Tuesday, October 28, 2014

አሸባሪዎች ገብተዋል ተብሎ ፍተሻ በተደረገ ማግስት በቦሌ የድምጻችን ይሰማ መፈክሮች በሌሊት ተጽፈው አደሩ

ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል። መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል።
ተመሳሳይ መልእክት የያዙ መፈክሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሊት ተለጥፈው ታይተዋል። መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ በሃይል ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርግም ተቃውሞው ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲል ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የፍርድ ሂደት በሰበብ አስባቡ እየተጓተተ መሆኑ መዘገቡ ይታወቃል።


No comments:

Post a Comment