስር ቤቱ ያለውን በፍርድ ቤቱ የሚታየውን አድልዎ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊነት እና ዘረኝነት በመቃወም አሳይታለች::


ሰበር ዜና የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ!!

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡

በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

Monday, February 2, 2015

ወያኔ የጋረደብንን የመበታተን አደጋ ለማክሸፍ ትግላችንን ማቀናጀትና በአንድ የአመራር ጥላ ሥር ማሰባሰብ ወቅቱ የሚጠይቀን እርምጃ ነው

ትግራይን ከተቀረው የአገራችን ክፍል ለመገንጠልና የትግራይን ሪፑፕልክ ለማቋቋም ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ የዛሬ 40 አመት ደደቢት በረሃ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፡ በለስ ቀንቶት የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ፡ በስሙ የሚነግድበትን የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በአገራችንና በመላው ህዝባችን ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎችና ያደረሳቸው ሰቆቃዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::

ከነዚህ ወንጀሎች ሁሉ የከፋውና ምናልባትም የሚቀጥለውን ትውልድ ጭምር ዋጋ ያስከፍላል ተብሎ የሚፈራው ምዕራባዊያን ቅኝ ገዥዎች አህጉራችን አፍሪካን በተቀራመቱበት ወቅት የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘምና ቅኝ የገዙዋቸውን ህዝቦች ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ እንዲመቻቸው የተጠቀሙበትን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊስ በምድራችን ተግባራዊ በማድረግ ለዘመናት የተገነባውን የህዝብ አንድነትና የአገር ሉአላዊነት ሊያናጋ በሚችል መልኩ በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍለን የጎሪጥ እንድንተያይ የተፈጸመብን ደባ ነው::

በአብድራፊና በሶረቃ ከተማ የህዝብ ተመራጮች እየተያዙ ነው፡፡

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ህዝቡን አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች እየታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች አመራሮችም እየታደኑ ነው።

የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአካባቢው ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አቶ አዋጁ አቦሃይ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2007 ዓም በ8 የፌደራል ፖሊሶች መሳሪያቸውን ተቀምተው ታስረዋል። ሶረቃ ውስጥ የሚኖሩ አቶ ደጀን የተባሉ ሰውም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሃይሌ ማሞ የተባለውን የአካባቢው ተወላጅ ለመያዝ እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም፣ ግለሰቡ ግን ከአካባቢው መሰወሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አካባቢው በልዩ ሃይል እየተጠበቀ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ ለ23 አመታት የተጫነው ቀንበር ይበቃናል በማለት ተቃውሞ እያሰማ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በርካታ የሰሜን አርማጭሆ ተወላጆች መንግስትን በሃይል ለማውረድ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተቀላቀሉ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።