Friday, October 31, 2014

የግንቦት 7 በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን የመጨረሻው ታጋዮች ምርቃት አካሄደ

ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ  ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል።

የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ  ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ ስርዓት ከህዝብ እና ከሃገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጊዚያት በርካታ ስራዎችን  በመስራት አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ማለታቸውን_ህዝባዊ ሃይሉ ለኢሳት የላከው መግለጫ ያመለክታል  ።

የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና  የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ባደረሱበት ወቅት ላይ መርቃቱ መደረጉን ያወደሱት ኮማንደሩ፣  የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው እንደሚሆን አስረግጠው ተናግረዋል።

ኮማንደሩ ‘’ስልጠና ለአንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደመሆኑ መጠን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ  እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ በማለት   ለስልጠናው መሳካት የተለያዩ  ድጋፎችን ላደረጉ አካላት ምስጋና  አቅርበዋል።

የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ከዚህ ቀደም በ4ተከታታይ  ዙሮች  ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ማስመረቁ ይታወሳል።


ሰበር ዜና –አብርሃ ደስታ; ሀብታሙ አያሌው; የሽዋስ አሰፋ ; ዳንኤል ሺበሺ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

• አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል

• ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡

የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-

1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው

ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡

የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል

አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል
* “መረጃ ለአንድ ለአምስት ማቀበል አለባችሁ” ፖሊስና ካድሬዎች
* የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል
* “መውጫና መግቢያ ሰዓታችሁ መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” ነዋሪዎቹ
ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

“አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ ቁጣቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በተለምዶ ካታንጋ ወደሚባል ስፍራ ሄደው ገዳዩን አውጡ ብለዋል፡፡ መኪኖችን ሰባብረዋል፡፡ ካታንጋ ምንም ፍንጭ ሲያጡ ወደ ፊላሚንጎ አምርተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ፖሊስ የተወሰኑትን ይዟል፤ ያመለጡም አሉ፡፡ እስካሁንም ውጥረቱ አለ” ስትል አንዲት የአካባቢው ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግራለች፡፡

ቀደም ብሎ ተለጥፎ በተገኘው ወረቀትና በሟቹ ምክንያትም ፖሊስና የኢህአዴግ ካድሬዎች የተለያዩ ጫናዎችን በነዋሪዎች ላይ ማሳደር መጀመራቸው ታውቋል፡፡ “ለስድስት ወራት ችላ ብለውት የነበረው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ስብሰባ አሁን እንደገና ጀምረውታል፡፡ አደረጃጀቱ ስራውን ካቆመና ስብሰባ ካደረግን 6 ወራት አልፈውት ነበር፡፡ ከትላንት ጀምሮ ግን በግዳጅ ጀምረውታል” ሲሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ምንጮች አክለው እንዳስታወቁት ነዋሪዎችን ፖሊስና ካድሬዎች በስብሰባ በመያዝ የተለያዩ የማሳመኛ ሰበቦችን እንደሚያነሱ ተገልጾአል፡፡ “ምርጫ ደርሷልና አብረን እንስራ፡፡ 97 የሆነውን ታውቃላችሁ፡፡ ያ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ስለሆነም ሙሉ ሌሊቱን በራችሁ ላይ መብራት ማብራት አለባችሁ፤ የተከራይ መታወቂያ ማየት አለባችሁ፡፡ እያንዳንዷን መረጃ ለፖሊስና ለአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ማቀበል አለባችሁ” እንዳሏቸውም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በየስብሰባዎቹ በአብዛኛው የሚገኙት ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ነዋሪዎች በግዳጅ በተፈጠሩት የአንድ ለአምስቱ አደረጃጀቶች መሪ ለመሆን የሚፈልግ አለመኖሩንም ምንጮች ተናግረዋል፡፡

“እያንዳንዱ ሰው የሚወጣ የሚገባበትን ሰዓት መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ “አከራዮች ተከራዮቻችሁ የሚገቡበትን ሰዓት ገደብ ማስቀመጥ አለባችሁ፤ የበር መብራቱንም ማጥፋት ክልክል ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ መብራት ያላበራ ይቀጣል፤ ፍርድ ቤት ሁሉ ሊቀርብ ይችላል” ተብሎ በየስብሰባዎቹ እንደተነገራቸው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጨምረው አስረድተዋል፡፡

   ምንጭ፡ ነገረ ኢትዮጵያ


Wednesday, October 29, 2014

የ “ካዛንችሱ መንግሰት በአዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት”

ግርማ ሰይፉ ማሩ

ዛሬ ጥቅምት 17/ 2007 እግር ጥሎኝ አዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት ጎራ ብዬ ነበር፡፡ የታዘብኩት ነገር ያስታወኝ ኤርሚያስ ለገስ “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ባወጣው መፅሃፍ ውስጥ “የካዛንችስ መንግሰት” ብሎ ያስነበበንን በገሃድ ከካዛንችስ ቦታ ቀይሮ አዲስ አበባ መስተዳደር ግቢ ውስጥ መኖሩን ነው፡፡ የካዛንችሱ መንግሰት ምን እንደሚሰራ እዚህ መዘርዘር አይጠበቅብኝም፤ በጥቅሉ ግን የአዲስ አበባ ህዝብ“መርጦ” ወይም ቀጥሮ ያስቀመጣቸው ሰዎች ሳይሆን ውሳኔ የሚስጡት ሌሎች በስውር በደህንነት ስም በኢህአዴግ የተቀመጡ ሰውር እጆች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

እነዚህ ሰውር እጆች ለእኛ ለተቃዋሚዎች አዲስ አይደሉም ለምሳሌ፤

በሆቴሎች አዳራሽ ለማከራየት አንችልም ምንም ጠቃሚ ገንዘብ ቢሆን ሆቴሎች ፈቃደኞች አይደለም፤

መብራት ኃይል ለአንድነት የማተሚያ ማሽን ሊያንቀሳቅስ የሚችል የኤሌትሪክ ሀይል (ሰሪ ፌዝ የሚባል ሀይል) ለፓርቲ ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለም፤

ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ላይ ነን – እንጠቀምበት!

በአለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንም የማይገናኙ እና የተመሰቃቀሉ የሚመስሉ፤ በጥልቀት ላያቸው ግን የተያያዙና የተደጋገፉ ከመሆናቸው አልፎ እንደከዋክብት ፈለግ አቅጣጫን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል። የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ሳንጠብቅ አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘነበው የዘለፋና የዛቻ ውርጅብኝ ህወሓት በቀጥታ በማይቆጣጠራቸው ማኅበራት ላይ ሁሉ ሲደርስ የቆየው ነፃ ማኅበራትን የማፍረስ ዘመቻ አካል መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። ህወሓት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ነፃ ማኅበርን በቁጥጥሩ ውስጥ ካስገባ በኋላ ፊቱን ወደ ክርስትና በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማዞሩ የተረጋገጠ ነገር ሆኗል። ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ማንም ከጥቃት እንደማያመልጥ፤ ለምንም ጉዳይ ይቋቋም ወያኔ የማይቆጣጠረው ማኅበር እንዲኖር የማይፈልግ መሆኑ ከዚህ በፊት የሚታወቅ ቢሆን በድጋሚ ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኗል።

Tuesday, October 28, 2014

ሰበር ዜና – የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ጥያቄ ያነሳው የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ሰራተኛ ታሰረ

ነገረ ኢትዮጵያ

- ‹‹ደርግንም ሆነ ምኒልክን እናውቃቸዋለን፡፡ እናንተ ስለ እነሱ መጥፎውን ከምትገልጹልን እንደ 97 እንደማትገድሉና ነጻና ፍትሃዊ ምትጫ እንደምታደርጉ ንገሩን፡፡››

– ስልኩን እና የማስታወሻ ደብተሩን ካድሬዎች እና ደህንነቶች እየተጠቀሙበት ነው።…
-ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ገዥው ፓርቲ በሚሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ጥያቄ የጠየቀና ስርዓቱን የተቸ የአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኛ ታሰረ፡፡ ፋንታሁን የተባለው የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ሰራተኛ በስልጠናው ወቅት ጥያቄዎቹን በማንሳቱና ስርዓቱን በመተቸቱ መታሰሩን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

በስልጠናው ወቅት ስላለፉት ስርዓቶች በተነሳበት ወቅት ‹‹ደርግንም ሆነ ምኒልክን እናውቃቸዋለን፡፡ እናንተ ስለ እነሱ መጥፎውን ከምትገልጹልን እንደ 97 እንደማትገድሉና ነጻና ፍትሃዊ ምትጫ እንደምታደርጉ ንገሩን፡፡›› ሲል አስተያየት የሰጠው ፋንታሁን ይህና ሌሎች አስተያየቶቹ መስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ የኢህአዴግ ካድሬዎችን እንዳስቆጣ ገልጾአል፡፡ ስብሰባው ካለቀ በኋላም ረቡዕ ጥቅምት 13/ 2007 ዓ.ም አንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ደህንነቶች እንደያዙት ገልጾአል፡፡

በስልጠናው ወቅት ጥያቄ በመጠየቁና ትችት በመሰንዘሩ አንበሳ አውቶቡስ ውስጥ የሚሰሩ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ‹‹ግንቦት 7 ብሎ ጠረጴዛ ላይ ጽፏል፡፡›› የሚል የሀሰት ክስ እንደከፈቱት ፋንታሁን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ከታሰረ በኋላ ስልኩና የግል አጀንዳውን የተቀማ ሲሆን ስልኮቹን መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያሉት ካድሬዎች እየተጠቀሙበት እንደሆነና ስልክ ሲደወልም እያነሱ እያነጋገሩ እንደሆነ መረጃ እንደደረሰው ገልጾልናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ አገሩ ወቅታዊ ሁኔታ የጻፋቸውንና ሌሎችንም ጉዳዮች ያሰፈረበትን የግል ማስታወሻው ደህንነቶች ‹‹ምን ማለት ናቸው? ከማን ጋር ነው የምትገናኘው?›› እያሉ ጫና እያሳደሩበት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ስልኩና ማስታወሻ በካድሬዎችና በደህንነቶች እጅ በመግባቱ ‹‹የግል ማስታወሻዬና ስልኬን ደህንነቶችና የኢህአዴግ ካድሬዎች እየተጠቀሙበት በመሆኑ እኔ ግንኙነት ከሌለኝ አካል ጋር ግንኙነት እንዳለኝ አሊያም ያልጻፍኩትን የጻፍኩ በማስመሰል እንደማይከሱኝ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡›› ሲል ፋንታሁን ስጋቱን ገልጾአል፡፡

ፋንታሁን በተለምዶ ችሎት ተብሎ በሚጠራው ቀጨኔ መዳህኒያለም አካባቢ በሚገኝ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን ነገ ማክሰኞ/ ጥቅምት 18 ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡

የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን ቅጣት ተጥሎባቸው ስልጠናውን ዳግመኛ እንደወሰዱ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል

አቡነ ማትያስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው! የዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ውሎ በድንገት ተቋረጠ

ያደረውን የሕገ ቤተ ክርስቲያን አጀንዳ በፈቃዳቸው ትተው ሌላ ርእሰ ጉዳይ አንሥተዋልየተቃወሟቸውን አባቶች በአሳፋሪ ንግግሮች በመዝለፍ ለማሸማቀቅ ሙከራ አድርገዋልየሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አጀንዳ ቀጣይነት በድምፅ ሊወሰንበት እንደሚችል ተመልክቷልእንደ ሕጉ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ይቀጥላል
‹‹ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡›› /ቅዱስ ሲኖዶሱ/በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንናከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡‹‹ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡››‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!››

/የምልአተ ጉባኤው አባላት/

* *

ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አክራሪና አሸባሪ ሊባል የሚችልና የሚገባው አካል እንደሌለ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አባላት ገለጹ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስም በማንኛውም መድረክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል/ተቋም አክራሪና አሸባሪ ከማለት እንዲቆጠቡ ምልአተ ጉባኤው በጥብቅ አስጠንቅቋቸዋል፡፡

‹‹በቤታችን ውስጥ አክራሪና አሸባሪ የሚባል አንድም አካል የለንም፤›› ያሉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ፓትርያርኩ ሌሎች በሌላ መድረክ እንደሚሉት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ የሚሉ ከኾነ ‹‹ተወጋግዘን እንለያያለን›› ሲሉ በአጽንዖት አሳስበዋቸዋል፡፡

ፓትርያርኩ በምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው፣ ቤተ ክርስቲያን በአክራሪነት የምትፈረጀው፣ ‹‹ማኅበራት በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት ስለሚሰበስቡ ነው፤›› በማለት ‹‹በሕግ ማስተካከል አለብን›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚኽም በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ‹‹ሕጋዊና ዘላቂ መፍትሔ አስቀምጣለኹ›› በሚል ለውይይት በቀረበው የማሻሻያ ረቂቅ÷ ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድድና ተጠሪነታቸውም ለቅ/ሲኖዶሱ መኾኑ ቀርቶ ለፓትርያርኩ እንዲኾን የሚደነግግ አንቀጽ ካልገባ በሚል የምልአተ ጉባኤውን ሒደት ለተከታታይ ኹለተኛ ቀን እግዳት ውስጥ ከተውት ውለዋል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የማሻሻያ ረቂቅ የማኅበራትን ጉዳይ ጨምሮ በፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ጎልተው የወጡ ሦስት ዐበይት ነጥቦችን ባስቀመጠው ልዩነት ትላንት የተጀመረው ፍጥጫ የተሞላበት ውይይት በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የቀትር በኋላ ውሎው ወደለየለት መካረር አምርቶ ብዙም ሳይቆይ ለስብሰባው በድንገት መቋረጥ ምክንያት ኾኗል፡፡
የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት፣ ጠዋት ስብሰባው እንደተጀመረ ርእሰ መንበሩ ከትላንት ለዛሬ ስላደረው አጀንዳ ምንም ሳያሳውቁ በቀጥታ በደቡብ አፍሪቃ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ ስላለው አለመግባባት ወደተመለከተው አጀንዳ አለፉ፡፡ በአንዳንድ የስብሰባው ምንጮች መረጃ፣ ፓትርያርኩ ለአኹኑ እንተወው በሚል ወደ ግንቦት እንዲሸጋገር ጠይቀው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ኹኔታው ለጊዜው በዝምታ ቢታለፍም በሻይ ዕረፍት ሰዓት ብፁዓን አባቶች በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት ከዕረፍት መልስ የአርቃቂው ኮሚቴ አባል በኾኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥያቄ ተነሥቷል፡፡

‹‹ለምን ወደ ሌላ አጀንዳ ይገባል፤ ጉዳዩ በዚኽ መልክ መታለፉ አግባብ አይደለም፤›› ያሉት ብፁዕነታቸው የልዩነት አቋም የተያዘባቸው የአጀንዳው ነጥቦች በውይይት እልባት እንዲያገኙ አልያም ምልአተ ጉባኤው በሕጉ መሠረት ድምፅ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡

ፓትርያርኩም የትላንቱን አቋማቸውን እየመላለሱ ‹‹ገንዘባቸውን ገቢ ያደርጋሉ፤ ገቢ ካላደረጉ በተኣምር አጀንዳውን አናየውም፤ ወደ ሌላው ጉዳይ እንግባ፤›› ይላሉ፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱም ‹‹ማኅበራት በበጎ ፈቃድ ለተነሡበት አንድ ዓላማ የቆሙ እንጂ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ለመሥራት ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴትና ምን እንደሠሩበት መቆጣጠር ይገባል፤›› በሚል አቋማቸው ያለበትን ግድፈት እየነቀሱ የቀናውን ለማመላከት ይሞክራሉ፡፡ በትላንት ውሏቸው እንዳደረጉትም ፓትርያርኩ ‹‹ማኅበራት›› ሲሉ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን እንደተናገሩ በመውሰድ የማኅበሩ አጀንዳ በወቅቱና በተራው እንዲታይ ያማፅኗቸዋል፤ ነገር ግን መግባባት ባለመቻሉና የምሳው ዕረፍት በመድረሱ ጉባኤው ይነሣል፡፡


አሸባሪዎች ገብተዋል ተብሎ ፍተሻ በተደረገ ማግስት በቦሌ የድምጻችን ይሰማ መፈክሮች በሌሊት ተጽፈው አደሩ

ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል። መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል።
ተመሳሳይ መልእክት የያዙ መፈክሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሊት ተለጥፈው ታይተዋል። መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ በሃይል ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርግም ተቃውሞው ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲል ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የፍርድ ሂደት በሰበብ አስባቡ እየተጓተተ መሆኑ መዘገቡ ይታወቃል።


ህወሃትና የጦር አበጋዞቹ እሴቶች

ህወሃት የትግሬ ተወካይ ብቻ ሳልሆን ለትግራይ ህዝብ የሚያመልከውን አምላክም ጭምር የምመርጥለት እኔ ነኝ በሚል እብሪት ውስጥ ይገኛል። በዚህ እብሪቱም እየተመራ የምታመልኩትን ልመርጥላችሁ ብሎ አጠቃላይ ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም እያመሰው እንደሆነ እያየን ነው። እኔን የማይቀበል እጣ ፈንታው ከመታመስ በላይ የሆነ ወዮታ ነው የሚል ያልተፃፈ አዋጅም አለው። ህወሃት በትግራይ ትከሻ ላይ ተፈናጦ፤ ትግራይን ምርጫ አሳጥቶ እኔን እምኑ መንገዳችሁም ህይወታችሁም እኔ ብቻ ነኝ ብሎ ራሱን የትግራይ ጣዖት አድርጎ ሹሟል። ይሄን ጣዖት አንቀበልም፤ እኛ የራሳችን ሂሊና ያለን እንደ ሰው ማሰብ የምንችል ነን ያሉ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ባልታወጀው አዋጅ መሠረት አብዮታዊ ፀሎት እየተፀለየላቸው አፈር ለብሰው ቀርተዋል።የህወሃት የእብሪቱ መጀመሪያ “እኔ ያልኩት ካልሆነ ሁሉም ገደል ይግባ” ማለቱ ነው። የትግራይ ተወካይ እኔ ብቻ ነኝ ሌላው ሁሉ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው የሚል እምነቱ የድርጅቱን ሥር የሰደደ መሠሪነትና እብሪት የሚያሳይ ነው።

ብዙ ኢትዮጵያዊያን ህወሃት የቆመው ለትግራይ ህዝብ ነው የሚል ዕምነት አሳድረዋል። ይሄን አስተሳሰብ መቀበል የሚጠቅመው ለህወሃት ብቻ ነው።ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ክብርም ፍቅርም ያለው ቡድን አይደለም። ለትግራይ ህዝብ በጎ ምኞት እና ክብር ያለው ቢሆን ኑሮ የትግራይ ህዝብ የወደደውን እንዲመርጥ፤ ያልወደደውን እንዲተው ያልተሸራረፈ ነፃነት እንዲኖረው ያደርግ ነበር። እኛ እንደምናየው ግን የትግራይ ህዝብ የወደደውን ለመምረጥ፤የጠላውን ለመተው እንዲችል ነፃነትያለው ህዝብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ነፃነቱን በነፃነት ሥም ያጣ ህዝብ ሁኗል። ህወሃቶች የትግራይን ህዝብ ነፃነት ሸራርፈው ሸራርፈው ህዝቡን በሙሉ መያዣ አድርገውና ከወገኑ ለይተውት እየገዙት ይገኛሉ። የትግራይም ህዝብ ሳይወድ በግዱ ህወሃቶችን ተሸክሞ መከራው በዝቶ እየተገዛ ይገኛል።

ህወሃት መራሽ በሆነው መከላከያ ድህረ-ገፅ ላይ “ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ማስረፅ” እሴታችን ነው የሚል መፈክር በጉልህ ተፅፏል። ህወሃቶች መከላከያ ኃይሉ የቆመው የህዝቡን ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲዊያ አስተሳሰብ ለመንከባከብ ነው እያሉን ነው። የህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብት ሳይሸራረፍ ተከብሮ ቢሆን ኑሮ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ተሰዶ ሂዶ በባዕድ አገር ባልሞተ ነበር። ህዝቡ በኑሮ ውድነት ባልተሰቃየ ነበር፤ አገሪቷ ሠላም ርቋት እዚህም እዚያም የዜጎች ደም በከንቱ ባልፈሰሰ ነበር፤ የአገሪቷ ብሄራዊ አንድነት ላልቶ ዜጎች ይሄ ክልል አገራችሁ አይደለም እየተባሉ ከኖሩበት መንደር ውጡ ባልተባሉ ነበር፤ ዜጎቿ አገር ውስጥ ከመኖር ይልቅ በባህር ውስጥ አዞ መበላትን ምርጫቸው ባላደረጉ ነበር። አገሪቷ እንዲህ ምስቅልቅሏ ወጥቶ ባለበት ሁኔታ ህወሃቶች ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን መንከባከብ የሚችል ሠራዊት ገንብተናል እያሉ እያላዘኑ ይገኛሉ። ይሄንንም ለማጠናከር ስንል የጦር አበጋዞችን መሾም አስፈልጎናል ብለው የአንደኛ ደረጃ ፊደል ቆጥረው ያልዘለቁ ሽፍቶችን ሹመት በሹት እያደረጓቸው ነው።

“ዘላለማዊ ክብር” በሰይጣን መንፈስ ሲመራ ለነበረው ለመለስ ዜናዊ ይገባል ብሎ የሚያመነው “ክርስትያኑ” ደሳለኝ ኃ/ማሪያም በመለስ ዜናዊ መንፈስ እየተመራ ስልጣኑን ከያዘ ግዜ ጀምሮ 4 ሌተናል ጄኔራሎች፤ 9 ሜጄር ጄኔራሎች፤ 28 ብርጋዴር ጄኔራሎችን ሹሟል። ብዙ ሰዎች ግን ደሳለኝ ኃ/ማሪያም በዚህ ሹመት ውስጥ የመወሰን ድምፅ የለውም ይላሉ። እንዲያውም ደሳለኝ የነብሩን ጭራ ይዞ እንዳይለቀው ጭንቅ ሆኖበት የሚኖር ብኩን ግለሰብ ነው ሲሉም ያክላሉ። ያም ሆነ ይህ ደሳለኝ ኃ/ማሪያም የመለስ ዜናዊን ራዕይ ሊያስፈፅም በትር ስልጣኑን ጨብጧልና በእርሱ ዘመን ለሚሆነው ሁሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

ወደ ጦር አበጋዞቹ እንመለስ ከእነዚህ የጦር አበጋዞች መካከል አብዛኞቹ የህወሃት አባሎች መሆናቸው የታወቀ ነው። በዚህ ጥቅምት ወር ብቻ 3 ሌተናል ጄኔራሎች እና 3 ሜጄር ጄኔራሎች ተሹመዋል። እነዚህ የጦር አበጋዞች በየትኛው መደበኛ ጦር አውድማ ላይ ውለው ለዚህ ማዕረግ የሚያበቃቸውን ምግባር እንደፈፀሙ የሚያውቅ የለም። ሽፍቶች እና ጎሬላ ተዋጊዎች መሆናቸው ግን የሚካድ አይደለም። የሽፍትነትና የጎሬላ ውጊያ ልምድ ግን ለዚህ ማዕረግ የሚያበቃቸው ሊሆን እንደማይችል የታወቀ ነው።

ሌተናል ጄኔራል ሁነው ከተሾሙት መካከል

1ኛ. አብርሃም ወ/ማሪያም

2ኛ. አደም መሃመድ

3ኛ. ብርሃኑ ጁላ

ሲሆኑ ወደ ሜጀር ጄኔራልነት ያደጉት ደግሞ

1ኛ. ክንፈ ዳኘ

2ኛ. ተክለብርሃን ወ/አርጋይ

3ኛ. ዘውዱ እሸቴ ይባላሉ።

የእነዚህ የጦር አበጋዞች ሹመት ባላቸው የትምህርት ደረጃ፤ ለህዝባቸው ባላቸው ክብር፤ ለአገራቸው ባላቸው ፍቅር ሳይሆን ለጣዖቱ ህወሃት ያላቸው ታማኝነት ሚዛን ደፍቶ በመገኘቱ ነው።

ከስድስቱ የጦር አበጋዞች መካከል የአራቱ ሹመት ቤተሰባዊ ዝምድናን መሠረት ያደረገ ስለመሆኑ የሚከተለውን ትሥሥር እንድትመለከቱ እንጋብዛላእን።

1ኛ. በሌተናል ጄኔራልነት ማዕረግ የተሾመው አብርሃም ወ/ማሪያም የመለስ ዜናዊ የሥጋ ዘመድ ነው። የመለስ ዜናዊ ቅደመ አያት በጎን ከሌላ ሴት የወለዷቸው ሴት ልጅ ልጅ ነው።

2ኛ. ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኜ ደግሞ አባቱ አቶ ዳኜ ገ/ስላሴና የመለስ አባት የአቶ ዜናዊ እናቶች እህትማማቾች ናቸው።

3ኛ. ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ እሸቴ ደግሞ የመለስ ዜናዊን የቅርብ ዘመድ አግብቶ በጋብቻ ተሳስሯል። ሚስቱ ደግሞ በ18 ዓመት ታንሰዋለች።

4ኛ. ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ የመለስ ዜናዊ የአክስት ልጅ ነው።

ይህ መከላከያ ኃይል ተብሎ የአንድን ጎጠኛ ድርጅት ህልውና ለመጠበቅ የቆመውን ቡድን የሚመሩት የጦር አበጋዞች በትምህርት ደረጃቸው ከሚያዟቸው ተራ ወታደሮች የማይሻሉ፤ ከራሳቸው ወዲያ ህዝብና አገር የሚባል ነገር የማያውቁ፤ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የአገሪቷን ሃብት ለመዝረፍ የሚሸቀዳደሙ እና ራሳቸውን እንደ ኢንቨሰተር የሚቆጥሩ፤ የውትድርናን ሙያ ከነፍስ ግዲያና ከጭካኔ ለይተው የማያዩ እና ርህራሄ የሌላቸው ስለመሆናቸው የህወሃት ድርሳናት ይመሰክራሉ።

ህወሃት ርህራሄን የማያውቁ ጭካኞችን የጀግንነት ማዕረግ እየሰጠ በአገሪቷ ላይ እያሰማራ ይገኛል። የህወሃቶች ስነ-ምግባርም ሆነ ስነ-ልቦና ለጀግንነት የሚያበቃቸው አይደለም። በህወሃት መንደር ጀግናና ጀግንነት አይታወቁም። ጀግና እውነትን አይፈራም። ህወሃት እውነትን ስለሚፈራ ገና ድክ ድክ የሚሉ ነፃ ሚዲያዎችን ያለ ምንም ማወላወል ሊደመስሱ የሚሸቀዳደሙትን ይሾማል። ጀግና ነፃ ሚዲያን የሚፈራበት ምንም ምክንያት አይኖረውም። ጀግና ነፍሰ ገዳይ አይደለም። ህወሃት ህፃን ነብዩን የመሰሉ እንቦቀቅላዎችን ግንባር ግንባራቸውን ብለው ለመግደል የማይራሩ ጨካኞችን ይሾማል። ጀግና ሌብነትን ከልቡ ይፀየፋል። ህወሃት ግን ሌብነትን የሚፀየፉትን ሳይሆን የድሃ ንብረት ሰርቆ ሃብት ማካበትን እንደ ብልጠት የሚቆጥሩ ደካሞችን ጄኔራል እያለ ያሰማራል።

በዚህ በጥቅምት ወር የተሾሙት 6 የጦር አበጋዞች ለሹመት ሲታጩ የትምህርት ዝግጅታቸውና ብቃታቸው፤ ለአገራቸው ያደረጉት የላቀ አስተዋፅዖ፤በውጊያ አውድማ ያሳዩት ጀግንነት ታይቶ ነው የሚል ወሬ ከህወሃት መንደር ተሰምቷል። ህወሃቶች እና ደጋፊዎቻቸው ይሄን ለማመን አይቸገሩም። የእነዚህ ቡድኖች ዋና መለያ የገዛ ውሸታቸውን እውነት ነው ብለው አምነው ጥሩ እንቅልፍ መተኛት የሚችሉ መሆናቸው ነው። የገዛ ውሸቱን እውነት ነው ብሎ የሚያምን ግለሰብ ብርቱ የሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ የወደቀ መሆንኑ የስነ-አዕምሮ ተማራማሪዎች ይናገራሉ። ህወሃቶችም ብርቱ በሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ለማየት የዕለት ተዕለት ውሸቶቻቸውን እና የሚፈፀሙትን ፀያፍ ድርጊቶች ማየት በቂ ይሆናል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በጥቂት በዘረ ሃረጋቸውና በቤተሰብ ክር በተሳሰሩ ወንበዴዎች እጅ ወድቋል። በእነዚህ ዘራፊዎች የሚመራ የሠራዊት ኃይል የህዝቡን ዲሞክራሲያዊ መብት ማስከበር አይቻለውም። የጦር አበጋዞቹ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት እየዘረፉ ከገነቧቸው ህንፃዎች በየወሩ የሚሰበስቡትን ገንዘብ የሚጠይቅ ለህዝብ ወገንተኛ የሆነ መንግስት እንዲመሰረት ምንም ፍላጎት አይኖራቸውም። ለእነዚህ ጦር አበጋዞች ነፃነት፤ ፍትህ፤ እኩልነት እና እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚባሉ ነገሮች ያሸብሯቸዋል። እነዚህንም ጥያቄዎች ያነሳ አሸባሪ ተብሎ የዚህን ምድር ሥቃይ እንዲያይ ይደረጋል።ይሄ ቡድን ሥልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ ነፃነት ፤የህግ የበላይነት፤ እኩልነት የሚባሉ እሴቶች በኢትዮጵያ ይሰፍናሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

በመጨረሻም ተራው ወታደር እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነፃነቱን ተገፎ ለምንና ለማን እንደሚገልና እንደሚሞት ሳያውቅ በገዛ ወገኖቹ ላይ እየተኮሰና የንፁህ ደም እያፈሰሰ እንደሚኖር እያየን ነው። ተራው ወታደር ጋምቤላ ሂዶ ያገኘውን ሁሉ የሚገድለው ለምንድ ነው? ኦጋዴን ሂዶ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ለምንድ ነው? ጉራፋርዳ ወርዶ የመዥንግሮችን ደም የሚያፈሰው በምን ምክንያት ነው? ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲን አስፍነናል ከተባለ ይሄ ሁሉ ውጊያ ምንጩ ምንድ ነው? ሠራዊቱ ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች በቂ መልስ መፈለግ ይኖርበታል።ምንም ትርጉም በሌለው ውጊያ ውስጥ እየሄደ የንፁህ ደም ማፍሰሱን ለማቆምና ነገ በወንጀል ከመጠየቅ ራስንም ለማዳን ሠራዊቱ ራሱን ከዘረኞቹና ከዘራፊዎቹ የጦር አበጋዞች መለየት ይኖርበታል።ከእርሱ በሞራልም ሆነ በትምህርት ደርጃቸው ከማይሻሉ ጄኔራል ተብየዎች ራሱን ለይቶ ለነፃነት፤ ለፍትህ እና ለእኩልነት ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪያችንን አሁንም እናስተላልፋለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !


የወያኔ እና የዶ/ር ዲማ ድርድር ለምን ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አልተፈለገም?

ቀብር ወይንስ ድርድር ? ? ? በ24 ሰአት ድምጽህን ሳታሰማ አገሪቱን ልቀቅ የሚባልበት ሁኔታ….

በቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ወይዘሮ ጸሃይ ቶሎሳ የቀብር ስነስርአት ላይ ለመገኘት በህወሓት ተፈቅዶላቸው አዲስ አበባ የገቡት የቀድሞ የሕወሓት ባለስልጣን እና የአርባጉጉ አሰቦት እባ በደኖ ጭፍጨፋዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ ዶ/ር ዲማ ነገዎ የቀብሩ ስነ ስር አት እንዳለቀ በ24 ሰአት አገር ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው እየሰማን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ለድርድር አዲስ አበባ ገቡ ሲባል አይደለም ለቀብር ነው ያለው ሕወሓት የዶ/ር ዲማን ከአባዱላ እና ከሙክታር ፋይሰል አሊ ከተባሉ የሕወሓት ታዛዦች ጋር መታየታቸው ቢጠቆምም ተከታታይ ውይይቶች ለመጀመር የሕወሓትን ቅድመ ሁኔታ ካለማንገራገር ተቀብለው እያለ ውስጣቸውን ሰላም ያልተሰማቸው የሕወሓት ሰዎች ደህንነቶቻቸን ልከው በ24 ሰአት እንዲወጡ ተደርጓል ለምን ድርድሩ ለህዝብ በሚዲያ ተነግሮ በይፋ አልሆነም የሚል ጥያቄ ስለጠየቁ ወይንስ ከኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ጋር በድብቅ ስለተገናኙ ?

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/2208#sthash.Ou3uqwfE.m4eezDrs.dpuf

ሚሊዮኖች ድምጽ -ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ።“ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” በማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። “እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል።በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ፣ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል። “የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል።የአንድነት ራዲዮ የዘገበዉን እንደሚከተለው ያድምጡ !

Saturday, October 25, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀልና በሽብር የሚጠረጥራቸውን ሰዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በቀላሉ ለመያዝና ንብረቶቻቸውን ለመውረስ የሚያስችለው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የጠረጠሩትን ዜጎች በመያዝ ለፈላጊው ሀገር አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ትብብር መሰረት መረጃው በሚፈለገው ሀገር አግባብነት ባለው ተቋም ህጋዊ መጠየቂያ ደብዳቤ መሰረት ለተጠያቂው ሀገር በመላክ ይከናወናል ይላል፡፡ ስምምነቱ በተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳይ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ፣ ቃል የመቀበል፣ የሚያዙ ሰዎችን ወይንም ምስክሮች ለትብብር ጠያቂው ሀገር የፍርድ አካላት የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ፣ የፍርድ ሰነዶችን ለተጠርጣሪዎች የማድረስ፣ የንብረት ብርበራ ማድረግና መያዝ፣ የወንጀል ፍሬነገሮችን በመለየት የሚያዙበት፣ የሚታገዱበትና የሚወረሱበት ሁኔታ የማመቻቸት፣ የተጠርጣሪ ግለሰቦች ግንኙነት የመጥለፍ፣ በወንጀል ሒደት ውስጥ ሰርጎ በመግባት የወንጀል መረጃዎችን የማሰባሰብና በጊዜያዊነት ለወንጀል ስራ የተያዙ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ትብብሮችን ያጠቃልላል፡፡ ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ ዲሴምበር 4/2013 በሱዳን ካርቱም ከተማ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋር ትብብር በፈጸሙት ስምምነት መሰረት ይህ አዋጅ መቅረቡ ታውቋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ አራት ክፍሎች፣ 26 አንቀጾች ያካተተ ሲሆን ፓርላማው ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ኮምቴ የመራው ሲሆን በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሚቃወሙትን ሃይሎች ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሚሉ ታፔላዎችን በመለጠፍና በሽብር ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት በጎረቤት ሀገራት በጥገኝነት እንዳይኖሩ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እያሳደደ፣ አንዳንዶቹንም እያሰረ መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እያስከተለበትእንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሱዳን ለተቃዋሚዎች የመንቀሳቀሻ ቦታ እንዳትሰጣቸው ለማድረግ የአገሪቱን ሰፊ መሬት አሳልፎ መስጠቱን ተችዎች ይገልጻሉ። የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ተወካይ አቶ አንጋው ተገኝ የሱዳን ታጣቂዎች በድንበር አካባቢ የሚፈጽሙት ወንጀል እየባዛ ነው በማለት ተናግረዋል


በመከላከያ የጄኔራሎች ፍጥጫ – ከኢየሩሳሌም አርአያ

በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።

የይለፍ ሚስጥር ቁልፍ ሰብሮ መረጃ የሰረቀው ግለሰብ ጥፋተኛ ተባለ

አቶ ዮናስ ካሳሁን የተባለ ግለሰብ የወ/ሮ አኪኮ ስዩምን ኢ-ሜይል አድራሻ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ያለ ግለሰቧ ፈቃድ ባልታወቀ መንገድ በመጠቀም ግለሰቧ ከተለያዩ ሰዎችና ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ ወደራሱ አድራሻ በመላክ፣ በማጥፋትና ለ3ኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ፡፡ ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍ/ቤቱ ለሰኞ ጠዋት ቀጠሮ ይዟል፡፡ የኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሆነችው የግል ተበዳይ ወ/ሮ አኪኮ ስዩምን የኤሌክትሮኒክ አድራሻ ባልታወቀ መንገድ አልፎ የግል የመረጃ ልውውጦቿን ወደራሱ አድራሻ መላኩና ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠቱ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መረጋገጡም ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኤሌክትሮኒክስ አድራሻ (ኢ.ሜል) መረጃ የመስረቅና የማጥፋት ወንጀል ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርግለት በጠየቀው መሰረት፤ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ለመፈፀም በህገ-ወጥ መንገድ የተበዳይዋን የወ/ሮ አኪኮ ስዩምን የኤሌክትሮኒክ አድራሻና የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ባልታወቀ መንገድ በመጠቀም ግለሰቧ ከተለያዩ ሰዎች እና ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ ወደ ራሱ ከመላኩም በተጨማሪ ኢ/ር ግርማ ገላው ለተባለ ሶስተኛ ወገን መላኩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያረጋገጠ ሲሆን ግለሰቧ በተለያዩ ወቅቶች ለተለያዩ የንግድ ስራዎች ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር መልእክት የተላላከችበትን ቀናት በአገራችንና በአውሮፓውያን ዘመን ቀመር በግልፅ አስቀምጦ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ልኳል፡ ከኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ሦስት ጠበቆች አንዱ የሆኑትን አቶ ወገኔ ካሳሁንን አነጋግረን በሰጡን ምላሽ፤ ተከሳሽና ተበዳይ ቀደም ሲል የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸውና ግንኙነታቸው መቋረጡን፣ ከዚያ በኋላ የተበዳይዋን የኢሜል ሳጥን በመስበር በርካታ መረጃዎችን እንደሰረቀ በመታወቁ መረጃዎቹን እንዲመልስላት ራሷም በአማላጅም ጠይቃው እንደነበር ጠበቃው ተናግረዋል፡፡ “ተጠርጣሪው መረጃዎቹን እንድመልስልሽ 40 ሚሊዮን ብር ክፈይኝ፤ ያለበለዚያ መረጃውን አልመልስም” ማለቱን የጠቆሙት ጠበቃው፤ ከዚያም ወመረጃዎችን በመያዝ ክስ መመስረቱን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ “ምስክሮች እንድናቀርብ ፍ/ቤቱ ጠየቀን፤ በምስክርነትም ራሷ ተበዳይና የሰረቃቸውን የኢ-ሜይል መረጃዎች እንዲመልስላት አማላጅነት የላከቻቸው ሰዎች ቀርበው የሚያውቁትን አስረዱ” ያሉት ጠበቃው፣ ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ ተጠርጣሪው በበቂ ሁኔታ መከላከል ባለመቻሉና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም ሆነ ምስክሮች በበቂ ሁኔታ ጥፋተኝነቱን በማረጋገጣቸው ባለፈው ረቡዕ ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል ብለዋል፡፡ ፍ/ቤቱ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ተጠርጣሪው ማረሚያ ቤት እንዲቆይ ያዘዘ ሲሆን የቅጣት ውሳኔውን ለመስጠት ለሰኞ ጠዋት 3፡30 ሰዓት ቀጠሮ ይዟል፡፡ “በአገራችን የግለሰቦችን የመረጃ ሳጥን በህገ-ወጥ መንገድ በመስበር ጥፋተኛ የተባለ ሰው ስሰማ የመጀመሪያዬ ነው” ያሉት የኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ጠበቃ፤ እነዚህ ወንጀሎች በአገራችን አዲስ ናቸው፤ በ1949 የወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ላይ አልተካተቱም፤ በአዲሱ ላይ ግን ተካተው ይሄው እየሰሩ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ በኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ በአስጐብኚ ድርጅትና ማሽነሪዎችን በማከራየት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35701#sthash.PGU59dhZ.6Tf8fgzX.dpuf

Friday, October 24, 2014

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፈንድ አቋረጠ

በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረው የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም ተቋረጠ:ሪፕሪቭ የተባለ ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ የእንግሊዝ ኩባንያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ነበር::

እነዚህ ወገኖች ይህንን ግፊት የጀመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ምክንያት ዜጐችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ያፈናቅላል በሚል ክስ ነበር:: ይሁን እንጂ የግንቦት ሰባት ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና
በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመን በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመንሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለው ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከተላለፉ በኋላ፣ በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ጫናው እንዲጠናከር ሲጥሩ ነበር::
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይልም ሆነ በተገኘው አማራጭ ለመለወጥ የሚታገለው የግንቦት ሰባት አመራር ይሁኑ እንጂ፣ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ተጨማሪ ግፊት ይፈጥራል ብለውም ነበር::

Wednesday, October 22, 2014

መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ለእስር ይወጣል››
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር፡፡ ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን›› በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር፡፡
የሆኖ ሆኖ፣ ከእስክንድር ጋር ለ15 ደቂቃ ያህል ለማውጋት ችለን ነበር፡፡ እስኬው፣ ሁሌም መንፈሱ ጠንካራ ነው፡፡ ሰኞም ያ አስደማሚ ጥንካሬው፣ ትህትናው፣ እውነተኛ ቅንነቱ፣ ብርታቱ፣ ቀናኢነቱ…አብረውት ነበሩ፡፡
ሰዓት ደርሶ ከእስክንድር ጋር ቻው ከተባባልን በኋላ ‹‹ኤልያስ፣ አንዴ ላናግርህ›› ብሎ ከጠራኝ በኋላ ‹‹እባክህ አንድ መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ አስተላፍልኝ›› አለኝ፡፡ እስንክድር፣ ሁሌ ሀሳቤን አስተላልፍልኝ ሲለኝ ግልጽነቱ እጅግ ይማርካል፡፡
‹‹እሺ›› አልኩት››
‹‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ጥሩ ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል፡፡ ተመስገን የህዝብ ልጅ ነው፡፡ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ፡፡ እስሩ ስለሀገሩ ያበረታዋል፤ ያጠነክረዋል፡፡ ብዙ ነገር እንዲረዳ ያደርገዋል፡፡ ሰዎች ይታሰሩ እያልኩ አይደለም፡፡ ይሄ አንዱ የሰላማዊ ትግል መስራት ውጤት ነው፡፡ በለውጥ እና በትግል መስመር ላይ ያሉ ኢትዮጵኖች መታሰራቸው ነገ ለውጥ ያመጣል፡፡››
ካለኝ በኋላ ለሁሉም ‹‹እወዳችኋለሁ፣ አከብራኋለሁ፣ በተሰማራችሁበት የህይወት መስመር፣ በሰላማዊ መንገድ በርትታችሁ ለለውጥ ታገሉ!›› በልልኝ ብሎኛል፡፡
እኔም ዛሬ ‹‹የሀገሪቱን ህዝቦች አንድነት እንዲፈርስ እና በሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል ጸብና ቁርሾ እንዲፈጠር በማሰብ …›› የሚል ከባድ ክስ ብቀበልም የእስክንድርን መልዕክት ለማስተላለፍ አልተቆጠብኩም፡፡
ፍቅር ያሸንፋል!


ሰበር ዜና፣ ህውሃት “የመለስ ትሩፋቶች” መጽሃፍን ለስለላ እየተጠቀመበት መሆኑ ታወቀ

በቀድሞው የመንግስት ኮሚውንከሽን ጉዳዮች ሚንስትር ድኤታ አቶ ኤርምያስ ለገሰ የተጻፈውን እና በብዙ በአለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተነባቢ የሆነው “የመለስ ትሩፋቶች” የተስኘው መጽሃፍ የኢህአዴግን መንግስት በተለይም ደግሞ የህውሃትን የጥፋት ዘመቻ በሰፊው  ያጋለጠ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም መጽሃፉ ወደ PDF File  ተቀይሮ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በኢሜይል ሲሰራጭ ቆይቷል። መጽሃፉ በተለይ በዲሞክራሲ አክቲቪስቶች ዘንድ ተፈለኣጊነት እንደሚኖረው በማወቅኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የደህንነት ምንጮቻችን በዛሬው እለት እንዳስረዱን የህውሃት ኢህአዴግ የስለላ ማእከል ይህንን ፋይል ፊን ፊሸር ከተባለ የስለላ ቫይረስ ጋር በማጣመር በአሁኑ ሰአት በከፍተኛ ፍጥነት በኢሜይል በማሰራጨት ላይ ይገኛል።ይህ ቫይረስ ከ“የመለስ ትሩፋቶች” ፍይል ጋር ተጣብቆ ወደ ኮምፒውተር ዳውንሎድ ከተደረገ፣ ኮምፒውተሮት ላይ ያለውን የግል ፍይሎች ወድ ህውሃት የስለላ ማእከል ከመላክ እልፎ  የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፥1)  የህውሃት ይስለላ ኤጀንቶች በኮምፒውተሮት ላይ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል2)  ይህ ማለት በፈለጉት ሰዕት የኮምፒውተሮትን ካሜራ እና ማይክሮፎን በመጠቀም የግል እንቅስቃሴዎን መከታተል እንዲችሉ ያደርጋል3) በኮምፒውተሮት ላይ በኢንተርኔት  የሚስገቧቸውን እንደ ክሬዲት ካርድ እና ሶሻል ሴኵሪቲ ያሉ ሚስጥራዊ ቁጥሮችን  በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል4) በኢንተርኔት ላይ የሚጎበኟቸውን ድረ ገጾች እንዲሁም  በግልዎ የሚሳተፉባቸውን የማህበርዊ ሚድያ አካውንቶች እስከ ዩዘር ስም እና ፓስዎርዳቸው በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል5)  ከቤተሰብዎ እና ከጏደኞችዎ ጋር የሚያደርጉትን የኢሜይል እና የስካይፒ ግንኙነት በቀላሉ ማንበብ እና ማዳመጥ እንዲሁም አካውንቶቹን ሌላ ጥቅም ላይ ማዋል ያስችላቸዋል6)  በድርጅት ውስጥም ሆነ በግልዎ ለስብአዊ መብትዎ ወይም ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሚሟገቱ ከሆነ፣ እርስዎን በሃሰት ወንጅሎ ለእስር አና ለስቃይ ለመዳረገ መንገድ ይከፍትላቸዋልስለዚህ ይህ “የመለስ ትሩፋቶች” የሚል የPDF ፍይል በኢሜይል ከተላከልዎ የኢሜይል መልእክቱን ሳይከፍቱ ዲሊት በማድረግ እራስዎን ከጥቃት ያድኑ።
አባይ ሚዲያ

Tuesday, October 21, 2014

“እኔ ብቻ” ቢያክሙት የማይሽር የወያኔ በሽታ

ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና ዕብሪት የወያኔ አዲሰ ባህሪያት ሳይሆኑ አስራ ሰባት አመት ጫካ ዉስጥ በቆየባቸዉ አመታትና ዛሬም ከጫካ ወጥቶ አገር እየመራ በቆየባቸዉ ሃያ ሦስት አመታት አብረዉት የኖሩ መታወቂያ ካርዶቹ ናቸዉ። ዘረኝነት፤ አማራ ጥላቻና የትግራይ ሪፓብሊክ ህልም ዋና ዋናዎቹን የወያኔ መሪዎች ደደቢት በረሃ ከገቡ በኋላ በድንገት የለከፋቸዉ በሽታ ሳይሆን ከና ከልጅነታቸዉ ተጠናዉቷቸዉ አብሯቸዉ ያደገ በሽታ ነዉ። ወያኔ ጨካኝ ነዉ፤ ወያኔ ዉሸታም ነዉ፤ወያኔ ከሃዲ ነዉ፤ ወያኔ ለኢትዮጵያ ዳርድንበርና የግዛት አንድነት ደንታ የሌለዉ ባዕድ አካል ነዉ። እነዚህ ሁሉ የወያኔን ማንነትና ምንነት በትክክል የሚገልጹ የወያኔ በሽታዎች ናቸዉ። በዛሬዉ ቆይታችን በልዩ መነጽር አብረን የምንመለከተዉ የወያኔ በሽታ ግን በአይነቱ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት በሽታዎቸ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም በጠባይና በአገላለጽ ግን ለየት ያለ ነዉ።የኢትዮጵያ ህዝብ ለአመታት እንዳየዉም ሆነ ሀወሓትን መስረተዉ ለስልጣን ያበቁትና ህወሓት ለእነሱም አልበጅ ብሏቸዉ ጥለዉት የወጡት ግለሰቦች በቃልም በጽሁፍም እንደነገሩን ወያኔ የጫካ ዉስጥ ጠባዩን ዛሬም ያልለቀቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዛሬማ ጭራሽ ብሶበት ያየዉን ነገር ሁሉ ነጥቆ የራሱ

“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል” – ታማኝ በየነ

አሻራ፦ ጤና ይስጥልኝ አርቲስና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ በቅድሚያ ስለ ጊዜህ በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። አቶ አንዳርጋቸውን ለምን ያህል ጊዜ ታውቃቸዋለህ ? እንዴትስ ትገልጻቸዋለህ?

ታማኝ፦ አንዳርጋቸውን የማውቀው ከምርጫ 97 ጀምሮ ነው።በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ማለት ነው። ያኔ መቼም ሁላችንም ልባችን የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ ስለ ነበር በየእለቱ እየደወልን ሁኔታውን እንከታተል ነበር። እኔም ራሴ ሃገሬ ገብቼ እንደልቤ በነጻነት ለመኖር የምችልበት ጊዜ አሁን ነው ከሚል እምነት የመግባት እቅድ ነበረኝ። አንዳርጋቸውን የማውቀው እንግዲህ በዛ ግዜ በነበረን የስልክ ግንኙነት ነው። እስኪታሰር ድረስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ከመታሰሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያናገረኝ እኔን ነበር። ከኔ ጋር አውርተን ስልክ እንደዘጋ ነው የታሰረው።

ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ። ከዚያም ተፈቶ ወደ እንግሊዝ አገር ተመለሰ። በኋላም በቅንጅት ኢንተርናሽናል ተመርጦ ሲሰራ በስልክም በአካልም እንገናኝ ነበር። ከአንዳርጋቸው ጋር የነበረን ትውውቅ ይህን ይመስል ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም እንደገና ተከሰሰ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ እስር አሁንም እንደቀጠለ ነው። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከሃያ በላይ ጋዜጠኞች አገር ለቀው ተሰደዋል። ሌሎች ጋዜጠኞች “አሸባሪ” የሚል ቅጽል ተሰጥቷቸው በእስር ቤት ይማቅቃሉ። በጣት የሚቆጠሩት ብቻ አገር ቤት ሆነው የሚመጣውን ለመቀበል የተዘጋጁ ይመስላል። በቅርቡም ተመስገን ደሳለኝ ወደ እስር ቤት እንዲወርድ መደረጉ የሚታወስ ነው።አሁን ደግሞ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና ማዕከላዊ ሄዶ ክሱን እንዲወስድ በስልክ ተነግሮታል። ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በራሱ ብዕር ስለሁኔታው ሲገልጽ እንዲህ ብሏል። “እንግዲህ፣ ‹‹ማዕከላዊ ናና ክስህን ውሰድ›› ተብያለሁ” ብሎ ይጀምራል፤ ዛሬ በላከው ማስታወሻ ላይ።ኤልያስ ገብሩ*********************************
ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሞባይል ስልኬ አቃጨለች፡፡ ከጎኔ ወዳጄ አቤል አለማየሁ ነበር፡፡ የመስመር ስልክ ነው፡፡ አነሳሁት፡፡ ‹‹አቶ ኤልያስ›› የሚል የሴት ድምጽ አደመጥኩ፡፡ ‹‹አዎን›› በማለት መለስኩላት፡፡ ‹‹ቆይ አንዴ መስመር ላይ ጠብቅ›› አለችኝ፡፡
ወዲያው አንድ ወንድ አነሳና ሰላምታ ሰጥቶ አናገረኝ፡፡ የሚደውለው ከፌዴራል ፖሊስ መሆኑን ጠቆመኝና ‹‹ባለፈው ተቋርጦ የነበረው ክስህ ስለተዘጋጀ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቁጥር 76 መጥተህ ውሰድ›› አለኝ፡፡ ስለጉዳዩ ጥቂት ቃላቶች ተለዋወጥን፡፡
‹‹እሺ ሰሞኑን መጥቼ እወስዳለሁ›› አልኩት፡፡ ‹‹ዛሬም የምትችል ከሆነ መምጣት ትችላለህ›› አለኝ፡፡ ጎሳዬ ሲልም ስሙን ነገረኝ፡፡
…በውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ መታሰር ሳይኖርብህ ትታሰራለህ፡፡ ዋስትና መከልከል ሳይኖርብህ ትከለከላለህ፡፡ ዳኛ የሰጠው የተጨማሪ የምርመራ ቀን ሳይደርስ ‹‹ስንፈልግህ ትመጣለህ፤ ዋስ አምጥተህ ውጣ›› ትባልና ከእስር ትለቀቃለህ፡፡ ከአምስት ወራት በኋላ ደግሞ ትጠራና ‹‹ከስህ ተዘጋጅቷል ና›› ትባላለህ፡፡ …ነገ የሚሆነውን ነገር ደግሞ አታውቅም፡፡ …እንግዲህ እንዲህ ነች የዛሬዋ ኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!==============ከላይ ያቀረብነው የኤልያስ ገብሩን ጽሁፍ ሲሆን፤ አሁን በስደት የሚገኘው የስራ ባልደረባው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ደግሞ እንዲህ ብሏል።=============ፍትህ በየት አለሽ?
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ማዕከላዊ መጠራቱንና የጥሪው መንስኤም ከዚህ ቀደም ለእስራት የተዳረገበት ዕንቁ መጽሔት ላይ በሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አማካኝነት የወጣ ጽሁፍ እንደሆነ ነግሮናል፡፡
የኤልያስን ክስ፣የፍርድ ቤት ውሎና የማዕከላዊ ቆይታውን በቅርበት ይከታተል እንደነበረ ሰው የአሁኑ ጥሪ ግርም ቢለኝ የተወሰኑ ነጥቦችን ለማንሳት ወደድኩ፡፡
የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ አንቀጽ 43/ቁጥር 1 ‹‹በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ፣ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ካልወሰነ በስተቀር በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 59/2/እና 3 ድንጋጌዎች መሰረት ፣ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት፡፡..በማለት በማያሻማ መልኩ ቢደነግግም ጽሁፉ በወጣበት ወቅት የዕንቁ ዋና አዘጋጅ የነበረው ኤልያስ በማዕላዊ መርማሪዎች ትዕዛዝ ቀበቶውን ፈትቶ ታሳሪዎችን እንዲቀላቀል ተደረገ፡፡
ኤልያስ ከእስሩ ሁለት ቀናት በኋላ አራዳ ምድብ ችሎት እንዲቀርብ ተደረገ ፣ከሳሽ የማዕከላዊ መርማሪ ተጠርጣሪው የተያዘው በመጽሔቱ ላይ በወጣ ጽሁፍ የተነሳ በጅማ ዩኒቨርስቲ ብጥብጥ ተነስቶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናገረች፡፡
ኤልያስ በበኩሉ አዋጁን ጠቅሶ ለእስር መዳረግ እንደሌለበትና ጉዳዩን በውጪ ሆኖ መከታተል እንደሚችል ገለጸ፡፡
ዳኛው ለደቂቃዎች ካቀረቀሩበት ቀና ብለው‹‹እውነት ነው አዋጁ ጋዜጠኛው መታሰር እንደሌለበት ይናገራል፣ነገር ግን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አለብኝ ስላላ የ7 ቀን ጊዜ ሰጥቻለሁ በማለት አረፈው፡፡
ኤልያስ ወደ ማዕከላዊ ተመለሰ፡፡በነጋታው ግን የማዕከላዊ ሰዎች 30.000ብር ዋስ እንዲያቀርብ አድርገውት ለቀቁት፡፡
በቀጠሮው ቀን ኤልያስ ፍርድ ቤት የመሄድ ፍላጎት ነበረው፤ ግን አጠገቡ የነበርን ሰዎች ‹‹እነርሱ ሲፈልጉ ክሱን ሊቀሰቅሱት ይችላሉ እስከዛው ዝም ብለህ ጠብቅ” አልነው፡፡
እውነትም እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ኤልያስን የፈለገውም አልነበረም፡፡አሁን መዝገቡን ከቆለፉበት ክፍል አውጥተውት ‹‹ና››ብለውታል፡፡
አወይ ፍትህ?አቤት ፍርድ ቤት?ከወራት በፊት በዚሁ ጉዳይ ኤልያስን ያናገሩት ዳኛ አሁን ሲመለከቱት ምን ይሉ ይሆን?ምን ችግር አለው ‹‹ባለፈው ቀን ምን ላይ ነበር ያቆምነው››ብለውም ይጀምሩ ሆነዋል፡፡
——-መልካሙን ሁሉ ወዳጄ ሆይ እመኝልሃለሁ፡፡——–

Monday, October 20, 2014

ያዲሳባ ባለሥልጣናትና ቀምጣላ ካድሬዎች--ዝግ ቤቶች

ጎልጉል
September 19, 2012 08:28 pm By Editor
“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።
እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።
ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች

ኢትዮ ቴሌኮም ያወጣውን የአለባበስ ህገ ደንብ ከታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገለፀ።

በ2006 ዓመተ ልደት መጨረሻ ላይ አመታዊ የስራ ክንውኖችንና ቀጣይ የማሻሻያ ግምገማና ውይይት የመንግስት ትልቁ ተቋም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞችን ጨምሮ የመስሪያ ቤቱ ትልልቅ ባለስልጣናት የተሳተፉበት ስብሰባ ተካሄዶ የነበረ ሲሆን በስብሰባውም ላይ በቴሌኮሙ ቀጣይ መሻሻልና መደራጀት ያለባቸው አሰራሮች ከስራተኞቹ የቀረቡ ሲሆን መሻሻል እንዳላባቸውና ከውጪ ሃገር(foreign country) አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን(New technologies) በማምጣት የተቀላጠፈ አሰራር በያዝነው አዲስ አመት አሻሽለን እንቀጥላለን በማለትም ስብሰባው የተቋጨ ቢሆንም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በአ/ቶ ደብረ ፂዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የቀድሞው የኢትዮጲያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፕሬሽን የአሁኑ (ኢትዮ ቴሌኮም) በአመታዊ የስራ ውይይት ላይ ማሻሻያዎች ሊደረጉ ይገባል ተብለው ከቀረቡትና በጭራሽ ሰራተኞቹ ችግር ነው ያላነሱትን ሙስሊም የቴሌኮሙን ሰራተኞችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚጨቁንና ስራህን ወይም እምነትህን ምረጥ የሚል አባዛ የተጠናወተበትን የአለባበስ ህገ ደንብ በያዝነው አዲስ አመት እንዳወጣ ይታወሳል።

በአዲስ አወቃቀር ኢትዮ- ቴሌኮም ከተባለ ወዲህ አዲስ ማኅበር ያቋቋመው የቀድሞ የኢትዮጵያ የቴሌ-ኮምንኬሽን ኮርፕሪሽን ባወጣው ህገ ደንቡ ላይም ማንኛውም የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችና አስተዳደር ፂማቸውን ማሳደግ እንደማይችሉ፣ ሱሪያውን ማሳጠር እንደማይችሉ፣ ለሴቶች ደግሞ አባያ፣ ጅልባብ፣ ኒቃብ፣ አባያ መልበስ እንደማይችሉ ና ጉርድ ቀሚስ ና ሸሚዝ እንዲያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሙስሊሞችን ብቻ አላማ ያላደረገ ለማስመሰል በደንቡ ላይ ፀጉር ማሳደግ፣ ፀጉር መፈረዝ፣ ሲኪኒ ሱሪ መልበስ ወ.ዘ.ተ እንዳይደረግ የተገለፀ መሆኑ ተገልፆል። ይህ በኢትዮ ቴሌኮሙ የሚሰሩ ሙስሊም የሃገሪቱ ዜጎችን በቀጥታ የሚያሸማቅቀውም ህገ ደንብ ከጥቅምት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልፆ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁንና የቂሊንጦ ልሳን ምንጮቻችን ሙስሊም የቴሌኮም ሰራተኞችን የሚያሸማቅቀው የአለባበስ ህገ ደንብ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ከያዝነው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ነው ቢሉም በድጋሚ ለታህሳስ ወር ተግባራዊ ይደረጋል በማለት ማሻሻያ እንደተደረገበት ዘግበዋል።

በወርሃ ጥቅምት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የአላባበስ ህገ ደንብ ያወጣው ኢትዮ ቴሌኮም ህገ ደንቡን ለሰራተኞቹ በኢሜል ልኮ አስተያየትም እንዲሰጡት የጠየቀ ሲሆን በቴሌኮሙ የሚሰሩ ካድሬዎችን በኢንተርኔት መረብ በማደራጀት አሪፍ ህግ ነው፣ ይቀጥል፣ መሳጭ ህግ ነው፣ ይበረታታል…(fantastic,­ intersting, it sound’s nice etc) በማለት የሃሳብ መስጫው ላይ አስተያየት (comment) እንዲሰጡ አድርገው ድጋፍ እንዳገኙ አድርገው ለማቅረብ እንደሞከሩ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ህገ መንግስቱንና አለም አቀፍ ስምምነቶችን በግልፅ የሚንደውን ህገ ደንብ ከወርሃ ጥቅምት ለታህሳስ ወር ያሸጋገረበትም ምክንያትም የወጣው ህገ ደንብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ቅድመ ዝግጅት ይልስፈልገዋል የሚል ሃሳብ እንደተነሳና የኢትዮ ቴሌኮም ማህበርም ሃሳቡን ስላመነበት ሁሉም ሰራተኞች ቅድመ ዝግጅት ሊያደርግ ይገባል ብለው ለሰራተኞች ኢሜል እንዳደረጉላቸው ተገልፆል።

ፍትህ ለኢትዮጲያ ሙስሊም!
ፍትህ ለክርስቲያን ወገኖቻችን!


Sunday, October 19, 2014

ህወሃት በአማራ ነገድ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚያስቆመው ማን ነው? (አንተነህ ገብረየ )

አንተነህ ገብረየ

(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

መግቢያ፦ የዛሬ ጹሑፌን ከሰሞኑ ክስተቶች እጀምራለሁ-በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካው ፕረዘደንት ጋር ልዩ ውይይት ያደረገው በደሳለኝ ኃይለማርያም የተመራው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማደጓንና በምግብ ራሷን መቻሏን ከአሜሪካው ፕረዝደንት ምስክርነት በማግኘቱና በመሞካሸቱ ጮቤ እንደረገጠና ስለወደፊቱ የህወሃት መንግሥትና አሜሪካ ወዳጃሞች ሆነው በጋራ ስለሚቀጥሉበት በየተራ የተደረጉት ንግግሮች ሁለቱንም ትእዝብት ውስጥ የሚከትና ነገ ቁጭትን የሚግት መሆኑ ባይዘነጋም ከሁለቱም ዘንድ በጣም ጽንፍ የሆኑትን ነጥሎ መጥቀስ አስፈላጊ ነው።አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ሁሉም የበለፀጉ አገሮች ለሦስተኛው ዓለም አገሮች በተለይም በሕዝብ ላልተመረጡ ጨካኝ የአፍሪካ መሪዎች (un elected dictator african leaders) እርዳታ የሚሰጡት ዲያስፖራውን ጨምሮ የየአገራቸው ሕዝብ የሚከፍለውን የታክስ ገንዘብ መሆኑ ይታወቃል።

Breaking News: የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ኢትዮጵያ ገቡ

(ዘ-ሐበሻ) ዶክተር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ::የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶ/ር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸውን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መግለጹዋ ይታወሳል::የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ
ዘንድሮ በሚደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ለመሳተፍና ድርጅቱንም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለማስመዝገብ ወደ አዲስ አበባ እንዳቀኑ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጉዳዩ ብዙዎችን ማስገረሙን ገልጸዋል::
በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አማካኝነት በተለይ በሚኒሶታ የቀድሞ የኦነግ መሪዎችን ለማግባባት ከፍተኛ ሥራ ይሰራ እንደነበር ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም በፎቶ ግራፍ በተደገፈ ማስረጃ ስትዘግብ የቆየች ሲሆን በዶ/ር ዲማ ነገዎና በኦቦ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴፍ ለኦሮሞ ሕዝብ አዲስ የትግል ራዕይ አለኝ በሚል ሃገር ቤት ገብቶ ለመታገል መወሰኑንና ከዚህ በኋላም የኦሮሞ ሕዝብ ስለመገንጠል ሳይሆን በአንድነት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚኖርበትን መንገድ ፈጥሮ ለመታገል መወሰኑን መግለጹ ይታወሳል::በቀጣዩ ዲሴምበር ወር አካባቢ አቶ ሌንጮ ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ በሰፊው ሲወራ የቆየ ቢሆንም ምክትላቸው ዶ/ር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ ቀድመው ገብተው ድርጅቱን በኢትዮጵያ ለማስመዝገብ እየተሯሯጡ ይገኛሉ ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ኦዲኤፍ በቀጣዩ ምርጫ እንደሚወዳደርም ጠቁመዋል::ዶ/ር ዲማ ነገዎ በሽግግር መንግስት ወቅት በማስታወቂያ ሚ/ርነት ያገለገሉ መሆናቸው ይታወሳል::ይህን ተከትሎ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በሚኒሶታ አካባቢ የሚገኙ ፖለቲከኞችን ያነጋገሩ ሲሆን የዶ/ር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባትና የኦዲኤፍ በምርጫ መሳተፍ በገደል አፋፍ ላይ የነበረውን የወያኔ/ኢሕ አዴግ መንግስት ነብስ ይዘራበታል ሲሉ ይህን ውሳኔ ይተቻሉ:: እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉትም ኢሕ አዲኤግን በኃይል ለመጣል የመጨረሻው ሰዓት ላይ የደረሰ ቢሆንም የአቶ ሌንጮና የዶክተር ዲማ ኦዲኤፍ ኢትዮጵያ መግባት ኢሕ አዴግ ለሚፈልገው ና በምርጫ ስም ለሚያገኘው የፕሮፓጋንዳ ጥቅም አንድ አጋዥ ይሆንለታል ሲሉ ትችታቸውን ያስከትላሉ::በሌላ በኩል የኦዲ ኤፍ ኢትዮጵያ መግባት ለኦሮሞና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ድል ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች በተለይ እነዚህ የኦነግ መስራቾች የመገንጠል አላማቸውን ትተው በአንድነት ለመታገል መወሰናቸው ለሁሉም የምስራች ነው ይላሉ::የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በዚህ ዙሪያ የምትሰጡትን አስተያየት እንጠብቃለን::የኦዲኤፍን ውሳኔ እንዴት አዩት?

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሃገር ሃብት እየቀሙ ለግል ኑሮአቸው እያዋሉት መሆናቸውን ተገለፀ፣

እኒህ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  ባለስልጣናት በሃገር እና በህዝብ ሃብት ከውጭ ሃገራት የተገዙ ማሽኖችን ለባለስልጣናት የግል ጥቅም እየዋለ መሆኑን የገለፀው መረጃው በዚህ የሙስና ተግባር ከተሰማሩት መካከል አንዱ የትግራይ ክልል የትምህርት ቢሮ ሃላፊ የሆነው ጎበዛይ ወልደ አረጋይ መሆኑን ተገልጿል፣  ይህ ከትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆነው ጎበዛይ ወልደአረጋይ ከውጭ ሃገራት ተገዝተው የመጡ ጀኔረተሮችንና ሌሎች ንብረቶችን ወደ ተገልጋዩ ህዝብ ሳይደርሱ ለግል ጥቅሙ እያዋለው መሆኑን መረጃው አስረድቷል፣    የቢሮው ሰራተኞች ታዛቢው ህዝብና ፖሊሶች በዚህ ባለስልጣን እየተፈፀመ ያለውን ሙስና መፍትሄ እንዲሰጥበት ወደ ሚመለከተው አካል ያቀረቡትን አቤቱታ ሃላፊዎች ርስበርሳቸው እየተሻረኩ ሰሚ ጆሮ እንዳሳጡት ለማወቅ ተችሏል፣

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፡ በአሜሪካ ሲያትል ዋሽንግተን ዉስጥ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ

የግንቦት 7 ንቅናቄ ቅዳሜ ኦክቶበር 11 ቀን 2014 አ.ም በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ደማቅ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በሲያትልና አጎራባች ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት የታደሙበት እንደነበር ያደረሰን ዘጋቢያችን አገር ወዳድ ኢትዮጵያኑ በስብሰባው ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት የንቅናቄው ሊቀመንበር ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ሰፊ አገራዊ ውይይት ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። በሲያትል የተካሄደው ይህ ህዝባዊ ስብሰባ ኢትዮጵያውያን በዘር በሃይማኖት በጎሳ ሳይለያዩ በአንድነት በመሰባሰብ በአገራቸው ጉዳይ ላይ በሰፊው የመከሩበት፤ ኢትዮጵያዊነት እጅግ አምሮና አሸብርቆ የታየበት እንደነበርም ተመልክቷል።
በህዝባዊ ስብሰባው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶ/ር ብርሀኑ ለስብሰባው ታዳሚዎች ባደረጉት ንግግር “የምንገኝበት ወቅት ጊዜያችንን እንደ ከዚህ ቀደሙ መቋጫ በሌለው ውይይትና ጭቅጭቅ የምናጠፋበት ሳይሆን፤ ስለ ነፃነቴ እታገላለሁ የሚል ወደ ተግባራዊው ትግል የሚቀላቀልበት፤ በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ትግሉን መቀላቀል የፈራ ዝም ሊል የሚገባበት ወቅት መሆኑን በአንክሮ በማስገንዘብ በተጨማሪ የነፃነት ትግሉን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ የሚገኘውን የእርስ በርስ ጥልና ሽኩቻ በአስቸኳይ ቆሞ ሁላችንም በአንድነት በመነሳት በዋናው አላማችን ላይ ማለትም የጉጅሌው ወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ መዝመት ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በተለይ የነፃነት ትግሉ ለመቀላቀል እስካሁን እድሉን ላላገኙና በትግሉ ላይ የራሳቸው የታሪክ አሻራ ማሳረፍ ለሚሹ ወገኖችም የተቀላቀሉን ጥር ማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል። የቀረበላቸውን ጥሪ በመጠቀም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያውያን በአባልነት እንዲሁም በደጋፊነት በመመዝገብ ግንቦት 7 ትን መቀላቀል መቻላቸው ታውቋል። ትግሉ አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ለታዳሚዎች በስፋት ያብራሩት ዶ/ር ብርሃኑ ተሰብሳቢዎቹ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግንቦት 7 ለነደፋቸው የትግል ስልቶች ማለትም ለሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ዛሬ ነገ ሳይባል ምላሽ መስጠት መጀመር እንዳለበት ማሳሰብያ ማቅረቡ ታውቋል። በተለይ እነዚህን ስልቶች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ በተቀናጀ ሁኔታ መተገበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቆም ብሎ ሊያስብና ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገባ የሚገባበት ሰአት አሁን ነው ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ ይህንን በተሳካ ሁኔታ መተግበር ስንችል ጉጅሌዎቹን ከአገራችንንና ከህዝባችን ጫንቃ ማውረድ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ብርሃኑ ከተሰብሳቢው ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎችም አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተዋል። በተለይ በኤርትራ በኩል እየተደረገ ያለውን ትግል አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በተሰብሳቢዎች ዘንድ የነበረውን ብዥታ ማጥራት መቻላቸውንና ተሰብሳቢዎቹ እየተደረገ ላለው ትግል በጭብጨባ ድጋፍ መስጠታቸውን ከስፍረሰው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በመጨረሻም በስብሰባው ላይ በጠላት እጅ ወድቀው የሚገኙት የንቅናቄያችን ዋና ፀሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሥራዎች በስፋት መወሳታቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ የአቶ አንዳርጋቸው ስራዎች ሲቀርቡ አብዛኞቹ በሐዘን እና በቁጭት ሲያነቡ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በስብሰባው መገባደጃ ላይ ለጨረታ የቀረበው የነፃነት አርበኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፎቶግራፍም በከፍተኛ ገንዘብ መሸጡ ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ በጋራ እጅ ለእጅ በመያያዝ እየተደረገ ያለውን የነፃነት ትግል ከዳር ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መነሳታቸውን በቃለ መሐላ ካረጋገጡ በኋላ ስብሰባው መፈጸሙም ታውቋል።

ሁለቱ ሙሰኛ ባለስልጣናት /ከእየሩሳሌም አርአያ/

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱን መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። የሕወሐት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አባይ ወልዱ በክልሉ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱ የሆነውና በመቀሌ – ዓዲ ሃውሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ይህን ቪላ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ካስገነቡት በኋላ እንደሸጡት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አባይ ወልዱ በባለቤታቸው ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ስም በአዲግራት ከተማ ባለሶስት ፎቅ ዘመናዊና በውድ ዋጋ የተገነባ ቪላ እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል። የአባይ ወልዱ ባለቤትና የህወሀት ማ/ኰሚቴ አባል እንዲሁም የፓርቲው የፕሮፖጋንዳ ሃላፊና የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪ/ማርያም በትግራይ ክልል ከመንገድና ኮንስትራክሽን ስራዎችና በተለያየ ንግድ በክልሉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሙስና ተግባር መሰማራታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ..ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር አባልና በጅማ ክልል ባለስልጣን የነበረ አንድ ጎልማሳ እዚህ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ 4 የንግድ ድርጅቶች መክፈቱን ማረጋገጥ ተችሏል። ከነአባዱላ ገመዳ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበረውና የ42 አመት ጐልማሳ የሆነው ይህ የኦሮሚያ- ጅማ ዞን የቀድሞ ባለስልጣን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ አሜሪካ እንደገባና በአሁኑ ወቅት 1 ሊከር ስቶርና ሶስት 7/11 የንግድ መደብሮችን ከፍቶ እየሰራ መሆኑ ተረጋግጧል። 3 የተለያዩ ሃበሻ ወጣት ሴቶችን በማስቀመጥ ከ2ቱ የወለደው ይህ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ምድር ዘርፎ ባመጣው ሃብት እንዳሻው እየፈነጨ መሆኑን የታዘቡ ወገኖች « በሰው ደም ሃብት አካብተው አሜሪካ የሚሸሸጉ ወንጀለኞችን የአገሪቱ መንግስት ለምን ዝም ይላቸዋል?..ለምን ሽፋን ይሰጣል?» ሲሉ በቁጭት መጠየቃቸው አልቀረም።


Friday, October 17, 2014

እስማኤል አሊስሮ 11 ወጣት ምሁሮችን ከስልጣናቸው ሊያነሱ ነው (ሾልኮ የወጣውን የተባራሪዎቹን ስም ይዘናል) – ጸጋዬ በርሄ 12 ሚሊዮን ብር እንደሚያገኙ ተጋለጠ

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፡

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ እስማኤል አሊስሮ በመጪው የ2007 ምርጫ የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ለመቀጠልና በተጨማሪም የአብዴፓ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በከፍተኛ ተስፋ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።


አቶ እስማኤል አሊስሮ ከምርጫው በፊት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ያሰቡ ሲሆን። ሃሣባቸውንም ለማሳካት በአሰራራቸው የማይስማሙ 11 ምሁር ወጣቶች ከመሀል ኮሚቴ አባልነትና ከየኃለፊነት ቦታዎቻቸው ለማንሳት ተዘጋጅቷል። እነዚህ ወጣቶች በብዛት የህወሓት መንግስት በክልሉ እጁን እንዳያስገባ የሚል አመለካከት ያላቸው ሲሆን አቶ እስማኤል አሊስሮ ደግሞ በዚህ አይስማሙም።

Thursday, October 16, 2014

በጋምቤላ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

የአካባቢው ምንጮች አቦቦ በሚባለው አካባቢ የተጀመረውን ግጭት ተከትሎ ወታደሮች የሚወስዱትን እርምጃ በመቃወም መንግስት ያስታጠቃቸው ከ15 በላይ ታጣቂዎች ስርአቱን አናገለግልም በማለት መጥፋታቸውንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ታጣቂዎችን ለመያዝ አሰሳ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግስት ታጣቂዎች የነበሩ የጋምቤላ ተወላጆች ከመጥፋታቸው በፊት በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በመወሰዱት እርምጃ ከ2 ያላነሱ የመከላከያ አባላት መገደላቸውና የተወሰኑትም መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

በመዠንገር አካባቢ የተነሳውን ግጭት ለመቆጣጠር መንግስት አሁንም የመከላከያ ሃይሉን በስፋት አሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን፣ በመዠንገር ተወላጆች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊትን ዋቢ በማድረግ ወኪላችን ገልጿል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የመዠንገር ተወላጆችና የወረዳ አመራሮች መታሰራቸውን የገለጸው ወኪላችን፣ የታሰሩት ተወላጆች የቶር መሳሪያ እንዳልተገኘባቸው አክሎ ተናግሯል።

በሌላ በኩል ከ40 ያላነሱ የፌደራል ፖሊሶችና ከ10 በላይ የመከላከያና የወረዳ ታጣቂዎች የተገደሉበትን ግጭት በተመለከተ መረጃ ያካፈሉን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከ30 በላይ የሚሆኑ የፌደራል ፖሊሶች የተገደሉት በኦራል መኪና ላይ እንዳሉ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው። ጥቃቱን ተከትሎ ታጣቂዎቹ መሳሪያዎችና ከርቀት ማሳያ መነጽሮችን መውሰዳቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።

በጋምቤላ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት የነበረው ውጥረት እየቀነሰ በመምጣጡ ሱቆች መከፈት መጀመራቸውንና የከተማው ህዝብ ከቤት መውጣት መጀመሩን የሚገልጹት ነዋሪዎች ሁኔታው ግን አሁንም አስፈሪ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአካባቢው ለሚታየው ግጭት አንዳንድ የአካባቢው ባለስልጣናትንና ተቃዋሚዎችን ተጠያቂ ቢያደርጉም ስለተገደሉት የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ አባላት ሰይናገሩ ቀርተዋል። አቶ ግርማ ሰይፉም ጉዳዩን በተመለከተ ለጠ/ሚንስትሩም ጥያቄ አላቀረቡም።


በመጭው ሰንበት/እሁዶች አዲስ አበባ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው

ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው።

ንቅናቄው በጩሐት ሳይሆን ብልሃት እና ብስለት የተሞላበት መሆኑ ታውቋል።
የኢሕአዴግ መንግስት እና በቤተክህነት ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የተዋህዶ እምነትን የፖለቲካ አሽከር ለማድረግ የጀመሩትን ሴራ እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም በድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ እና በእኔም ለእምነቴ በብስለት እና ብልሃት በተሞላበት ሁኔታ በጋራ የተዘጋጀ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ሊካሄድ እንደሆነ እና ምእመናን ለዚሁ ንቅናቄ እንዲዘጋጁ ጥሪው ተላልፏል።
===============================
የመጀመሪያው ዙር ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ነው።
ለማኅበረ ቅዱሳን እመሰክራለው :: ለቀጣዩ የአደባባይ ምስክርነት በተጠንቀቅ እንዘጋጅ።
ምእመናን ምን ማድረግ እንዳለብን በቀጣይ ቀናት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

††† #ድምጻችንይሰማዘኦርቶዶክስ - #እኔም_ለእምነቴ ! ††† የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለማኅበረቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁልም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡

ናይሮቢ የሚገኘውን የጋዜጠኛ ሚሊዩን ሹሩቤ አስከሬን ወያኔ ወሰደው።


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ ራሱን የሰየመው አንተነህ አብርሃም ለጋዜጠኞች እየደወለ እየዛተ ነው፡፡

በቅርቡ የስደቱን አለም የተቀላቀለው እና ባጋጠመው የምግብ መመረዝ ድንገት ከዚህ አለም በሞት የተለየው የማራኪ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሪክተር እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አስከሬን ወያኔ በጉልበት መውሰዱን ከናይሮቢ ተሰምቷል።

በወያኒ ሴራ በተመረዘ ምግብ ሞቷል የሚባለው እና ለሞቱን መንስኤ እንደሆነች የምትጠረጠረው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማት ባልቤት የሆነች ግለሰብ ራሷን የሰወረች መሆኑ ሲታወቅ ጋዚጠኛ ሚሊዮንን ከዚመሞቱ ቀድሞ በየምሽቱ እየመጣች በዘመናዊ መኪና ፒክ እያደረገቸው ስታዝናናው እንደነበር ይታወቃል።የሚሊዮን ሹሩቤን አስከሬን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ ሲሰሩ የነበሩ ስደተኛ ጋዜጠኞች ፕሮሰስ ሲያደርጉበት የነበረውን ዶክመንት አስረክበዋል፡፡ የጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ ራሱን የሰየመው አንተነህ አብርሃም ለጋዜጠኞች እየደወለ እየዛተ ነው፡፡

መንግስት ጋዜጠኞችን አላሰደድኩም በማለት የጀመረውን ድራማ በአሳዛኝ ሁኔታ አስክሬን ቁጭ ብለው የሚጠብቁት ቤተሰብ ላይ ድራማ መስራት ስለጀመረና አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ እየሰራ ያለን ጋዜጠኞች ለደህንነታችን አስጊ ሁኔታ በመፈጠሩ ካሁን በኋላ የጋዜጠኛ ሚሊዮን አስክሬን መላክ ጉዳይ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ሃገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ የስራ ባልደረቦቻችን እንዲሁም መላው ህዝብ እንድታውቁት ይሁን ፡፡ ከቤተሰብ ተወክለው መጡ የተባሉት ሰዎች የማናውቃቸው ሲሆን አስከሬኑን ለመውሰድ ሀገር ውስጥ ገብታለች የተባለችው የጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ እህት የት እንዳለች የማናውቅና እህቱንም ማን እንደተቀበላት የምናውቀው ነገር አለመኖሩን ማሳወቅ እንፈልጋለን ፡፡የሚሊዮን ሹሩቤን ሞት ተከትሎ በኪንይ የምግኙ ስደተኛ ጋዜጠኞች በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እና ክትትል ስር መግባታቸው ታውቋል።


Wednesday, October 15, 2014

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት….

ከመልካም-ሰላም ሞላ

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ከ12 አመት በላይ የሰራ ወጣት ጋዜጠኛ “ነበር”፡፡ በነሃሴ ወር ውስጥ በመንግስት ወከባ ህይወቱን ከእስር ለማትረፍ ተሰዶ ወደሀገሩ በሳጥን ለመመለስ እየጠበቀ ያለ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ…ሚሊዮን፡፡ ተስፋ የነበረው ስደተኛ ጋዜጠኛ የመልካም ባህሪ እና ስብእና ባለቤት የነበረው ሚሊዮን፣ ስለሀገሩ ፍቅር ብዙ መሰናክሎችን ሊጋፈጥ ስደትን መርጦ ባሰበበት ሳይሆን በታሰበለት ሊኖር የተገደደው ሚሊ እንደወጣ በሰው ሀገር ልጄን እህቶቼን ቤተሰቦቼን ሃገሬን እንዳለ በድንገት ታሞ እንደፈራው ላይመለስ አሸለበ፡፡

ከሚሊ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት አብረን ኖረናል፡፡ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ እንደመጣ ከጓደኛው መላኩ ጋር ከኖረው እና ሆስፒታል እስከገባበት የመጨረሻዎቹ ሶስት ቀናት፤ የተረፉትን ሶስት ሳምንታት አብረን ነበር፡፡ እኔ ባሴ እና ሚሊ በጠባቧ ክፍላችን ያለፉትን ሶስት ሳምንታት ተጋርተን ነበር፡፡ ሚሊ ከሃገሩ ከወጣ በኋላ ወደ ሃገሩ በድጋሚ እንደማይመለስ ሲያውቀው አንድም ቀን ከጭንቀት ወጥቶ አያውቅም ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ “ከሃገሬ ስወጣ ሰማዩን አይቼ አለቀስኩ ካሁን በኋላ ሃገሬን አላይም” ብሎ ከመጨነቀን እና ከመተከዝ ያረፈበትን ጊዜ አላስታውሰውም፡፡ የህመም ስሜት እየተሰማው እንደሆነ ሲነግረን ስለምትጨነቅ ነው ነገሮችን አምነህ መቀበል አለብህ እያልን እናጽናናው ነበር፤ ቅሉ ሚሊ በድጋሚ እስከመጨረሻው ለሃገሩ እንደማይበቃ ያወቀው ይመስል የሃገሩን ሰማይ እያየ እንዳለቀሰ እያለቀስን በሳጥን ልንሸኝው እየተዘጋጀን ነው ….

የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የዛሬው ፍርድ ቤት ውሎ

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ።

ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ።

በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል።

በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።


ማህበረቅዱሳንን ለማፍረስ ከመነሳት በፊት የራሳቸውን ካድሬያዊ ጵጵስና ያፍርሱ !!!

ጳጳሳት ከመንግስታት ጋር ተዋህደው ህዝብን ከማስጨቆን ውጪ እንደማህበረ ቅዱሳን በጎ የሆነ ስራ አልሰሩም።

ከአሁን ቀደም ለዜጎች የማይበጁ የሃይማኖት መሪዎች ለሼጎች የማይበጁ ከሆነ ቆባቸውን እንዲያወልቁ ተናግሬ ነበር። (http://minilik-salsawi.blogspot.com/2014/06/blog-post_18.html) ወደደም ጠላም ቄስም ሆነ ጳጳስ እያንዳንዱ በመንፈሳዊም ይሁን በስጋዊ ሕይወቱ እመራዋለው የሚለውን ምእመን ሁሉ የማገልገል ግዴታ አለበት። ይህ ካልሆነ የማይገባ አንቱታ የስድብ ያህል ይቆጠራል ነውና የሚሰራቸውን እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ይነገርዋል።

ባለፈው እንደ መግቢያ የተተቀምኩትን ለመጥቀስ ያህል ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች  አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

በዚህ ሰሞን ከበፊት ጀምሮ እየተቀጣጠለ የመጣ እና የተጋጋለ የማህበረ

የህግ የበላይነት፣ የፓለቲካ ምህዳር እና ሰብአዊ መብት – የጸረ ሽብር ህጉ ሲገመገም

“ጋዜጠኝነትን እና የፖለቲካ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ የሀገሪቱንና የሕዝቦቿን ሰላም ለማደፍረስ ከሚያስቡና ከሚፈልጉ ‘ሀይላት’ ጋር ግንኙነት በማድረግ የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል።“

ይህ መግለጫ (መልስ) የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ከወጣበት ከነሀሴ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዜጠኞችና በሰላማዊ መንገድ ተመዝግበው የፖለቲካ ምህዳሩን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከታሰሩ በኋላ በመንግስት አካላት የሚሰጥ የተለመደ አባባል ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥም ከጋዜጠኛ እስከ ፖለቲከኛ (political personalities)፣ ከሀይማኖት መሪዎች እስከ ጦማሪያን፣ ከታጣቂ ወታደሮች እስከ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች… በዚሁ አዋጅ አማካኝነት ‘ሽብርተኝነታቸው ተረጋግጦላቸዋል’ ወይም ‘ይረጋገጥባቸው ዘንድ ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ።’ ለመሆኑ ይህ ከ14 ዓመት ህፃን[1]  እስከ 80 ዓመት አዛውንት[2]  በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የሚያስቀጣው፣ ይህ ከጉምቱ ምሁራን እስከ ገበሬዎች ድረስ የሚያስረው… ሕግ በተጨባጭ ስፋትና ጥበቱ ምን ያህል ይሆን? ለታሪካዊ ጥያቄዎች ያለው ምልከታስ?  በሀገሪቱ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታስ (The state of Democracy) ምን ይነግረናል? ስለ ጨቅላው የኢትዮጵያ ፌደራሊዝምስ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ተግባራዊነት አንፃር ምን ይታየናል? ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በመሬት ላይ ያሉ የሕጉ እውነታዎችን በመመርመር (Fact investigation) ምልከታዎቹን (Implications) በዚህ ፅሁፍ ለማየት ሞክረናል።

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ አልሸባብ ጥቃት ሊያደርስ ነውና ራሳችሁን ጠብቁ ሲል አስጠነቀቀ።

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ አልሸባብ ጥቃት ሊያደርስ ነውና ራሳችሁን ጠብቁ…ዩኤስ ኢምባሲ በመቅረብ ራሳችሁን ባሉት መረጃዎች ላይ አፕዴት አድርጉ… ሲል ጥሪውን አቀረበ፡፡

በርከት ብሎ ሰው ከሚገኝባቸው አካባቢዎች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያዊያንና ምዕራባዊያን ከሚበዙባቸው አካባቢዎች ራሳችሁንም አርቁ ሲል ያሳስባል፡፡ ኢምባሲው እንደሚለው ከአልሸባብ ደረሰኝ ያለው መልዕክት እንደሚያሳየው ቦሌ አካባቢ ኢላማው እንደሆነ ነው የገለፀው ብሏል፡፡ ሆቴሎች ባሮች ስብሰባና ወርክሾፕ ቦታዎች፣ ሱፐርማርኬትስ እና የገበያ አዳራሾችና ትልልቅ ሱቆች ኢላማ መሆናቸውንም አስገንዝቧል፡፡
ሽብሩ ሊፈፀም እንደሚችል እርግጠኛ ባንሆንም ስጋት ውስጥ ማስገባት የሚችል ደረጃ ላይ በመሆኑ ራሳችሁን ጠብቁ ይላል ኢምባሲው ባወጣው ጥሪ፡፡ እኔ ህሊና ደሞ እላላው መንግስታችንየሚያሸብረን ይበቃል፡፡ አሜሪካ ለዜጎቿ ስታስብ እኛም ለኢትዮጵያዊያን እና ሁሉም ስዎች እናስባለንና እባካችሁን ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም አፍሪካ በዚህ እመጣለው ብሎ በዚያ ነውና የሚመጣ አልሸባብ በቦሌ እመጣለው ያለ ሊያደናግር ሊሆን ስለሚችል ቦሌ እመጣለው ካለ መርካቶ ሊሆን ስለሚችል ታርጌቱ መርካቶዎችና ሌሎች አካባቢም ራሳችሁን ጠብቁ ነው መልዕክቴ፡፡
አሜሪካን ግን ታዘብኩሽ ልክስክስ ነገር ነሽ ለራስሽ ዜጋ ስታግዥ እኔም ለወገኖቼ ጥሪውን አስተላልፋለው የሚሰጎድ መሪ ብናጣም ቅሉ፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም አዲስ አበባዎች ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊያን ጥቃቱ ምናልባት የሚደርስ ከሆነ ሊደርስ ስለሚችል ራሳችሁን አንቁና ጠብቁ ምናልባትም ጥቃቱን የሚያደርሰውም ማን እንደሆነ ስላልተለየ ላለመድረሱ ምንም ዋስትና የለንምና፡፡


Emergency Message for U.S. Citizens: Addis Ababa (Ethiopia), Potential of an Imminent Terrorist Attack in Addis Ababa, Bole Area Terrorism

The U.S. Embassy advises U.S. citizens in Addis Ababa to avoid large crowds and places where both Ethiopians and westerners frequent. The Embassy has received threat reports of al-Shabaab’s intent to target the Bole area. Restaurants, hotels, bars, places of worship, supermarkets, and shopping malls in the Bole Area should be avoided until further notice because they are possible targets for a potential imminent terrorist attack. While the exact location of this planned terrorist attack is not known, U.S. citizens should continue to maintain heightened personal security awareness.

We strongly recommend that U.S. citizens traveling to or residing in Ethiopia enroll in the Department of State’s Smart Traveler Enrollment Program (STEP). STEP enrollment gives you the latest security updates, and makes it easier for the U.S. embassy or nearest U.S. consulate to contact you in an emergency. If you don’t have Internet access, enroll directly with the nearest U.S. embassy or consulate.

Regularly monitor the State Department’s website, where you can find current Travel Warnings, Travel Alerts, and the Worldwide Caution. Read the Country Specific Information for Ethiopia. For additional information, refer to the “Traveler’s Checklist” on the State Department’s website.

Contact the U.S. embassy or consulate for up-to-date information on travel restrictions. You can also call 1-888-407-4747 toll-free in the United States and Canada or 1-202-501-4444 from other countries. These numbers are available from 8:00 a.m. to 8:00 p.m. Eastern Time, Monday through Friday (except U.S. federal holidays). Follow us onTwitter and Facebook to have travel information at your fingertips.

The U.S. Embassy in Addis Ababa is located at Entoto Street, P.O. Box 1014. The Consular Section of the Embassy may be reached by telephone: +251-111-306-130 or e-mail at consacs@state.gov, and is open Monday-Thursday, 7:30 a.m.-5:00 p.m. For after-hours emergencies, U.S. citizens should call +251-111-306-911 or 011-130-6000 and ask to speak with the duty officer.


Tuesday, October 14, 2014

Ana Gomez faults the British on Andargachew Tsige case

Member of the European Parliament Ana Gomez blamed London for being soft on Ethiopia and, in particular, for the extradition of British national Andargachew Tsege.

The MP made the remarks in an EU Parliament subcommittee hearing that focused on Andargachew Tsege, who was second-in-command of the rebel group Ginbot 7. The man was detained on June 23 at Sana’a international airport, Yemen, when he was transiting to Eritrea, and subsequently extradited to Ethiopia.

Andargachew’s detention became public knowledge after a week, when his group issued a statement. Another week passed before Ethiopia confirmedthat the Yemenis extradited him, while the Yemeni are silent to date.

ተመስገን ደሳለኝንም አሰሩት

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ። ተመስገን ደሳለኝ ከትላንት ጀምሮ፤ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የታሰረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በተከሰሰበት እና ፍርድ ቤት ሲመላለስባቸው በነበሩት ክሶች ነው አሁን ለእስር የበቃው።

ጋዜጠኛ ተመስገንን ለክስ ካበቁት ጽሁፎች መካከል፤ “መጅሊሱ፣ ሲኖዶሱና የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ማጥመቂያዎች”፣ “የፈራ ይመለስ” እና “የብሄረሰቦች መብት እስከ መጨፈር” በሚል ርእስ የጻፋቸው ጽሁፎች ናቸው። ሁሉም ጽሁፎች አሁን እንዳይታተም በታገደው ፍትህ ጋዜጣ ላይ የወጡ ነበሩ።  በነዚህ ጽሁፎች ምክንያት አቃቤ ህጉ የክሱን ጭብጥ የመሰረተው፤ መንግስትን በአመፅ ለመናድ ቀስቅሷል፣ የመንግስትን ስም አጥፍቷል፣ የህዝብን አስተሳሰብ አናውጧል፤ በሚል ሲሆን ጽሁፎቹም ሆኑ ክሱ ሁለት አመታትን አስቆጥሯል።

በእነዚህ ክሶች ምክንያት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት በቀጠሮ ሲመላለስ ቆይቶ፤ ትላንትና ግን ፍርድ ቤቱ በተመስገን ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፏል። በመሆኑም ጋዜጠኛ ተመስገን በ እስር ላይ ቆይቶ የቅጣት ውሳኔውን ከ2 ሳምንታት በኋላ ማለትም ጥቅምት 17፣ 2007 በፍርድ ቤት ተገኝቶ እንዲያዳምጥ ውሳኔ ተሰጥቷል። በመሆኑም ጥቅምት 17 ቀን ከታሰረበት መጥቶ፤ ለምን ያህል ተጨማሪ አመታት እንደሚታሰር በንባብ ተነግሮት ወደ ወህኒ እንዲወርድ ይደረጋል ማለት ነው።

በሸኮ መዠንገር ታጣቂዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከ50 በላይ የፌደራልና የመከላከያ አባላት ተገደሉ

ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና
ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመዶቻቸው ሲሸኙ፣ የቀሪዎቹ የቀብር ስነስርዓት ደግሞ ሚዛን ውስጥ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል።
በአዲስ አበባ የፖሊስ ሆስፒታል ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ በርካታ አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ የገባ ሲሆን፣ በመዠንገሮች የተገደሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

በሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባይቻልም፣ በዛሬው እለት መንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው በመላክ ጥቃት መፈጸሙንና ብዙዎችን መግደሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ከብሄረሰቡ ውጭ ያሉ ሰፋሪ ነዋሪዎች በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ቀያቸውን እየለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹም ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።

በፌደራል ፖሊሶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በሚዛን አማን ሆስፒታልተገኝቶ የተመለከተ አንድ ወጣት፣ ሁኔታው አስከፊና አስፈሪ መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል በአካባቢው ያለው የኢሳት ወኪል እንደገለጸው 18 የፌደራል ፖሊስ አስከሬን መቁጠሩን ተናግሯል። መንግስት ታንኮችንና ከባድ መሳሪያዎችን ማጓጓዙን ገልጾ፣ የሸኮ መዠንገር ተወላጆች ሚዛን ከተማ ድረስ በመምጣት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ
ወረቀት መበተናቸውንም ተናግሯል።በርካታ ቁጥር ያላቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያን በሚዛን ከተማ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩና እስካሁን እርዳታ ያደረገላቸው ድርጅት አለመኖሩንም ገልጿል።

መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። ከዚህ ቀደም በቴፒና ሜጤ በሚባሉት አካባቢዎች የነበረው ግጭት ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ መሸጋገሩን እና የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው መሰማራቱን መዘገባችን ይታወሳል።
መስከረም አንድ በነበረው ግጭት መንግስት ከ 13 ያላነሱ ዜጎች መገደላቸውን ሲገልጽ፣ የአይን እማኞች የተገደሉትን ዜጎች ቁጥር ከ50 በላይ ያደርሱታል።


Monday, October 13, 2014

አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡

አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡ አርብ ዕለት እንደጉርጎሪያን አቆጣጠር ጥቅምት 10 በሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የዳብሊው ሆቴል በዲሞክራቲክ ናሽናል ኮሚቴ /ዲኤንሲ/ አማካኝነት የተደረገለትን ግብዣ አጋጣሚ በመጠቀም ከፕሬዘዳንቱ ጋር አንድን ስብሰባ የተከታተሉ ሲሆን እንደሚሰጥ ቃል በገባው ለፕሬዘዳንቱም በተወካያቸው አማካኝነት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡
አበበም በዕለቱ ባስተላለፈው መልዕክት ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ሰፊውን ህዝብ እና የተከበረችውን ሃገራችን ኢትዮጵያን ድምፅ ማሰማት አለብን ብሏል፡፡ የምዕራባዊያን ሃገራት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አምባገነን መንግስታትን እንደሚረዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እና ፖሊሲና ስትራቴጅዎቻቸውን እንዲከልሱ እንዲሁም ከሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አለመጠበቅ ጋር በቀጥታ ማያያዝ እንደሚገባቸው በሁሉም አጋጣሚዎች ማሳወቅ ይገባልም ተብሏል፡፡


ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸው ታወቀ

ተቃውሞ አስነስተዋል የተባሉት ተማሪዎች ታስረዋል
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ታውቋል፡፡
ስልጠናውን አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱ ሲሆን መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረው የውሎ አበል አይከፈላችሁም በመባላቸው በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ተማሪዎቹ አበሉ አይከፈላችሁም ቢባሉም አሰልጣኞቻቸው ‹‹ገንዘቡ መጥቷል፡፡ አንከፍልም የሚሉት ዝም ብለው ነው›› ማለታቸው ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ገፋፍቷል ተብሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሴት ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ የከለከለ ሲሆን ወንድ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ መደብደባቸውንና መታሰራቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የደኢህዴን 22 አመት ምስረታን ተከትሎ በሀዋሳ በርከት ያለ ፌደራል ፖሊስ እንደነበርና ተማሪዎቹ አበላቸው እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ወቅት ‹‹ከተማው ውስጥ ፌደራል ሞልቷል፡፡ እናስደበደባችኋለን›› እያሉ ያስፈራሯቸው እንደነበር ታውቋል፡፡


የፈራ ይመለስ! (ከተመስገን ደሳለኝ)

በ2004 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ፣ ‹‹የፈራ ይመለስ!›› በሚል ተመሳሳይ ርዕስ፣ ከሰላማዊ አብዮት ውጪ አማራጭ ካለመኖሩም ባለፈ፣ ኢህአዴግ ቢያንስ ሕገ-መንግስታዊ ጥበቃ ላላቸው ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት አቅምም ፍላጎትም እንደሌለውለመሞገት ሞክሬ ነበር፡፡ ግና፣ አገዛዙ ለእንዲህ ያሉ ግዴታዎች የተዘጋጀ ባለመሆኑ ከማድመጥ-መዳ–መጥን፤ ከመመከር-መከራን፤ ከማሰብ-ቃሊቲ መሰብሰብን፤ ከመሻሻል-ከሀገር ማሸሽን፤ ከማመን-መርገጥን… በመምረጡ፤ ዛሬም ድረስ ነፃነት ናፋቂው ዘመነኛ ትውልድ፣ በፀጥታ አርምሞ ወደተዋጡት አደባባዮች ከማማተር ያለፈ አማራጭ እንዳያገኝ ገፊ-ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ያንን ጽሑፉም ከዓመት ከስድስት ወር በላይ ፍርድ ቤት ከምመላለስባቸው ክሶች የአንዱ መወንጀያ አድርጎ በተከበረችዋ ፍትሕ እየተሳለቀባት ነው፡፡ በርግጥ ጉዳዩ ገና እልባት ያላገኘ በመሆኑ፣ በዚህ ተጠየቅ አናነሳውም፡፡
ያ ጽሑፍ የታተመባት ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ የስርዓቱ ቅጥ ያጣ አፈና ሰለባ የመሆኗን ጉዳይ ግን ሁሌም ስናወሳው እንኖራለን፤ ምክንያቱም የ‹‹ቅድመ-ምርመራ›› (ሳንሱር) ግብአተ-መሬት በግላጭ በሕገ-መንግስቱ ሳይቀር ከታወጀ ሃያ ዓመት ባስቆጠረበት ኢህአዴጋዊ ዘመን የተፈፀመ ታላቅ መብት ረገጣ ነውና፤ ያውም ተራ የወሮበሎች ረገጣ መሆኑን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ፡፡ በመንግስታዊው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ለዚሁ ሕገ-ወጥ ተግባር አድፍጠው እንዲጠብቁ የተመደቡ ‹ግልገል› ካድሬዎች ጋዜጣዋ የምትታተምበትን ሐሙስ ቀንን በዝምታ አሳልፈው ነገር ግን ድንገት በዕለተ አርብ ማለዳ ‹‹ይህንን ዜና ማውጣት አትችሉም! ቆርጣችሁ አውጡ›› ማለታቸው ነው፤ ምን ዋጋ አለው ትዕዛዛቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ውጪ የተደረገበትን፣ 30 ሺህ የጋዜጣዋ ህትመት እንዲቃጠል በፍርድ ቤቱ አማካኝነት በጭካኔ በየኑ፤ ‹‹ፍትሕ››ንም በሕገ-ወጥ መንገድ ዳግም እንዳትታተም አገዱ፤ ይህ ሁሉ ከሆነ እነሆ ሃያ ወራት ተቆጥሯል፡፡ ግና፣ የተከፈለው ሁሉ ስለነገ የተሻለች ኢትዮጵያ ሲባል ነውና ባለፈ ጉዳይ ማለቃቀሱን እዚሁ ገታ አድርገን፣ ኩነቱንም ከነጋዴነት ለተሻገሩ ታሪክ ጸሐፊዎች ትተን፣ በአዲስ መስመር ወደ አጀንዳችን እንለፍ፡፡

Sunday, October 12, 2014

”የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” -ማኅበረ ቅዱሳን

“ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ…በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል ትን.ዕንባ.3፡17-19″ አትም ኢሜይል

በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡

ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?

አቶ በላይ ፍቃዱ አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት ሆኑ፤ ኢንጂንር ግዛቸው በፍቃዳቸው ለቀቁ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አቶ በላይ ፍቃደን የድርጅቱ ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል።

ከሰባት ወራት በፊት ድርጅቱን እንዲመሩ የተመረጡት ኢንጂነር ግዛቸው ፣ “ወጣቶችን ወደ አመራር አመጣለሁ፣ ወጣቶችን ባካችሁ አቅማችሁን አጎልብቱና ተኩኝ” በማለት ለወጣት አመራሮች ሃላፊነታቸውን ለማስረክብ ፍላጎት እንደነበራቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ቃላቸውን በመጠበቅ አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት መምጣታቸው ትግሉን ይረዳል የሚል እምነት ስላደረባቸው ኢንጂነር ግዛቸው፣ በፍቃዳቸው ሃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው ነው፣ በድርጅቱ ሕገ ደንብ መሰረት፣ ብሄራዊ ምክር ቤቱ አዲስ አመራር የመርጠው።

አቶ በላይ ፍቃደ የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የሰሩ፣ በድርጅቱና አባልትና አገር ዉስጥም ሆነ ከውጭ ባሉ ደጋፊዎች ዘንድ፣ ከመኢአድ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ ፣ ከትብብር …እንዲሁም ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት እንዳላቸው ይነገርላቸውል።


በቤንች ማጅ ዞን ጉራፋርዳ ወርዳ ወያኔ አሰልጥኖ ባሰማራቸው የአካባቢው ታጣቂዎች የተጀመረው የአማራው እልቂት ተባብሶ ቀጥሏል

በቤንች ማጅ ዞን ጉራፋርዳ ወርዳ የአማራው እልቂት ቀጥሏል
ወደ ሀገራችሁ ሂዱ እሄ የኛ ሀገር ነው በሚል ወያኔ አሰልጥኖ ባሰማራቸው የአካባቢው ታጣቂዎች የተጀመረው እና ትናንት ከጥዋቱ 12 ሳሀት ጀምሮ የ25 ንፁሀንን ህይወት የቀጠፈው እረብሻ ቀጥሎ ዛሬም ሌሊቱን ሙሉ በተደረገ የቤት ለቤት ግድያ ሌሎች 4 ሰወች ተገድለው ፤ አንድ የ3 አመት ህፃን ከናቱ ተነጥቆ ተወስዷል : ትናንት በእረብሻው በጥይት ከተመቱት 11 ሰወች ውስጥ አቶ አሰፋ ቢለው የተባለው እና አቶ ስማቸው ካሳ ህክምና ባለማግኘታቸው ዛሬ ህይወታቸው አልፋል ።

በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ መንግስት እየተከተለ ያለው ዘርን ማእከል ያደረገ ፖሊሲ ለግጭቱ ዋናው መንስኤ ቢሆንም፣ በአካባቢው የሚታየው የመሬት ቅርምት ግጭቱ በማየሉ፣ በተለይ ሴቶችና ህጻናት አካባቢውን እየለቀቁ በመሰደድ ላይ ሲሆኑ፣ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ መኪኖች ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱ ወደ ሌሎች ከተሞች ይዛመታል በሚል በፍርሃት መዋጣቸውን ተናግረዋል::


Saturday, October 11, 2014

ማህበረቅዱሳንን ለማፍረስ ከመነሳት በፊት የራሳቸውን ካድሬያዊ ጵጵስና ያፍርሱ !!!

ወደደም ጠላም ቄስም ሆነ ጳጳስ እያንዳንዱ በመንፈሳዊም ይሁን በስጋዊ ሕይወቱ እመራዋለው የሚለውን ምእመን ሁሉ የማገልገል ግዴታ አለበት። ይህ ካልሆነ የማይገባ አንቱታ የስድብ ያህል ይቆጠራል ነውና የሚሰራቸውን እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ይነገርዋል።

ባለፈው እንደ መግቢያ የተተቀምኩትን ለመጥቀስ ያህል ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች  አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

በዚህ ሰሞን ከበፊት ጀምሮ እየተቀጣጠለ የመጣ እና የተጋጋለ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ቤተክህነትን ሲያምስ ሰንብቷል። እያመሰም ነው። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የማይደሉትን እና የተማሩ ሰዎች ስብስብ የሆኑትን ቡድኖች ባገኘበት ሁሉ እየፈረጀ መበተን ከተያያዘ 20 አመታት አስቆጠረ፤ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ማስፋፋት ስም ከዘመተባቸው ማህበራት አንዱ እና ንብረቱን ወርሶ ለመቅበር ካሰፈሰበት ማህበር ዋነኛው እና በመንፈሳዊ አገልግሎት ታላቅ አስታውጾ ያበረከተው ማህበረቅዱሳን ተጠቃሽ እና የዚህ ሳምንት በስፋት ተዘምቶበት ይገኛል።

ማህበረ ቅዱሳን ባለፉት አመታቶቹ በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ሃገራት በመዘዋወር በተለያየ መስኩ ዘር ቀለም እና ሃይማኖት ሳይለይ በስፋት ኢትዮጵያውያንን በመርዳት የልማት አስታውጾ በማበርከት መንፈሳዊነትን በማስረጽ እና በማስተማር ወዘተ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታሪክ ውስጥ በጉልህ ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የሆነ አስታውጾ አበርክቷል። ማህበረ ቅዱሳን ነዳያንን ከመርዳት አንስቶ እስከ ማቋቛም አስተምሮ ለወግ ማእረግ እስከማብቃት ድረስ ለውገን እና ለሃገር ተቃሚ ተግባራትን አበርክቷል። (ድህረገጹን http://eotcmk.org/site/ መጎብኘት ይቻላል)

የኢሕአዴግ መንግስት እና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ጳጳሳት ሲኖዶሱን በመጠምዘዝ ማህበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ለማገድ ያደረጉት ሙከራ ይሁንታ በማጣቱ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል።በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስጋት ጨምሯል። ስብሰባ ማብዛት መፍትሄ አልሆነም።

☞ «ተቃዋሚዎች ተንሰራርተዋል… ሕዝቡ እንዳይውጠን መጠንቀቅ አለብን»
☞ የተጀመረው ትግል ፍሬያማነቱ እየታየ ስለሆነ ተቃዋሚዎች እና ሕዝቡ በንቃት በጋራ መሳተፍ አለባቸው።
☞ የባለስልጣናቱ ተስፋ እየተመናመነ ስለሆነ ሕዝቡ ትግሉን ማጠናከር ይጠበቅበታል።
የወያኔ ባለስልጣናት በስልጣን የመቆየት ፍላጎታቸው ላይ የተደነቀረው የህዝብ አቤቱታ እና የተቃዋሚዎች መንሰራራት ስጋት እንደሆነባቸው ታውቋል። ህዝቡ በጎሪጥ እያየን ያለበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች አንድ እርከን አንሰራርተው መታየታቸው እንዲሁም ዲያስፖራው ጥርሱን ነቅሶ በነቂስ እየተቃወማቸው እንደሆነ ከዚህም በተጨማሪ ስልጠና ብለው በጠሩበት ቦታ ላይ ሁሉ የደረሰባቸው ተቃውሞ ሕዝባዊ ጥያቄ እና አስተያየት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተወያይተዋል።
እንደ አዲሱ ለገሰ እምነት የተቃዋሚዎች መንሰራራት እና የህዝቡ ጥያቄ መፍትሄ ካልተፈለገለት በስተቀር እንደበሰበስን ማወቅ አለብን። በአሁን ወቅት እያየነው ያለነው ነገር ሕዝቡ ምን ያህል እንደተንገሸገሸ እና በጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደከተተን ከስልጠናዎች የሚመጡ ሪፖርቶች ብቻ በቂ ናቸው። ከየቦታው በየጊዜው የሚሰበሰበው ሪፖርት ከታየ ከዚህ በበለጠ ምን ያህል በስብሰን ልንወድቅ እንደቀረብን ያሳያል። ብለዋል የኢህአዴግ የጀርባ አጥንቶች የሚባሉ አንጋፋ እና ታማኝ የሚባሉ ታጋዮች በተሰባሰቡበት ስብሰባ ውይይት ላይ። ህዝቡ ሊውጠን ይችላል ስልጠናዎች ላይ የታዩ ሂድቶች ይህንን አመላካች ናቸው። ብለዋል።
በተቃዋሚ ሃይሎች ውስጥ የመደብናቸው ሰዎቻችን ስጋት ላይ ናቸው። ምንም አይነት መረጃዎችን ይዘው አይመጡም ፍሬ ከርስኪ ወሬ ነው የሚያወሩት የሕወሓት ሰዎችን እንዳንመድብ ሕዝቡ በትግሬዎች ላይ ያለው ጥርጣሬ በፍጹም እንዳይተነፍስ ሆኗል። የምንከፍላቸው የተቃዋሚ አመራሮችን ከሃገር የሚወጡበት መንገድ ከማመቻቸት ውጪ ምንም ሲፈይዱ አላየንም። ከወጡ በኋላ የተለያዩ መረጃዎች እያፈተለኩ ያሉበት ሁኔት እየታየ ነው። የገዛናቸው ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ በዘረፋ ተክነው ከሃገር ውጪ እየሸሹ ስለሆነ ሕዝቡ እንዳያበላሸን መጠንቀቅ አለብን ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ጸጋዬ በርሄ ተናግረዋል።
ወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በውጥረት እና በስጋት ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች ስርአቱ እንደበሰበሰ እና በጉልበት እንዲሁም በምእራባውያን ሃይል እየኖረ እንዳለ ተነጋግረውበታል። የምእራባውያን ድጋፍ ጥሩ ያለ ቢሆንም እያበሰበሰን እና እየገደለን ነው ያሉት ባለስልጣናት በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ከፊል ገደብ እንዲጣል ተስማምተዋል። ከመጀመሪያው የትኛውን መብት ለፖለቲካ ድርጅቶች እንደሰጡ እንኳን ያልተረዱት ባለስልጣናት ፓርቲዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው ሳለ ከፊል ገደብ እንጥላለን ማለታቸው ባዶነታቸውን በገሃድ ያመላክታል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ኢሕአዴግ እንደበሰበሰ በይፋ ያመኑት አቶ አዲሱ ለገሰ እና አቶ ጸጋዬ በርሄ በንግግራቸው ውስጥ ስለመጭው ጊዜ ከባድ ፍርሃት ይነበብባቸው ነበር ሲሉ የገለጹት ምንጮች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጀመሩትን ትግል አጠናክረው ከቀጠሉ ኢሕአዴግ ምንም አይነት ተስፋ እንደሌለው እና ምእራባውያንም ቢሆን የተቃዋሚዎችን ጥንካሬ እና በትግሉ መግፋት ካዩ ወደ ተቃዋሚው ጎራ የማይገለበጡበት አንዳችም ምክንያት የለም ሲሉ ምንጮቹ ኢህአዴግም ቢሆን ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።


አቡነ ማቴዎስ ፓትርያርኩን ተቃወሙ፤ “አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት” አሏቸው

ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ: ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከቅ/ሲኖዶሱ ያጡትን ይኹንታ በአቋራጭ ለማግኘት ‘በመልካም አስተዳደር’ ስም የጠሩትን ስብሰባ ተቃወሙ!‹‹ባላወጣነውና ባላጸደቅነው ሕግ ማኅበራትን መፈረጅና ሕገ ወጥ ማለት አንችልም፡፡››
‹‹አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት፡፡››
‹‹ከአለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ የተደረገው ውይይት አባቶች የተዘለፉበትና ያዘኑበት ነው፡፡››
‹‹ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን!!››
/ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/በአዲስ አበባ ታትሞ ዛሬ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበውበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተጠርቶ መስከረም ፳፯ እና ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የተካሔደው ስብሰባ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ኹኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን ያልጠበቀ እና ጽ/ቤታቸው የማያውቀው መኾኑን በመግለጽ ተቃወሙ፡፡የመ/ፓ/ጠቅ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ ከትላንት በስቲያ በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ የግማሽ ቀን ስብሰባ በተደረገበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመግቢያ ንግግር ተከትለው ቅድሚያውን በመውሰድ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ ‹‹አኹን ወደ ስብሰባው ስገባ ነው መልእክቱን የሰማኹት፤ አጀንዳውም ከመቅረቡ በፊት ከቋሚ ሲኖዶሱ ወይም ከእኔ ጋራ ምክክር አልተደረገበትም፤›› በማለት ስብሰባው መዋቅሩን ሳይጠብቅና ከዕውቅናቸው ውጭ የተጠራ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አስተላልፎታል በተባለው የቃል

Friday, October 10, 2014

ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል በቃ ብለን አሁኑኑ ለትግል እንነሳ!

በዳንኤል በቀለ* (ከኖርዌ)

ወያኔ የጥቂት ባለሃብቶችን እና የታማኝ ካድሬዎችን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ብሎም የስልጣን ላይ ቆይታቸውን ለማርዘም የዋሁን እና ምስኪኑን የኦሮሞ ገበሬ ያለምንም ተተኪ ቦታ እና ያለምንም የካሳ ክፍያ ከመሬቱ ላይ እያፈናቀሉ ለረሃብ እና ለስደት እንዲሁም ኩሩው የኦሮሞ ህዝብ በታሪኩ አይቶት ለማያውቀው ለልመናና ለተለያዩ ችግሮች እየዳረጉት ይገኛሉ። በኦሮሞነታቸው በሚያነሱት የነፃነት ጥያቄ በወያኔ እስር ቤት በግፍ የታጎሩ የኦሮሞ ልጆች ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ ነው – በብዙ ሺዎች እንደሚቆጠር ይታወቃል። በየቦታው ባሉ የወያኔ እስር ቤቶች ዋናው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ እስከ መሆን የደረሰበት ሁኔታ እንዳለ ብዙ ጥናት ያደረጉ የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አመላክተዋል። የአንድ ብሄር ዝርያዎች ብቻ በስልጣን ላይ መቀመጥና መግዛት የሌሎች ብሄሮች በህይወትና በሞት መሃል ተገዝቶ መኖር የኦሮሞ ህዝቦች ደግሞ እያጣጣሩ እንኴን እንዳይኖሩ በሚደረግበትና የወያኔ የእስር ቤት ቋንቌ ኦሮምኛ በሆነበት በዚህ ወቅት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር አለን ብለው በውሸት ህዝብንና አለምን ለማታለል መሞከር ገዢው ወያኔ በፍፁም ዲሞክራሲን በስም እንጂ በተግባር የማያውቅ መሆኑን ለተመለከተው ሰው ሁሉ ግልፅ ነው። በየትኛው ዲሞክራሲ በሰፈነበት አገር ነው አንድ መንግስት ራሴን እችላለሁ፤ አስተዳድራለሁ፤ በቅኝ ግዛት መተዳደር በቃኝ ያለን ህዝብ እኔ አውቅልሃለው በማለት በግፍ የሚገዛው። በፍጹም! ይህ አምባገነናዊ የቀኝ ግዛት የወያኔ መንግስት ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል።

ነዋሪዎች የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት ተቃወሙ

ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በአዲስአበባ ባለፈው ዓመት
22ሺ ያህል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 22ሺ ያህል ቤቶች ቀደም ሲል ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች መተላለፉን አስተዳደሩ ይፋ ከማድረጉም በላይ አንዳንድ ግለሰቦች የቤቶቹን ቁልፍ ሲረከቡም በዕለቱ ታይተው ነበር፡፡
ነገር ግን 22ሺ የተባሉት ቤቶች ዕድለኞቹ በቴሌቭዥን ከማየታቸው በስተቀር አስካሁን ሊረከቡ እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
በየክፍለከተማው ቤቶች ማስተላለፊያ ጽ/ቤት ሄደው ሲጠይቁ «ገና ነው፤ ደውለን እንጠራችሁዋለን» የሚል ተመሳሳይ መልስ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
የቤቶቹ ዕጣ ከደረሳቸው በኃላ በህዳር ወር 2006 ዓ.ም ከንግድ ባንክ ጋር የብድር ውል መፈጸማቸውን፣ በውሉ መሰረት ከአንድ ዓመት እፎይታ በሃሁላ የባንክ ዕዳ መክፈል ግዴታቸው መሆኑንና ቤቶቹን ተረክበው ከኪራይ ቤት
ባልተላቀቁበት ሁኔታ ወደባንክ ዕዳ ክፍያ መሸጋገር እጅግ ከባድና የማይቻል በመሆኑ ሁኔታው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ የደረሳቸውን ሐሰተኛ ሪፖርት መሰረት አድርገው 22ሺ ቤቶች ተላልፈዋል ሲሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ መዋሸታቸው የአገዛዙን ይሉኝታ ያጣ ያልተገባ ባህርይ ያሳያል ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ለተፈጠረው ችግርና መስተጓጎል የኢትዮጵን ሕዝብ በነግግራቸው ይቅርታ መጠየቃቸው አግባብ ቢሆንም ኪሳራው ግን በይቅርታ ብቻ የሚታለፍ
እንዳልሆነ ያነጋገርናቸው የአዲስአበባ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ኤሌክትሪክ ኃይል ተርፎን ለጎረቤት ሀገር ጭምር ለመሸጥ ችለናል የሚል መንግስት አንዳንዴ በቀን ውስጥ እስከሶስት ጊዜ በተደጋጋሚ ኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንደሚያጋጥም የገለጹት አስተያየት ሰጪ፣ አንድ ነዋሪ ይህ ደግሞ
የዜጎችን ገቢ ከመጉዳቱም ባሻገር እንደባንክ፣ ቴሌ ፣አየር መንገድ የመሳሰሉ ከኔትወርክና ኢንትርኔት ጋር የተያያዙ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ስራ የሚፈቱባቸው ጊዜያት እየተበራከቱ እንዲመጣ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ በተለይ እየተስፋፋ ነው በሚባለው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳረፍ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑ መካድ አይቻልም ሲሉ አስረድተዋል፡፡ «ባንክ ቤቶች ሄደህ ተመልከት፡፡ ሰዎች
እንደዳቦ ሰልፍ ቁጭ ብለው ከአሁን አሁን መብራት መጥቶና ኔትወርኩ ተስተካክሎ አገልግሎት እናገኛለን ብለው ተኮልኩለው ሲጠብቁ ታገኛለህ፡፡
አንዳንዴ መብራቱ መጥቶ ኔትወርኩ እምቢ ካለ ቀኑን ሙሉ ተጎልተህ ውለህ ብር ሳታገኝ ወደቤትህ ልትሄድ ትችላለህ፡፡ ይህ ዓይነቱን ቀውስና ኪሳራ ምን ዓይነት ይቅርታ ይተካዋል” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላው አስተያየት ሰጪ ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው የመብራት መቆራረጥ አንዱ ምክንያት የመልካም አስተዳደር ችግር ነው ማለታቸውን አስታውሶ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር ካለ ችግሩን መፍታት፤ ካልተቻለ ለሚችል ኃይል
ስልጣን መልቀቅ እንጂ ዕድሜ ዘላለም ሰበብ እየደረደሩ ለመቀጠል መሞከር ሕዝብን መናቅ ነው ብለዋል፡፡


ማተቤን አልበጥስም

በአንድ ወቅት በጨካኝነቱ ተወዳዳሪ ያልነበረው የታላቋ ሩስያ መሪ የነበረው ስታሊን በአገዛዝ ዘመኑ የሩስያ ኦርቶዶቶዶክስን ለማጥፋት ያልወሰደው አረመኔአዊ ድርጊት አልነበረም ። ከእነዚህም መካከል የቤተክርስቲያኒቱን አማኞች በጥይት መግደሉ ጥይት ማባከን ነው ብሎ በማሰቡ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አራስ ህፃናት ድረስ ያሉትን ኦርቶዶክሳውያን በግዙፍ መርከቦች እየጫነ ውቅያኖስ ውስጥ በመጨመር ለአሳነባሪዎች ቀለብ እስከማድረግ ደረሰ ። ይህን የመሰለው ግፍ ግን ኦርቶዶክሳውያኑን ከማጥፋት ይልቅ ይበልጥ ሃይማኖታቸውን እንዲያጠብቁ አደረጋቸው ። እንዲያውም በሩሲያ ታሪክ እንደዚያን ዘመን የኦርቶዶክሳውያን አማኞች ቁጥር በዝቶ የታየበት ዘመን እንደሌለ የታሪክ ፀሐፊዎች ይናገራሉ ።

የሁኔታውን አደገኛነት የተገነዘበው ስታሊን ፓርላማውን ሰበሰበና እንዲህ አለ ።” ጓዶች ይሄ አካሄዳችን አላማረኝም ከሃይማኖቱ ሰባኪዎች ይልቅ የእኛ ግድያ የሩስያ ኦርቶዶክስን እያለመለመ እና እያጠነከረ ይገኛል። እናም ግድያው ይቁም ። ምክንያቱም ከዚህ አይነቱ አካሄዳችን የተማርኩት ነገር ቢኖር ክርስቲያን እና ምስማር በመቱት ቁጥር እየጠበቀ መሄዱን” ነው ብሎ የሩሲያን ኦርቶዶክስ ማጥፋት ድክም ብሎት አቆመ ይባላል ።

በጉራፈርዳ ወረዳ 25 አማሮች መገደላቸው ተሰማ

በደቡብ ክልል በቤንች ማጅዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የመዠንግር እና የሸኮ ተወላጆች አንድላይ በማበር የአማረኛ ተናጋሪዎችን እየጨፈጨፉ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።



(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በስፍራው ይኖሩ የነበሩት እነዚሁ አማሮች ቤት ንብረታቸውን ለቀው ወደ አካባቢው ከተሞች እየተሰደዱ ሲሆን እስካሁንም እየተፈጸሙ ባሉ ጭፍጨፋዎች 25 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።



በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ እነዚህን ዜጎች የጨፈጨፉት የመዠንገርና የሸኮ ተወላጆች አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን መያዛቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ዘጋቢዎች ይህ መሳሪያ ለደቡብ ሱዳን ተብሎ የመጣ እንደሆነና ከጭፍጨፋው በስተጀርባ የመንግስት እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር የሚያሳይ ነው ሲሉ በአካባቢው ጥቃት የደረሰባቸውን አማሮች አስተያየት በመጥቀስ ዘግበዋል።

በጉራፈርዳ በተፈጠረው ጭፍጨፋ በአካባቢው ያሉ የመንግስት ወታደሮች ከመዠንገር እና ከሸኮ ተወላጆች ጋር መተባበራቸውን የሚገልጹት እነዚሁ የጥቃት ሰለባዎች ሆን ተብሎ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት እየተደረገ ያለ ሴራ ነው ይሉታል። በጉራፈርዳ መሬታችንን ለቃችሁ ውጡ በሚል እንዲህ ያለው ጭፍጨፋ ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑ ይታወሳል።


‘አሸባሪ ብዕሮች’ (ክንፉ አሰፋ)

ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።መብትን ማወቅ እና ማሳወቅ፤ ‘ህዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ማድረግ፤ ወይንም በስራዓቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር  ነው’ ተብሎ ከተተረጎመ ደግሞ ጋዜጠኛን በአሸባሪነት መፈረጁ ብዙ ሊደንቀን አይገባም።ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት-አመታት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በቁጥር አንደኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሃገር ናት።  አሁን ይህንን ደረጃዋን ለቃለች። እድገትና  ትራንስፎርሜሽኑን ተከትሎ ከመጡት ለውጦች አንደኛው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የአንደኝነት ደረጃዋን ያጣችው ታዲያ ትራንስፎርሜሽኑ ይዞት በመጣው መሻሻል አይደለም።  ነጻ ፕሬሱ ከሃገሪቱ እንዲጠፋ በተደረገ ሁለገብ ጦርነት እንጂ። አብዛኛው ጋዜጠኛ ተሰድዷል፣ ጥቂቶቹ ታስረዋል፣  አንዳንዶቹም  አቅማቸው ተሟጦ አልቆ፤ ዝም ብለው እንዲቀመጡ ተደርገዋል።  ለነጋሪ የተረፉትንም እስከዛሬዋ እለት ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ።ከጅምሩ በፕሬሱ ላይ የተከፈተው የገዥው ፓርቲ ውግያ ቀላል አልነበረም። ፕሬሱ ግን እለት ተዕለት የሚያርፍበትን የአንባገነኖች ጡጫ ሁሉ ችሎ ብዙ ተጉዟል። እየተንገዳገደ፤ እየወደቀና እየተነሳ የህዝቡን የህሊና ንቃት እንዲሰፋ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዲዳብር ነጻው ፕሬስ ተግቶ ሰርቷል።   የህትመት ዋጋ እስከ 500% እንዲጨምር ቢደረግም ፕሬሱ አልቆመም ነበር። ጋዜጠኞች እንደጥጃ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣  እየተሰቃዩም  ስራቸውን ላለማቋረጥ መትጋታቸውን አላቆሙም። በካድሬ ዳኞች ፍርደ-ገምድል ፍትህ ሲሰጣቸው፤  ያለ አግባብ በእስርና በገንዘብ ሲቀጡም ሰ

ሰበር ዜና ማኅበረ ቅዱሳን ሠይጣን አምላኪ በሆነው ወያኔ ታገደ

ማኅበረ ቅዱሳን ታገደ፣የማህበሩ አባላት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ዕጣ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት የለቀቁት በ ወያኔ የደህንነት ኃይሎች በደረሰባቸው ማስፈራራት ነው ተባለ። ማተብ በጥሱም የሚል አዋጅም በ ወያኔ ታውጁዋል።
በወያኔው ፓትርያርክ አቶ ማትያስ ፊታውራሪነት ከተለያየ አድባራት እና ገዳማት የመጡት ጥቂት በጥቅም የተገዙ የደብር አለቆች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ሃላፊዎች፣የ አዲስ አበባ ሀገረስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተብሎ በወያኔ የተሾመው ኦህዴድን ወክሎ ወያኔ ፓርላማ ተመራጭ የሆነው አቶ በላይ መኮንን፣ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራውና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ መዝገበ ጥበብ ቀሲስ ዮሐንስ ኤልያስ፣ኤልያስ አብርሃ እንዲሁም ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ ያሉበት ቡድን ከ ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ጋር በመሆን ባቀነባበሩት ክስ ማህበሩን ወደ ማገድ እና በ አሸባሪነት የማስወገዝ ደረጃ ተሸጋግረዋል ።

የጎዳና ላይ ነውጥ ለማነሣሣት ሁከትና ብጥብጥ የሚሰብኩና የሁከትና ብጥብጥ መንገድን የሚቀይሱ ግለሰቦችና ቡድኖች የተሰባሰቡበት ነው በሚል የሀሰት ክስ የመታገድ እርምጃ የተወሰደበት ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ያወጣው ምንም አይነት መግለጫ የለም። የማህበሩ የጂማ ንዑስ ማዕከል እና የዋናው ማእከል አንዳንድ አመራሮች እና አባላት ባለፉት ሁለት ቀናት በወያኔ የ ፅጥታ ኃይሎች ማዋከብ እና ፍተሻ እየተካሂደባቸው ቢሆንም ምንም አይነት መረጃ ለሚድያ እንዳይሰጡ በማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ እንደተነገራቸው ለማወቅ ተችሉዋል ። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢወች ማህበሩ ለ ቤተ-ክርስቲያኒቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ቢሆነም የማህበሩ ጥቂት አመራሮች ግን ከወያኔ ጋር በመተባበር አሁን በ ወያኔ የተሾሙተን አቶ ማትያስ ከማስመረጥ ጀምሮ ከበስደት ሀገር ከሚገኘው በብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ከሚመራው ሕጋዊው ሲኖዶስ ጋር ይደረግ የነበረውን የአባቶችን የእርቅ ውይይት እስከ ማስተጉዋጎል ድረስ አፍራሽ ሚና ይጫወት እንደነበር አስታውሰዋል ። በአሁኑ ሰዓት ወያኔ በሀገራቺን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ፅዋውን ሞልቶ እየፈሰስ ይገኛል ። በ ወንዶምቻችን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ያደረገውን የሐሰት ክስ አሁንም በማህበረ ቅዱሳን ላይ ሊደግመው ዝግጅቱን አጠናቆ ይገኛል ።


የጎዛምን ወረዳ የሰማያዊ አመራሮች በገዥው ፓርቲ አፈና እየተደረገባቸው መሆኑን አስታወቁ

‹‹ወጣትና አርሶ አደሩ ‹‹ለምን ከሰማያዊ አባላት ጋር ታወራላችሁ እየተባለ ይታሰራል››በምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ በአባሊባኖስ ቀበሌ የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ አመራሮችና አባላት፣ ‹‹ለምን የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆናችሁ?›› በሚል ከፍተኛ አፈና እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
የወረዳው የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ አክሊሉ ውቤ፣ ወጣት ምህረት እንየውና አቶ አንመው ይዘንጋው ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የወረዳና የቀበሌ ባለስልጣናት የሰማያዊ አመራሮችን ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲወጡ እንደሚያስገድዷቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ አንመው ይዘዘው የተባለውን የፓርቲው አባል መስከረም 14/2007 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ሚሊሻ ጥሩነህ መኮንን፣ ሚልሻ ሽታሁን ዘውዴ፣ ሚሊሻ አበባየሁ አባተ አስገድደው ወደ ቀበሌው ቢሮ በመውሰድ የቀበሌው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በልስቲ ትዛዜ ከሰማያዊ ፓርቲ ካልወጣ እንደሚገረፍ፣ ካልሆነ አገር ጥሎ መሰደድ እንዳለበት እንደዛቱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡የቀበሌው ሊቀመንበር ‹‹ኢህአዴግ በ1997 ምርጫ ቢሸነፍም ሰራዊቱም፣ ወታደሩም፣ ፖሊሱም፣ የኛ ነው፣ እናንተ ወረቀትና እስክርቢቶ ይዛችሁ ልታሸንፉ አትችሉም፤ አሁንም እርምጃ እንወስድባችኋለን›› በሚል እንደዛቱበትና ከፓርቲው እንዲወጣ እንዳስጠነቀቁት ገልጾአል፡፡በተመሳሳይ አቶ አክሊሉ ውቤ የተባሉትን ግለሰብ ‹‹ቢያርፍ ይረፍ ከፖለቲካ ድርጅት መውጣት አለበት፣ ካላረፈ ለህይወቱ ያሰጋዋል›› በሚል የቀበሌው ሹም የሆኑት አቶ ገነነ እና አቶ በልስቲ ትዕዛዜ እንደዛቱባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ምህረቱ ይታየው የተባለው ወጣትም ተመሳሳይ ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል፡፡በሌላ በኩል አቶ በልስቲ ትዕዛዜ፣ ኮማንደር አንተነህ ፈንታሁን፣ አቶ ተሻገር አዲሱ የተባሉት የቀበሌው ባለስልጣናት ‹‹ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለምን ታወራላችሁ፣ ለምን ከእነሱ ጋር ትቆማላችሁ›› በሚል በየዕለቱ ወጣቱንና አርሶ አደሩን እንደሚያስሩ የወረዳው የፓርቲው ቅርንጫፍ አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ አክለው ገልጸዋል፡፡የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በከፈተባቸው ቦታዎች ቢሮዎችን ለመዝጋት፣ ቢሮ ለመክፈት እየጣረ በሚገኝባቸው ቦታዎች ደግሞ አባላቱንና አመራሮቹ ከፓርቲው እንዲወጡ ጫና እያደረገ እንደሚገኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Thursday, October 9, 2014

ማህበረ-ቅዱሳን አደጋ አንዣቦበታል

ኢሳት ዜና :-‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››ሲሉ የኢትዮፐያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተናሩ።

ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህን ያሉት ፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ

የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ የሆነ መዋቅር ያላት ቢሆንም፤ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራት፣ ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ በመንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት ያከማቹና እያከማቹ

መሆናቸውን የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠራቸው ከሆነ አሸባሪ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ ነው ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ፓትርያርኩ በዚሁ ንግግራቸው በቤተ ክርስቲያን ስም ለሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የቤተክርስቲያኗ ልጆች ከቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀ ሀብትና ንብረት ማካበት የተከለከለና

በከባድ ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ ድርጊት እየተስፋፋ ነው፡ያሉት ፓትርያርኩ፣ እየታየ ያለው የማኅበራት ዝንባሌ ሀብት ማካበት፣ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተፈቀደውን ‹‹አሥራት በኩራት››

ለራሳቸው መሰብሰብ፣ ከቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ የአገር ውስጥና የውጭ ሥራዎችን በሌላቸው ሥልጣን መሥራት- መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ፓትርያርኩ አክለውም፦” ማኅበራቱ በሰበሰቡት ሕገወጥ ሀብት አባቶችን ይከፋፍላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ያሾማሉ፣ ያሽራሉ፡፡ የእነሱን ፍላጎት የማይፈጽሙትን ያስፈራራሉ፣ አካሄዳቸው ለቤተ ክርስቲያኗ ጥንካሬና

ህልውና ፍጹም አደጋ ሆኗል”ብለዋል። ፓትርያርኩ በዚሁ ንግግራቸው -በአድባራትና ገዳማት የመልካም አስተዳደር እጦት መንገሡንና ባለፉት አሥርት ዓመታት የምዕመናን ቁጥር መቀነሱንም አመልክተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለማኅበራት በጎ ያልሆነ አሠራርንሲናገሩ ‹‹ማኅበራት›› እያሉ በወል ስም ከመጥራት ባለፈ የማህበራት ስም ባይጠቅሱም፣ በስብሰባው ላይ የነበሩ ከገዳማትና ከአድባራት የተወከሉ

አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ግን ያስገነባውን ሕንፃ ጭምር እየገለጹ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን በመጥቀስ በማህበሩ ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ መጠይቃቸውን የጋዜጣው ዘገባ አመልክቷል።

የቤተ ክርስቲያኗ ማንኛውም ገቢ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር በአንድ ቋት ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት እንዲመራ ያሣሰቡት አንዳንድ የጉባዔው ተሳታፊዎች፤ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቀድሞ ቤታቸው

ይመለሱ ሲሉ ተናግረዋል።


የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በሦስት አሳታሚ ድርጅቶች መሪዎች ላይ የእስራት ቅጣት በየነ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በሦስት አሳታሚ ድርጅቶች መሪዎች ላይ የእስራት ፍርድ በየነ።

የፌዴራል አቃቤ ሕግ ዩፋ ኢንተርቴይንመንትና የፕሬስ ሥራዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ዳዲሞስ ኢንተርቴይንመንትና ሮዝ አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተሰኙ ድርጅቶችና በዋና ስራ አስኪያጆቻቸው ፋጡማ ኑርዬ፣ አቶ ግዛዉ ታዬ ኦርዶፋና አቶ እንዳልካቸዉ አድጉ ላይ ባቀረበዉ ክስ መሰረት፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት “ጥፋተኛ” ናቸው ሲል ወስኖባቸዋል። ሶስቱም ተከሳሾች ቀደም ብሎ አገር ጥለው የኮበለሉ ሲሆን፤ የእስራት ቅጣቱ የተፈረደባቸው በሌሉበት ነው።

ዛሬ በዋለዉ ችሎት ፍርድ ቤቱ በእያንዳንዳንዱ ተከሳሽ ላይ ከ3 አመት ከ3 ወራት እስከ 3 ዓመት ከ11 ወራት የሚደርስ እስራት ፈርዷል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የዳዲሞስ ኢንተርቴይንመንት እና የፕሬስ ዉጤቶች ሚዲያ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ድርሻ በስልክ በሰጡን ቃል ፍርድ ቤቱ የወሰደዉ እርምጃ የጠበቅነዉ ነዉ ብለዋል። ዝርዝሩን ከዘገባዉ ያድምጡ።


አቶ በረከት ስምኦን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችን ማሰልጠናቸውን ቀጥለዋል

ኢሳት ዜና :-በመላው አገሪቱ ለሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለኢህአዴግ አባላት የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና የዩኒቨርስቲ መምህራንም እንዲወስዱ በመገደዳቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን በቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር እና በአሁኑ የጠ/ሚ የፖሊሲ አማካሪ በአቶ በረከት ስምኦን እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው።
ስልጠናውን የሚወስዱት በታሪክ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣ በሶሺኦሎጂ፣ በጆግራፊ፣ በፊዚክስ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች የፕሮፌሰርነት ማእረግ ያገኙ፣ የተለያዩ ጥናታዊ ምርምሮችን የሰሩና በሙያው የዶክትሬት ተማሪዎችን ሳይቀር የሚያስተምሩ ናቸው።
ኢሳት ውይይቱን በርቀት በመከታተል ለመረዳት እንደቻለው አቶ በረከት በፌደራሊዝም፣ በታሪክ፣ በሃይማኖትና በኢኮኖሚ ጥያቄዎች ዙሪያ ለአስተማሪዎች ስልጠና ሰጥተዋል።
“ማለባበስ የማይቻለው የብሄረሰቦች ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው፣ ሚዲያው በወቅቱ ባይነግረንም ከተፈታ በሁዋላ ‘ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በሽማግሌ፣ በክልሉ የጸጥታ ሃይሎች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በመጨረሻም በመከላከያ ጥረት ሊፈታ ችሎአል’ ይባላል።

ጃዋሪዝም (የማምታታት ፖለቲካ) – በጌታቸው ሽፈራው (የግል አስተያየት)

‹(ጠባብ) ብሄርተኝነት ልክ እንደ ርካሽ መጠጥ ነው፡፡ መጀመሪያ እንድትጠጣው ይገፋህና ያሰክርሃል፡፡ ቀጥሎ አይንህን ያውርሃል፡፡ ከዛም ይገድልሃል፡፡›› ዳን ፍሪድ

በጌታቸው ሺፈራው

(የግል አስተያየት)

ጃዋር መሃመድ ከአመታት በፊት ከማደንቃቸው ኢትዮጵያዊ አክቲቪስቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በተለይ ይህ ወጣት ከጥቂት አመታት በፊት እነ በረከት ስምኦንን አልጀዚራ ላይ ሲያፋጥጣቸው ሳይ አድናቆቴ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጃዋር ወደ ሶማሊያ ዘው ብሎ ስለገባው ሰራዊት፣ ቋንቋ ሳይለይ በየትኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰውን በደል ሽንጡን ገትሮ መከራከሩ ይታወሳል፡፡ ግን ምን ያደርጋል ይህ አቋሙ እንደተጠበቀው ሊዘልቅ አልቻለም፡፡ መሃል ላይ የ‹‹እኛ እና እነሱ›› ብልሹ ፖለቲካ ሰለባ ሆነ፡፡

በተለይ በአንድ ወቅት አልጀዚራ ላይ ቀርቦ ‹‹በቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ›› ካለ በኋላ የፖለቲካ አቋሙ እየተንሸራተተ ሜንጫን እንደ ህጋዊ ነገር ማንሳት ውስጥ ገባ፡፡ አንዴ ‹‹ኢትዮጵያዊ ሙስሊም›› ሆኖ የኦሮሞ ሙስሊሞች ነጻነት ለሌላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ነጻነትም ወሳኝ ነው ሲል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኑን ኦሮሞ በሜንጫ አንገቱን ስለመቅላት ይሰብካል፡፡ (ይህን መረጃ የተቀነባበረ ነው የሚል መረጃ ያቅርብ)፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ክርስቲያኑን ኦሮምኛ ተናጋሪም ጭምር ወክሎ ‹‹ቅድሙያ ኦሮሞ ነኝ›› አለ፡፡

ጋጠ ወጡ ማን ነው?

የህወሃት ጉጅሌና ሎሌዎቹ መቼም ራሳቸውን የሚያይ አይንም መስታዎትም ያላቸው አይመስሉም። ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው የዘሩ የማይመስሉት ለዚህ ሳይሆን ይቀራል። ምናልባትም ብልግና፣ ጭካኔ፣ ግፍ፣ አውሪያዊ ስብእና፣ ወገን ካለህግ መግደልና ማዋረድ፣ የህዝብ ሃብት በጠራራ ጸሃይ መዝረፍ ለእነሱ የተፈቀደና የተሰጠ ጸጋ አድርገው ሳይቆጥሩት ይቀራሉ?ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰለጠነና የዳበረ ስርዓት አከባበር በሰፈነበት ከተማ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ በመዋላቸው ለደረሰባቸው ትዝብት የነውረኝነት ሀፍረት እንደማፈር ሰላማዊዎቹንና በሰላማዊ መንገድ እስከ ሲቪላዊ አልታዘዝም ባይነት መብት ያላቸውን ጠንቅቀው አወቀው የተንቀሳቀሱትን ዜጎች ጋጠ ወጥና ባለጌዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ትንሽ ሲቀዠብርባቸው ደግሞ ኦባማ ስላነጋገረን የቀኑ ተቃዋሚዎች፣ ይህ አልበቃ ሲል ደግሞ የሻእቢያ ተላላኪዎች ሲሉም ተደምጠዋል። ከአውሬነት ብዙ ያልተለዩት ደጋፊዎቻቸው ተኩሱን ሲያንጣጣ የነበረው የቀድሞ የስዩም መስፍን የግል አሽከርና ሹፌር የነበረው ወዲ ወይኒ ግደይ ስለተባረረ ንዴታቸውን ከአደባባይ እንኳን መደበቅ አልቻሉም። እናስ እዚህ ውስጥ ጋጠወጡ ማነው? ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን አራዊታዊና ህግ አልባ ስርአት በሰለጠነ ህዝብ ሀገር በአደባባይ ለኤግዚብሽን የሚያቀርብ መደዴ ወይስ እስከ ሲቪል እምቢተኝነት ድረስ ሊደርስ የሚችል መብታቸውን ጥንቅቀው የሚያውቁና በግፍ ስርአት ለሚኖረው ወገናቸው ድምጽ ያሰሙ የህዝብ ልጆች?በዘሩ ታማኝነት ተመርጦ ከስዩም መስፍን ሾፌርነት ውጪ ቅንጣት የዲፕሎማሲ እውቀት የሌለውን ደንቆሮ የዲፕሎማት ማእረግና ሽጉጥ አስታጥቆ ዋሽንግተን ከሚልክ መንግስት በላይ ጋጠወጥና አጉራ ዘለል ከየት ይገኛል።እውነቱ ግን ወዲህ ነው ያለው። ቢያንስ በነጻው አለምየሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራቸውና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ስቃይ ውርደትና ግፍ ተንገፍግፈዋል። የወያኔ ሹማምንት ግፋቸውን እንዲያቆሙ ያሰሩዋቸውን እንዲፈቱና ሀገር ዝርፊያ እስኪያቆሙ ድረስ በገቡበት እየገባ ቁም ስቅላቸውን ማሳየትና ጋጠወጥና የነውረኛ ስርአት አገልጋዮች መሆናቸውን ማጋለጡን ይገፉበታል። በሰሩት ወንጀል አለምአቀፍ ፍርድቤቶች መድረክ ላይ እየጎተተ የሚያቀርብበት ጊዜም ሩቅ አይደለም።የወጋ ይርሳ እንደሆነ እንጂ የተወጋ አይረሳም። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሰላማዊ ተቃዋሚውን ድርጅት አባል በብረት ሶዶማዊ ምግባር የፈጸሙትን ጋጠ ወጥ የወያኔ ተላላኪዎች ማን ይረሳል። በየቤቱና በየጎዳናው በዱላ የሚቀጠቀጡትና ደማቸውን ሲጎርፍ ያየናቸው አዛውንት ሙስሊም ወገኖቻችን ደም እንዴት እንረሳለን። ሬሳቸው እንኳን ክብር አጥቶ የጋጠወጥ ወያኔ መጫወቻ የሆኑትን የኦጋዴን ወገኖቻችንን ማን ይረሳል። ጋምቤላ ጫካ ውስጥ እንደደኑ ተጨፍጭፈው የተቆለሉትን አኙዋኮች ማን ይረሳል። ከየኖሩበት ቦታ በግፍ እየተፈናቀሉ የሚንከራተቱትን እና የሚሞቱትን አማሮች ማን ይረሳል። በቆራጥነት ብቻ በሰላም መንገድ እንታገላለን ብለው በተነሱ ወህኒ የተወረወሩትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የታሰሩትንና የተሰደዱትን ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች የምንረሳቸው ስንሞት ብቻ ነው። ከየጎረቤት ሀገሩ እየታፈኑ የሚሰቃዩትን እነ አንዳርጋቸውን እና ሌሎች የሞቱትን ማን ይረሳል።ህዝባችንን ወደ ሰላማዊ አመጽም ሆነ ወታደራዊ አመጽ እየገፋው ያለው ይህ የወያኔ ባህሪ ነው።ግንቦት 7 ከዚህ አራዊታዊ ስርአት ጋር ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት በህዝባችሁ ስቃይ ላይ የምትተባበሩ ወገኖች ሁሉ በአገኛችሁት አጋጣሚ ከእዚህ እኩይ ስርአት ተግባራት ራሳችሁን እንድታወጡ፣ ከቻላችሁ በውስጥም ሆናችሁ ወገናችሁን ሳትበድሉ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ይመክራል።መላው ህዝባችን በያለህበት ራስህን በራስህ እያደራጀህ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎችን ጀምር። በመላው አለም ዙሪያ ተሰደህ የምትኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለወገንህ ለራስህም ትንሳኤ ተነስ!!ትግላችን የመጨረሻውን መጀመሪያ እየተያያዘ ነው። የትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝብ ባለቤቶች ስለሆንን ከወያኔ ወሮበላ ጉጅሌ በበለጠ የሚገባን ህዝብ ነን!!ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, October 8, 2014

ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ

“ድርጊቱ የሚፈጸመው በእንግሊዝ ዕርዳታ ነው” አሉ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በሥራ ጉዳይ እንግሊዝ አገር ተገኝተው የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሎንዶን የሚገኘው Minority Rights Group International ጽ/ቤት ባደረገላቸው ግብዣ ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡በቃለምልልሱ ወቅት ሁለተኛው የአፍሪካ የመሬት ነጠቃ እየተካሄደ እንደሆነ እና እንዲህ ዓይነቱ አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በእንግሊዝና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ዕርዳታና ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች መብት

Tuesday, October 7, 2014

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መንግስት በሚቀጥለው አመት በኤርትራ መንግስትና በተቃዋሚዎች ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል አሉ

ኢሳት ዜና :-
የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ለጀመሩት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ከኤርትራ
መንግስት ለሚሰነዘር ማንኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል። የኤርትራ መንግስት አስታጥቆ የላካቸውን የ ግንቦት7 ፣ ኦብነግና ኦነግ ጥቃቶችን መከላከላቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በዚህ አመትም ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
ዶ/ር ሙላቱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በዘረኝነትና በጥላቻ ተነሳሰስተው ተቃውሞ እንደሚያነሱም ገልጸዋል። መንግስት በአንድ በኩል ተቃዋሚዎች ጉልበት የላቸውም እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ጥቃታቸውን ሲመክት መቆየቱንና ተመሳሳይ እርምጃ በዚህ
አመትም እንደሚወስድ መግለጹ እርስ በርስ የሚቃረን መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ዶ/ር ሙላቱ መንግስት ለኤርትራ መንግስት ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄ ሲያቅርብ መቆየቱንም ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ችሎት ለኤርትራ መንግስት ሲሰልሉ ተገኝተዋል በተባሉ ሶስት ኢትዮጵያውያን ላይ እንዲከላከሉ ወስኗል። በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉለመዲ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ነጋሲ ብርሃነ ሹማይ፣ ተበጀ
በረኸ እና ብለጽ ገብረጻድቃን ዛላንበሳ ስለሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ለኤርትራ መረጃ ሰጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ግለሰቦቹ ከኤርትራ መንግስት ስልጠናና ገንዘብ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ውሳኔ አስተላልፏል።


Monday, October 6, 2014

ህወሃቶች “አቅም ግንባታ” የሚሉት፤ እኛ ደግሞ “አቅም አድክም” የምንለው ሂደት

ህወሃት የመምህራንን፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችንና የመንግስት ሠራተኞችን ”አቅም እገነባለው” ብሎ ተነስቷል። ለዚህ “አቅም ግንባታ” እያሉ ለሚጠሩት አሰለቺ እና አደንቋሪ አቅም አድክም ፕሮፖጋንዳ እየወጣ ያለው ወጪ ለሌላ ተግባር ውሎ ቢሆን ኑሮ የተሻለ ይሆን ነበር። የተሻለ ነገር በህወሃቶች መንደር ይሠራል ብሎ መጠበቅ ግን ሞኝነት ነው። ህወሃት የተፈጠረው አገርን ለማፍረሰና ህዝብን ለማስጨነቅ እንጂ የተሻለ ሥራ ሠርቶ ህዝብን ለማስደስት አይደለም።

ህወሃቶች በአፍቅሮተ ንዋይ አብደው አቅላቸውን የሳቱ፤ ለእውቀትና ከእነርሱ በተሻለ ደረጃ ለሚያውቅ ቅንጣትም ታክል ክብር የሌላቸው፤ ውሸት የመኖሪያቸው ድንኳን ሁኖ ለብዙ ዘመን ያኖራቸው ቡድኖች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን የገነቡ ቡድኖች የሌሎችን አቅም እንገነባለን ብለው የመነሳታቸው ነገር አገራችን የገባችበትን የውርደት አዘቀት ፍንትው አድርጎ የሚያሳየን ነው።

የአዜብ ዱላ በሰሎሞን አስመላሽ ላይ…

ከአርአያ ተስፋማሪያምጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። የ120 መዝናኛ አዘጋጅ ነበር። ከኢቲቪ ከወጣ በኋላ ሜጋ አመራ። (በ1989ዓ.ም ከሳምሶን ማሞ ጋር በታዋቂ አትሌት ላይ የሞከሩት የፔፕሲ ማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊት ነበር፤ ጉዳዩን ለጊዜው እንለፈው) የሜጋ ሃላፊዎች እግር ስር ወድቀው ከወጡ በኋላ ሰሎሞን አስመላሽ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ መስራት ቀጠለ። በአደባባይ የገዢው ፓርቲ ደጋፊና አቀንቃኝ መሆኑን የሚናገረው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ከአራት አመት በፊት በምሽት መዝናኛ ውስጥ መጠጥ እየተጐነጨ ነበር። በድንገት መብራት ድርግም ይላል።ሰሎሞን ጮክ ብሎ « አዜብ መስፍን ያስገባቸው ጄኔሬተር ተቸበቸበ! ሆን ተብሎ ነው መብራት የሚጠፋው..የአዜብን ጄኔረተር ለመሸጥ!» እያለ ተናገረ። በሚገርም ፍጥነት ይህቺ ቃል አዜብ መስፍን ጆሮ ደርሳለች። አዜብ ወዲያው በቀጭን ትእዛዝ ወደ መዝናኛው ደህንነቶች አዘመቱ። በዛው ሰሞን ሰሎሞን በውድ ዋጋ እጅግ ዘመናዊ አውቶሞቢል ሸምቶ ነበር። በስፍራው የደረሱት ደህንነቶች የመኪናዋን መስተዋት በመሰባበርና ጐማዎቿን በማስተንፈስ ተልእኳቸውን ጀመሩ። ሰሎሞን አስመላሽ ከመዝናኛው ሲወጣ አንድም የሰውነት አካሉ ሳይቀር በዱላ ቀጥቅጠው መንገድ ዳር ዘርረውት ሄዱ።አዜብ « እንዳትገድሉት ግን ሰባብራችሁ ጣሉት» በማለት አዘው ስለነበረ ያንን ደህንነቶቹ እንደፈፀሙ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋልጦዋል።…በነገራችን ላይ መስከረም 1 ቀን 1995ዓ.ም ፒያሳ ትግራይ ሆቴል በገዢዎቹ ተቀነባብሮ የተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱት 60 ንፁህ ሰዎች አንዱ የሰሎሞን አስመላሽ ታናሽ ወንድም ይገኝበታል። ይህ ዘግናኝ ድርጊት እንዴት እንደተፈፀመ ጋዜጠኛው ካወቀ በኋላ ሞቅ ሲለው ይናገር ነበር።..በ1990 ዓ.ም ሰሎሞን አስመላሽ እጅግ ውብ የሆነች ፍቅረኛውን ተነጥቋል። በአሜሪካ ትኖር የነበረችው ፍቅረኛውን አንድ ለባለሃብቱና ለገዢው ባለስልጣናት ቅርብ የሆነ ግልገል “ቱጃር” የግሉ አድርጓታል። .. ጋዜጠኛው አሁንም የገዢው ደጋፊ ነው።

Sunday, October 5, 2014

ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?

አገርና መሪ ላላቸው ኤምባሲ አገር ነው
ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ”ባንዲራ ቀን” በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ”ባንዲራ ክብር” ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል።ባድመ ስትወረር “ደርግ ኢሰፓ” ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ “እናት አገር ጥሪ” ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል ኪዳን ይኸው “አታስፈልግም ጨርቅ ነህ” የተባለው መለያ ነበር። ሲፈልጉ የሚጥሉት፣ ሲጨንቃቸው የሚያነሱት መከረኛ ባንዲራ ዳግም አጀንዳ ሆኖ ሰሞኑንን ቀርቦልናል።በአሜሪካ በሚገኘውና ኢህአዴግ “ኤምባሲ” በሚለው ቅጥር ግቢ ውስጥ ወዲ ወይኒ የሚባሉ ታጋይ የፈጸሙት ድርጊት ነው የባንዲራን ጉዳይ ዳግም አጀንዳ ያደረገው። የወዲ ወይኒ ገድለ ዜና አስገራሚ የሆነባቸው፣ ያሳዘናቸው፣ ያናደዳቸው፣ የተደፈርን ስሜት የፈጠረባቸው፣ ክስተቱን በመቃወም ኢህአዴግን በመወከል መግለጫ ያወጡ፣ እስከመቼ ኢህአዴግ “ሆደ ሰፊ ይሆናል” ብለው የጠየቁ፣ አሜሪካንን የወነጀሉ፣ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቁ፣

ሰልጣኙንም አሰልጣኙንም ያንገሸገሻቸዉ ሥልጠና

አባትና የ10ኛ ክፍል ተማሪ ልጁ አምርረዉ ሲጨቃጨቁ እናት ትደርስና . . . . እባክሽ ልጄ አባትሽ የሚልሽን ለምን አትሰሚም ብላ ልጇን ትቆጣታለች። ልጅት ከተቀመጠችበት ትነሳና ምነዉ እማዬ ምኑን ነዉ የምሰማዉ፤ አባዬኮ እሱ እራሱ የማያዉቀዉን ነገር ላሳይሽ እያለኝ ነዉ ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ በቁጣዉ ብዛት ፊቱ እንደ ፊኛ ያበጠዉ አበቷ ካንቺ ማወቅ ዬኔ አለማወቅ ይሻላል፤ ይልቅ የምልሽን ስሚ ብሎ ጮኸባት። ወጣቷ ተማሪ ወላጅ አበቷ ከስምንተኛ ክፍል በላይ ዘልቀዉ እንዳልተማሩ ብታዉቅም ለግዜዉ ማድረግ የምትችለዉ ምንም ነገር አልነበረምና እሽ አባዬ ብላ አባቷን መስማት ጀመረች። ይህ የአባትና የልጅ ስሚኝ አልሰማም ጭቅጭቅ ባለፉት ሁለት ወራት መሀይሞቹ የወያኔ ካድረዎችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየስልጠና አዳራሹ ያደረጉትን ፍጥጫ አስታወሰኝ። ይህ አብዛኛዉን ዕድሜያቸዉን ትምህርት በመማር በሳለፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በወጉ ስምንተኛ ክፍልን ባላጠናቀቁ የወያኔ ካድሬዎች መካከል በክረምቱ ወራት ተጀምሮ አሁን ድረስ የዘለቀዉ የ”አሰለጥናለሁ አታሰለጥንም” ትንግርታዊ ድራማ ወያኔ አስካሁን ከሰራቸዉ ድራማዎች በአይነቱ ለየት ያለ ድራማ ነዉ።የወያኔ ምርጫዎች ምንም አይነት ዉድድር የማይታይባቸዉ ማንም ተወዳደረ ማንም ወያኔ ብቻ የሚያሸንፍባቸዉና ምርጫዎቹ ከመካሄዳቸዉ በፊት የት ቦታ እነማን ማሸነፍ እንዳለበቸዉ ተወስኖ ያለቀላቸዉ የለበጣ ምርጫዎች ናቸዉ። ወያኔ ግን “ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል” እንደሚባለዉ ምርጫዉ በቀረበ ቁጥር የሚያክለፈልፍ በሽታ ይይዘዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1997ና በ2002 ዓም የተደረጉትን ምርጫዎችና እርግጠኞች ነን አሁንም በ2007 ዓም የሚደረገዉን ምርጫ የሚለያያቸዉ ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ ምርጫ መኸል የአምስት አመት ልዩነት መኖሩ ነዉ እንጂ የምርጫዉን ዝግጅት፤ ሂደትና ዉጤት በተመለከተ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የሚችል ልዩነት የለም። ሁሉም ምርጫዎች የሚካሄዱት ወያኔ የምርጫ ተቋሞች፤ ሜድያዉንና ፍርድ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠርበት ሁኔታ ዉስጥ ነዉ። በዚህ ላይ

ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!

ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡
‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡›› /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ/
* * *

‹‹ሚኒስትሩ የመንግሥትን ሴኩላርነት ለማረጋገጥ በሚል የሰጧቸው አስረጅዎች የግልጽነትም የአግባብነትም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚበዛው ኢትዮጵያዊ አማኝ ከመኾኑ አንፃር ትርጉም እንዳለውና በሕገ መንግሥቱ እምነት ነክ ድንጋጌዎች እንደተንጸባረቀ ከሚታመነው የሴኩላሪዝም ፈርጅ (positive secularism) ይልቅ በርእዮትና አሠራር የተደገፈ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን የማዳከም (negative secularism) አዝማሚያዎች ያይልባቸዋል፡፡ ከእምነት ተቋማት ጀርባ የግንባሩን አባላት ጨምሮ ሰፊው አማኝ ሕዝብ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ‘በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር’ እንደሚኖር በመንግሥት የኢንዶክትሪኔሽን ጽሑፎች ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ጋራም የሚጣጣሙ አይደሉም፡፡ በተለይ ከቤተ ክርስቲያናችን አንፃር ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የሚመስል ‘issue’ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ በዚኽ አኳኋን እንዴት ነው ዜጎች ‘ሚዛናዊ አስተሳሰብ’ እንዲያዳብሩ የሚጠበቀው? ከመንግሥት ጋራ አብሮ መሥራትስ እንዴት ይቻላል?››
‹‹ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚt

Saturday, October 4, 2014

በ46 አመቱ የህወሃት አገልጋይ እና የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ላይ የአሜሪካን መንግስት ክስ መሰረተበት

ቢል ሚለር የአሜሪካ ፍትህ አካል ቃላ አቃባይ የሆኑት ባለፈው ሰኞ በሰላማዊ ሰልፈኞች እና በኢትዮጵያ ኢምባሲ ዋሽንግተን ጽ/ቤት መካከል በነበረው ሂደት ላይ የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ሽጉጥ ተኩሶ የመግደል ሙከራ ማደርጉ ወንጀል መሆኑን አምነው ይህም የዲፕሎማቲክ ፈቃዱ ከክስ እንደማያድነው ተናገረዋል። በዚህ መሰረት የአሜሪካን መንግስት ፍትህ ጸ/ቤት ክሱን አዘጋጅቶል። ሰውየው ከሀገር ቢባረርም በሌለበት ሂደቱ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ሰለሞን ገ/ስላሴ ከዚህ በሆላ ጥፋተኛ ከተባለ ከ15 እስከ 20 አመት በሚደርስ የእስራት ቅጣት እንደሚጠብቀው የህግ ባለሙያዎች የተነተኑ ሲሆን ይሁን እንጂ ሰለሞን ወይም የኢትዮጵያ ኢምባሲ ይህን ሂደት ስለሚያውቁ ተጠርጣሪው ወደ አሜሪካ የመመለስ አጋጣሚን እንደማያደርግ ይታመናል።

ለህግ ባለሙያው; ከክስ ሂደቱ ማጠናቀቂያ በሆላ ውሳኔዉን ለማስፈጸም የአሜሪካን ሀገር ወንጀለኛውን ለመያዝ የማደኛ ትእዛዝ ሊያስተላልፍ ይችላል ወይ ብለን ላቀርብንላቸው ጥያቄ አሁን የሚወሰን ሳይሆን ወደፊት እንደወንጀሉ ክብደትና ቅለት የሚለካ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያው ለአባይ ሚዲያ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በእንደዚህ አይነት የቀለለ ወንጀል ሲገባ የመጀመሪያ ባይሆንም ይህ ለየት የሚያደርገው አምባሳደር ግርማ ብሩም የጉዳዩ ተዋናያን መሆናቸው እንዲሁም በርካታ የአለም ሚዲያዎች የዘገቡት መሆኑ ነው።

አምባሳደር ግርማ ሰሙኑን ከሬዲዮ ፋና ጋርና ከሌሎች የወያኔ ሚዲያዎች ጋር ባደረጉት ንግግራቸው ምንም አይነት ስለ ጠባቂው ሰለሞን የሰጡት ማስተባባያ የለም። በደፈናው የተቃዋሚ ቡድኖች በኤርትራ  ተደግፈው ያደረጉት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

ዘጋቢያችን በማጠቃለያው የኤርትራ መንግስት አሜሪካ ውስጥ ገብቶ ወያኔን ያስጭንቃል እንዴ? ምን አይነት አምባሳደር ይሁን ሀገሪቱ ይዛ ፕሮፖጋንዳ የምትሰራው ሲል ትዝብቱን በማከል ሪፖርቱን ለአባይ ሚዲያ ልኮልናል ።


አቶ አንዳርጋቸውን ለማስፈታት እንግሊዝ ለመንግስት መጮህ የዋህነት ነው::

ከቢላል አበጋዝ

ዋሽግተን ዲ ሲ

ለአጭር ግዜ ተጕዠ ካለሁት ቦታ ከመምጣቴ ቀደም ብሎ ከወድሞቼ አንዱ White Gold ትርጉም “ነጭ ወርቅ” የሚለውን በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሀፍ አውሶኝ ነበር:: ሙሉ ርእሱ “አስገራሚው የቶማስ ፔሎ ታሪክና የእስላም አንድ ሚሊዮን ባሮች። ደራሲው ጋይልስ ሚልቶን የተባለ እንግሊዛዊ ነው::

 የተሰኘው ታሪካዊ መጽሀፍ ቶማስ ፔሎ ይባል የነበር በአስራ አንድ ዓመቱ በባሪያ ፈንጋዮች ታግቶ ሞሮኮ ተዋስዶ ሃያ ሶስት ዓመታት በባርነት ኖሮ ለማምለጥ ችሎ አገሩ የተመሰ ንግሊዛዊ ታሪክ ነው።  ቶማስ ፔሎ የተያዘው 1716 ዓ መ፡እ አ አ በዚህ ዘመን አልጀርስ ቱኒስ ሞሮኮ የባርያ ንግድ ማከሎች ነበሩ። ላነዴም ለሁሌም ሰሜን አፍሪካውያኑ ባሪያ ፈንጋዮች የተሸነፉት በ 1816 እ አ አ ነበር።በሰሜን አፍሪካ ይገኙ የነበሩት እስላም ባሪያ ፈንጋዮች በባህር ላይ ውጊያ ያየሉ ነበሩ። የንግሊዝ፡ፈረንሳይ፡እስፓኝና ጣሊያን ዜጎች ተባህር ተይዘው በባርነት ከገበያ ላይ ለጨረታ ይቀርቡ ነበር:: ቶማስ ከአምሳ አንድ ወገኖቹ ጋር ከተያዘ በኋላ ለሞሮኮው ሱልጣን ሙሌይ እማኢል ይሸጣል። ሙሌይ እማኢል በባሮች ጉልበት ታላላቅ  ቤተመንገስታት ሰርቶ በሺ የሚቆጠሩ ቁባቶች የነበሩት ጨካኝና አረመኔ ነበር። ሌሎች በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያንም ባሮች ነበሩት። ቶማስ ፔሎ ቀልጣፋ ደፋርና ቆራጥ ነበር። በዚህም ሱልጣን ሙሌይ እማኢል የግል አገልጋይ ሆኖ በቤተ መንግስት ውስጥ ይሆን የነበረው ግፍ ለማየት ችሎአል። የሰቆቃ ታሪክ ነው። ባርነት ቆዳ ቀለም የማይል የኢኮኖሚ ስርዓት እንደነበ ለማሰተማር የሚረዳ መጽሀፍ ነው::

የሕዝብ ተስፋ የሆነው አንድነት ፓርቲ ትልቅ አደጋ ላይ ነው (አማኑኤል ዘሰላም)

ያለፈው የ2006 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ከዘጠና ሰባት አመት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ፣ ለሕዝቡ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ፣ ከፍተኛ አገር አቀፍና ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል። በባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በጊዶሌ፣ በጂንካ, በአርባ ምንጭ ፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በወላይታ ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍቼ በመሳስሉ ከተሞች የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ንቅናቄ ፣ ብዙዎችን ለትግሉ ለማነሳሳት የቻለ ሲሆን፣ የፓርቲው ተቀባይነት እጅግ በጣም ከፍተኛ እንዲሆንም አድርጎት ነበር።

ጠንካራ ፓርቲ እንዲኖር የማይፈልገው ሕወሃት/ኢሕአዴግ በፓርቲው ጠንካራ አመራር የሆኑትን በማሰር የአንድነት ፓርቲን እንቅስቃሴ ለመግታት መሞከሩ አልቀረም። እንደ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ ያሉ ወጣት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ክስ ሳይመሰርትባቸው በማእከላዊ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡

የአገዛዙ እኩይ ተግባር እንደተጠበቀ የአንድንት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፍፈራው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባላትን እና ደጋፊዎች አሰባስበው ትግሉን ከማስቀጠል ይልቅ፣ በአባላት ዘንድ መከፋፈሎች እንዲመጡ፣ ሊሰሩ የሚችሉ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሸሹ በማድረግ፣ አንድነት ፓርቲን ትልቅ አደጋ ላይ እየጣሉት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡።

የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሐሳብ አመንጪና በአባላትና ደጋፍፊዎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያለውን ፣ አቶ በላይ ፍቃዱን ጨምሮ፣ በርካታ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከኢንጂንር ግዛቸው ጋር ልንሰራ አንችልም በሚል ከሥራ አስፈጻሚ ሃላፊነታቸው የለቀቁ ሲሆን፣ በምክር ቤት አባልነት ብቻ ለፓርቲው የድርሻቸውን ለማበርከት ተወስነዋል።

ያለፈው ሰኔ 8 ቀን 2006 በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ፣ ተጠሪነቱ ለምክርር ቤቱ በሆነውና ሃብታሙ አያለው በሚሰበስበው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል አመራርነት ፣ ከተደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዉጭ ፣ ላለፉት ሶስት ወራት ከአሥራ አምስት ቀናት ምንም አይነት እንቅስቃሴ የአንድነት ፓርቲ ከማድረግ ተቆጥቧል። ፓርቲው እንደነ ዶር በየነ ፓርቲ በቢሮ ዉስጥ መገልጫዎችን በማወጣት ላይ ብቻ የተወሰነ ፓርቲ ሆኗል።

በቅርቡ የፓርቲዉን መፍዘዝ ያዩ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወጣቶች፣ ከሌሎች ድርጅቶች ወጣቶች ጋር በመመካከር ፣ የታሰሩ ወገኖችን ለማሰብ የሻማ ማብራት እና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች ቢጀምሩም፣ ኢንጂነር ግዛቸው ከኢሕአዴግ ጋር መጋጨት አያስፈልግም በሚል፣ መግለጫ በመስጠት ብቻ በመወሰናቸው፣ በርካታ ወጣቶችን ከማሳዘን አልፈው ተስፋ እያስቆረጡ ነው።

በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ያሉ በርካታ አባላት፣ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ በፓርቲው ዉስጥ ትልቅ አስተዋጾ አድርገው አሁን ከጀርባ ሆነው የሚያገለግሉ ወገኖች፣ ምሁራን፣ የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን ፣ የኢንጂነር ግዛቸው አመራር ስላሳሰባቸው ፣ ሕዝቡ ተስፋ የጣለበትን ፓርቲ ለማዳን ሲባል፣ ኢንጂነሩ እንዲለቁ መጠየቃቸውንም፣ አንዳንድ ዜናዎች ይጠቁማሉ። ከነዚህ የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ፣ ከኢንጂነር ግዛቸው ጋር አንድነት የመሰረቱትና ከኢንጂነሩ ጋር የብዙ አመታት የትግል አጋር የሆኑት ዶር ያእቆብ ወልደማሪያም፣ የተከበሩ አቶ ይልማ ይፍሩ፣ ዶር ዳኛቸው ይገኙበታል።

በዉጭ አገር የሚገኙም፣ አንድነት ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ፓርቲው ሲደገፉ የነበሩ፣ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች፣ የፓርቲው አቅጣጫ እንዳሳሰባቸው በመገልጽ ፣ አንድነት ከቢሮ ፖለቲካ ወጥተው ሕዝቡን ወደ ማንቀሳቅቀስ እንዲመለስ በማሳሰብ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በኢንጂነሩ አመራር ትግሉ ዉጤት ያመጣል ብለው እንደማያምኑም እየገለጹ ነው።

በቅርቡ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ግርማይ ግዛው፣ ለኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በላኩትና ለደጋፊዎች ግልባጭ ባደረጉት ደብዳቤያችው፣ ኢንጂነር ግዛቸው ለትግሉ ሲሉ ሃላፊነታቸው እንዲለቁና ፣ ሊሰሩ ለሚችሉ አዳዲስ አመራሮች እንዲያስረክቡ ተማጽነዋል።

“I plead with you for the sake of your legacy and honor as well as for UDJP, step down nowand with dignity, honor and the love of the country, please transfer your leadership for a new bread of leaders. You have many unchartered opportunities such as to be a member of the council of elders and advice and mentor many young leaders for years to come like Dr. Hailu Araya” ሲሉ ነበር አቶ ግርማይ ትልቅ ተማጽኖ ያቀረቡት።

ኢንጂነር ግዛችው በአስቸኳይ ከሃላፊነታቸው ተነስተው ፣ የፓርቲዉን አባላትና ደጋፊዎች በቶሎ በማሰባሰብ፣ ፓርቲው ሕዝቡን ወደ ማደራጀት ሥራ በቶሎ ካልተመለሰ፣ የአንድነት ፓርቲ ትልቅ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልም ይገመታል። በመሆኑም አባላትና ደጋፊዎች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለጽ፣ አቶ ግርማዬ ግዛዉ እንዳደረጉት፣ መልእክታችንን ለኢንጂነር ግዛቸው እናስተላልፍ። “ የወያኔ ተጠቃሚ እንደሆነው፣ በሕዝብ እንደቀለለው ፣ እንደ አየለ ጫሚሶ አይሁኑ። የዶር ኃይሉ አርአያ ፈልግ ተከትለ፣ ስምዎትን በክብር ቦታ ያስፍሩ እንበላቸው” ። አንድነት እንደ ዶር በየነ ፓርቲ፣ ሕዝባዊ ሳይሆን የግለሰቦች ፓርቲ ሆኖ እንዲቀር፣ እንዲሞት የማንፈልግ ከሆነ፣ አሁን ድምፃችንን እናሰማ። አንድነትን እናድን !!!


Friday, October 3, 2014

አንድ መምህር ጠንካራ ጥያቄዎችን ብቻ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን ገለጹ

ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ለመምህራን እየሰጠ ባለው የፖለቲካ ስልጠና ላይ የሚሳተፉት በወሊሶ ከተማ አስተማሪ የሆኑት ግለሰብ “ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን” ተከትሎ መታሰራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።
መምህሩ እንዳሉት ” የመንግስት ባለስልጣናት መሬት እየከፋፈሉ መሸጣቸውን አስመልክቶ ማስረጃ አቅርበው በመጠየቃቸው” ህዝብን “ልታነሳሳ ነው” በሚል ለአንድ ቀን ታስረው ” ሁለተኛ እንዳትናገር በሚል በማስጠንቀቂያ መፈታታቸውን ተናግረዋል።
ማስጠንቀቂያው ከተሰጣቸው በሁዋላ ጥያቄ መጠየቅ ማቆማቸውንም አክለው ገልጸዋል


የኢሕአፓ አባላት እና ደጋፊዎች በስቶክሆልም ከተማ የወያኔ ኤምባሲን ለተወሰነ ጊዜ ይዘው ቆዩ

ሰበር ዜና፡ በዛሬው ዕለት (ሴፕቴምበር 30 ቀን 2014) ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በስቶክሆልም ከተማ የወያኔ ኤምባሲን ለተወሰነ ጊዜ ይዘው ቆዩ። ተቃውሞውን ያዘጋጁት በኖርዌይ የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ፣ የሴቶች ክንፍ እና ደጋፊ ኮሚቴ ኣባላት መሆናቸውም ታውቋል። ወያኔ የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች አባላትን በሰበብ አስባቡ እየከሰሰም ቢሆን አስሮ እንደያዛቸው ሲያሳውቅ፣ ገና ከጠዋቱ የሚያራምደውን ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ሕዝብ አቋም በመቃወም የታገሉትን ፋና ወጊ የኢሕአፓ አመራሮችና አባላትን አፍኖ፣ አሁንም እያፈነ ዬት እንዳደረሳቸው አለመታወቁን በመቃወም ነበር ዝግጀቱ የተቀናበረው። ተቃዋሚዎቹ ኤምባሲው ውስጥ በመግባት የጓዶቻቸውን ደብዛ መጥፋት እና ሌሎችንም መሪ መፈክሮች ሲያስተጋቡ የወያኔው ኤምባሲ ሠራተኞች በድንጋጤና ፍርሃት ርደው ነበር። በሎሌነታቸው ሊያሳዩት የፈለጉት መኮፈስ ጥሏቸው ሄዶ መግቢያ ነው ያጡት። ተቃዋሚዎቹም አምባሳደር ተብዬዋ መጥታ ካላነጋገረችን እና ጌቶቿ ገዢዎች ''ጓዶቻችንን ዬት እንዳደረሱዋቸው ለጥያቄያችን መልስ ካልሰጠችን አንወጣም!'' ብለው ኤምባሲውን ለአንድ ሰዓት ይዘው ቆይተዋል። ሰሞኑን ወያኔ በዓባይ ግድብ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ ባዘጋጀውና አድር ባዩ ንዋይ ደበበ ባቀንቃኝነት በተገኘበት ጭፈራ ላይ የክብር ታዳሚ ለመሆን ስትመጣ፣ በኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በተወረወሩ ዕንቁላሎች ቀልቧ የተገፈፈው አምባሳደር ተብዬዋም የኢሕአፓ አባላት እና ደጋፊዎች ጥያቄን በተመለከተ ፊት ለፊት ለማነጋገር ድፍረቱን አላገኝችም። በፖሊሶቹም በኩል የኢትዮጵያዊያኑ ጥያቄ ቀርቦላት ''አሁን መልስ ልሰጥ አልችልም በቀጠሮ ካልሆነ'' ስላለች፣ ፖሊሶቹ ጉዳዩን ተከታትለው ለእናት ድርጅታቸው ለኢሕአፓ የክትትላቸውን ወጤት እንደሚያሳውቁ ቃል ገብተውላቸዋል። የተፈቀደው የተቃውሞ ሰዓት ሲያልቅም ኢትዮጵያውያኑ ወደሚኖሩበት ሀገር በሰላም ተመልሰዋል።


Thursday, October 2, 2014

የወያኔ አምባሳደር ግርማ ብሩ ኮከብ የለሽ ባንዲራን የሰቀሉትን ጋጣ ወጦች አላቸው

ኢትዮጵያዉያኖች በኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረጉት የተቃዉሞ ሰልፍ፣ ኮከብ ያለበትን የአገዛዙ ባንዲራ አንስተው፣ የጠራዉን የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ መትከላቸው ይታወቃል። መሳሪያ ያልታጠቁ፣ ወረቀትና ባንዲራ ብቻ በእጃችቸው የያዙ ሰላማዊ ዜጎች “ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንፈልጋለን፣ ወንጀለኞች አይደለንም” በሚሉበት ጊዜ፣ አንዱ የኤምባሲ ጠባቂ፣ ጥይት መደቀኑና ሶስት ጊዜ መተኮሱ፣ በኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሜዲያዎች ሁሉ በስፋት እየተዘገበ ነው።መሳሪያ ባልያዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት መደቀኑ ብዙዎችን እያስቆጣ ባለበት ወቅት፣ የአገዛዙ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ፣ ለኢትዮጵያ ፈርስት በሰጡት አስተያየት፣ ሠልፈኞቹን “ጋጣወጦች” ሲሏቸው፣ ጥየት የተኮሰዉን ግለሰብ ደግሞ “ስራውን በትክክል የሰራ” ሲሉ አሞግሰዉታል።በሰልፉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ላይ ክስ እንዲመሰረትና እርምጃ እንዲወሰድ ጠበቃዎች እንደሚቀጥሩ የገለጹት አቶ ግርማ ብሩ፣ “ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ የተናደዱ ናቸው” ሲሉም ከሰዋቸዋል። ከአሜሪካኖች ጋር በቅርበት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ እየተነጋገሩበት እንደሆነም የተናገሩት አቶ ግርማ፣ ሰልፈኞቹ ተቃዉሞ እንዲያሰሙ ስለገፋፋቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረገው ዜጎችን የማሽበር፣ የማሰር መረን የለቀቀ የሰባአዊ መብት ረገጣ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡
አምባሳደሩ ሰልፈኞችን ጋጣወጦች ቢሏቸውም፣ ህዝቡ በሰልፉ ለነበሩ ወገኖች ያለዉን አድናቆትና ክብሩን እየገለጸ ሲሆን፣ ብዙዎች በኤምባሲ የተሰቀለዉን ባንዲራ የሚያሳየዉንን ፎቶ የፌስቡክ ፕሮፋይላቸዉ እያደረጉ ነው። በርካታ በዉጭ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች፣ አክቲቪስቶችም በ ኤምባሲ የታየው በተጠናከረ መልኩ መቀጥል እንዳለበት ይናገራሉ።በጉዳዩ ላይ ያነጋግርናቸው የፖለቲካ ተንትታኝ “ በዲስም ሆነ እንደ ለንደን ብራሰልስ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ለአገራቸው፣ ለሕዝባቸውና ለባንዲራቸው ክብር የቆሙትን የሚያኮሩ ኢትዮጵያዉያንን “ጋጠወጦች” ብሎ ለጠራው የወያኔ ቅጥረኛ ግርማ ብሩ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል” ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ በኤምባሲ የታየው ህዝቡን ኤነርጃይዝድ በማድረጉ አንጻር ፣ ትግል ብዙ እርምጃ ወደፊት እንደወሰደው ይናገራሉ።

የአዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ ፣ ፋክት መፅሔትና ስራአስኪያጆቻቸው ጥፋተኛ ተባሉ

ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት ፤ ሀሰተኛ ወሬዎችን አሳትሞ በማሰራጨትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ በሚል ክስ የቀረበባቸው ሶስት መፅሔቶች እና የድርጅቶች ስራ አስኪያጆች ጥፋተኛ ተባሉ ።

ጥፋተኛ የተባሉት አዲስ ጉዳይ መፅሔት እና የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ፣ ሎሚ መፅሔትና የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ፣ ፋክት መፅሔትና ስራ አስኪያጅዋ ፋጡማ ኑሪያ ናቸው።

ቀደም ሲል የመፅሄቶቹ ስራ አስኪያጆችን ፖሊስ በአድራሻዎቻቸው አፈላልጎ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ በመግለፅ፣ ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ማድረጉንና በዚህም ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ባቀረብኩት ማስረጃ መሰረት ብይን ይሰጥልኝ ሲል አቃቤህግ መጠየቁ ይታወሳል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ የአቃቤህግን ማስረጃዎች በመርመር ነው ሶስቱ መፅሄቶችና ስራ አስኪያጆቻቸው ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን የሰጠው።

በዚህም መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍ መስከረም 27፣2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።


በጋምቤላ ክልል የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ አማሮች ወደ መኢአድ ቢሮ መጡ

ተስፋሁን አለምነህ
በፋሽሽቱ ወያኔ ከጋምቤላ ክልል በግፍ የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የተረፉት አማሮች ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መጥተዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ አቶ በለጠ ጌታቸው ጎጃም ቢቸና አካባቢ የመጡ የግራ እጃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በዚሁ ቀበሌ ከወሎ መካነሰላም ቦረና አካባቢ የመጡ አቶ ገበየሁ ኮስትር በጀርባቸው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ በጥይት ከተመቱ በኋላ ጥይቱ በሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በአካባቢው በተደረገላቸው ህክምና ጥይቱን ማውጣት ስላልተቻለ በከፋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይዳኑ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ጀምበሬ ኮስትር፣ ወ/ሮ ሳዓዳ ተፈራ፣ ወ/ሮ ኮከቤ ኮስትር ከእነ ህፃን ልጆቻቸው በባሰ ችግር ውስጥ ሆነው ወደ መኢአድ ጽ/ቤት በመምጣት በሰቀቀን ችግራቸውን ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃዮችና ከዘር ማጥፋት የተረፉት፤ እኛስ ከእነ ችግሩም ቢሆን የተወሰነ ድጋፍ አግኝተናል፡፡ ከዚያው የቀሩት ወንድሞቻችን ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ካሉ በኋላ ለእኛም ሆነ ለወንድሞቻችን የኢትዮጵያ ህዝብ በአሰቸኳይ እንዲደርስልን ሲሉ ተማጽነዋል፡፡


በትግራይ ኣፅቢ 5 ጣልያናውያንና 2 ኢትዮዽያውያን በሕወሓት ፖሊሶች ለሰዓታት ታገቱ።

በትግራይ ኣፅቢ 5 ጣልያናውያንና 2 ኢትዮዽያውያን በሕወሓት ፖሊሶች ለሰዓታት ታገቱ።
የህወሓት ፖሊሶች ጋዘጠኞቹን ኣግቶ፣ ፈትሾ፣ ኣንገላትቶ ለቋቸዋል።

ትናንት ሰኞ 19/ 01 / 2007 ዓ/ ም ለስራ ጉዳይ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በኣንድ ጣልያን የሚገኝ ቴሌቭዥን ጣብያ የሚሰሩ 4 ጣልያናውያን ጋዜጠኞችና ኣንድ ሌላ ኣገር ጎብኚ ጣልያናዊ ከሁለት ኣብሯቸው የሚሰሩ ኢትዮዽያውያን ጋራ ወደ ተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች የጎበኙ ሲሆኑ እገታው ያጋጠማቸው ወደ ኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ, ሩባ ፈለግ ቀበሌ የዓረና ኣባል የሆነው ኣቶ ሕድሮም ሃይለስላሴ መኖርያ ቤት በመሄዳቸው ነው።
የወረዳው ፖሊስ መኪናቸው ወደ ፖሊስ ጣብያ እንድት ሄድ በማዘዝ ከኣስተዳዳሪዎች ጋራ በመሆን ቪድዮና ፎቶ ካሜራዎቻቸው እንዲፈተሹ በማድረግ፣ ፓስፖርታቸው ፎቶ ኮፒ በማድረግ፣ ወደ የዓረናው ኣባል ለምን ጉዳይ እንደገቡ በመጠየቅና ታስረው እንዲያድሩ ብሎው ውሳኔ ኣስተላልፈው ነበር።
ኣምስቱ ታጋቾች ኣዲስ ኣበባ ወዳለው የጣልያን ኢንባሲ ደውለው በመነጋገር ማታ 2:30 ኣከባቢ ሊለቀቁ ችለዋል።የህወሓት መንግስት እነዚህ ጋዘጠኞች ኣግቶ፣ ፈትሾ፣ ኣንገላትቶ ከፌደራል መንግስት በተሰጠው ትእዛዝ ሊለቃቸው ተገደዋል።


ያለ ጠበቃ የተካሄደው የየሸዋስ፣ ኃብታሙ፣ ዳንኤልና አብርሃ ችሎት

ትክክለኛውን የቀጠሮ ቀን ለማወቅ አልተቻለም
(ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 20 ነው ሲሉ፤ ፖሊስ ጥቅምት 22 ነው ብሏል)

ዘሬ መስከረም 22/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ኃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ የአረና ም/ የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ፡፡ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ መቼ እንደተቀጠረ ያልታወቀ ሲሆን ችሎቱ ግቢ ሆኖ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ የችሎቱን ውሳኔ ከመዝገብ ቤት ጠይቆ እንዳይረዳ በፖሊስ ተከልክሏል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ቀጠሮውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ፖሊስ ቀጠሮው ጥቅምት 22 ነው ሲል ኮማንደር ተክላይ ቀጠሮው ለጥቅምት 20 እንደሆነ ገልጸውለታል፡፡

ችሎቱ 8 ሰዓት ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበር ቢሆንም የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ አያሌውና የአንድነት ም/ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዳንኤል ሺበሽ 10 ሰዓት እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሸዋስ አሰፋና የአረና ም/የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ 10፡30 አካባቢ ላይ ወደ ችሎት ገብተዋል፡፡

የዛሬው ችሎት ከእስከ ዛሬው በተለየ በርካታ ትዕይንቶች የታዩበት እንደሆነም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከእነዚህም መካከል እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች የበለጠ ህዝብ የተገኘበት ሲሆን ህዝቡም ለመጀመሪያ ጊዜ እየተፈተሸ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች በተለየ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ ታይቷል፡፡ በችሎቱ የሰማያዊና የአንድነት ሊቀመናብርት፣ ዶክተር ያቆብ ኃይለማሪያምን የመሳሰሉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች፣ የተለያዩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ዜጎች በችሎቱ ግቢ በመገኘት ለታሳሪዎቹ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ጋዜጠኞች ገብተው ችሎቱን መከታተል እንደሚችሉ ተገልጾ የነበር ቢሆንም በኋላ ግን እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአራቱ የፖለቲካ አመራሮች ጠበቆች የተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ ደንበኞቻቸውን እንዳያገኙ መደረጋቸው፣ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው በመሆኑና ህጉ የማይከበር በመሆኑ በጊዜ ቀጠሮ ለደንበቻቸው መቆም ስለማይችሉ ለጊዜው ለአመራሮቹ የሚያደርጉትን ጥብቅና በማቆማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡

ችሎቱ 11፡30 አካባቢ ያበቃ ሲሆን አጋርነቱን ለማሳየት ወደ አራዳ ምድብ ችሎት ያቀናው ህዝብ ታሳሪዎቹ ከችሎቱ ግቢ ከወጡ በኋላ እስኪርቁ በር ተቆልፎበት ችሎቱ ግቢ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊሲ ትመርምር

መስከረም 15 ቀን 2007 ዓም፣ የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦቦማና ባልደረቦቻቸው በአንድ በኩል ኃይለማርያም ደሣለኝና አለቆቹ በሌላ በኩል ሆነው የሁለትዮሽ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያደረጉት ንግግር የዲፕሎማሲ ጨዋነት ከሚጠይቀው ርቀት በላይ ተጉዘው ሸሪኮቻቸው ባልሠሯቸው ጀብዶች ማሞገሳቸው አሳዝኖናል። ፕሬዚዳንት ኦባማ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ያደረጉት ንግግር ላይ በርካታ ስህተቶች፣ ህፀፆችና ግድፈቶች የያዘ ከመሆኑም በላይ አንዳንዱ አስተያየት የኢትዮጵያዊያንን ክብር የሚነካ ሆኖ አግኝተነዋል።ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን የጀመሩት “ኢትዮጵያ በዓለም ከሁሉም በላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አገር ነች“ በሚል ዓረፍተ ነገር ነበር። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት የፈጠራ ቀመሮች በዓለም ባንክ በኩል ዞረው በሚስ ሱዛን ራይስ ተቀነባብረው በባራክ ኦባማ አንደበት መስማት የሚያሳፍር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኦባማ የተናገሩትን ዓረፍተ ነገር ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥና ራድዮ ደጋግሞ ሰምቶ ሰልችቶታል። ኦባማ፣ ይህ የተሰለቸ ዓረፍተ ነገር በእሳቸው አንደበት ሲነገር ስለሚሰጠው ትርጉም ጥቂት ቢያስቡ ኖሮ ለእሳቸውም ለአሜሪካም የተሻለ ነበር ብለን እናምናለን። “በአንድ ወቅት ራሷን መመገብ ያቅታት የነበረችው አገር ዛሬ ከፍተኛ እድገት የሚታይባት ሆናለች፤ አሁን የግብርና ብቻ ሳይሆን [የኤሌክትሪክ] ኃይልንም በመሸጥ በቀጠናው ቀዳሚነት ይዛለች” ሲሉ ያሞካሿት

Wednesday, October 1, 2014

የፓርቲዎቹ አባላት ጠበቃ ደረሰብኝ ባሉት ጫና ለጊዜው ሥራቸውን ማቆማቸውን አስታወቁ

በሕገመንግስቱ መሠረት ለደንበኞቼ አገልግሎት መስጠት አልቻልኩም፤ ከፍርድ ቤትና ከፖሊስም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል ያሉት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና ፓርቲ አባላት ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። ደንበኞቼ የምርመራ ቃላቸውን ለፖሊስ ከመስጠታቸው በፊት ላገኛቸው ሲገባ ይህ አልተደረገም ያሉት ጠበቃው፤ የጊዜ ቀጠሮው ችሎት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለቀጣዩ አንድ ወር ደንበኞቻቸውን እንደማያገኙና ሕግን ባልጠበቀ መንገድ ለሚከናወን ተግባር የፕሮፓጋንዳ ሽፋን መሆን እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለአንድነት ፓርቲ አባላቱ ለሀብታሙ አያሌውና ለዳንኤል ሺበሺ፤ ለአረናው አብርሃ ደስታ እና ለሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ ጠበቃ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኙ የነበሩ ሲሆን፤ ደረሰብኝ ባሉት ጫና እና ኢ-ሕገመንግስታዊ አሰራር ምክንያት ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለጊዜውም ቢሆን ማቋረጣቸውን ለፓርቲዎቹ አመራሮች መግለፃቸውን አስረድተዋል። ይህም በመሆኑ ሦስቱ ፓርቲዎች (ማለትም አንድነት፣ ዓረና እና ሰማያዊ) በእስረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት በተመለከተ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በአንድነት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።እንደማንኛውም ጠበቃ ደንበኞቼን ማግኘት ቢኖርብኝም፤ ላገኛቸው አልቻልኩም፤ በፍርድ ቤት የምናቀርባቸው አቤቱታዎች እና ስሞታዎች በሙሉ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ ይደረጉብናል፣ ይባስ ብሎም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር በመኖሩ ለስርዓቱ ሕጋዊ ከለላ መሆን አልፈልግም የሚሉት አቶ ተማም አባቡልጉ፤ በዚህም ምክንያት የታሰሩት የፖለቲከኛ እስረኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ ከለላ ማግኘት አልቻሉም ሲሉ ነገ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደሚያነሱ ምንጮች ጠቁመዋል።በጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ በጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡት ያለጠበቃ ቢሆንም፤ ምናልባትም ከወር በኋላ ዐቃቤ ሕግ ክስ የሚመሰርት ከሆነ፤ በችሎት ተገኝቼ ደንበኞቼን አገለግላለሁ የሚሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ፤ ደንበኞቼ ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት እኔን ማግኘት ሲገባቸው ሳያገኙኝና ቃላቸውን ሰጥተው ከፈረሙ በኋላ ባገኛቸው ምን አደርግላቸዋለሁ? ሲሉ ጥያቄ አዘል ኀሳባቸውን ይሰነዝራሉ። ከዚህም ባሻገር ደንበኞቼ ከተጠረጠሩበት ጉዳይ ውጪ በሆነ መልኩ የሚደረግባቸው ምርመራ በፓርቲ ጉዳይ ላይ ሆኗል ሲሉ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡት ጠበቃው፤ ለዚህም ጠንካራ አባል ማነው? የገንዘብ ምንጫችሁ ከየት ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው እንደነበር ደንበኞቼ ለፍርድ ቤት ቀርበውም አመልክተዋል ሲሉ ያስረዳሉ።      ይህም በመሆኑ የተላላኪነት ስራ ከመስራት ውጪ የምፈይደው ነገር የለም በሚል ለጊዜው ከደንበኞቼ ጋር መገናኘቱን አቁሜያለሁ ያሉት ጠበቃ ተማም፤ በዚህ አጋጣሚ ደንበኞችዎ ምን ሊያጋጥማቸው ይችላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “የሚደርስባቸው ሁሉ ደርሶባቸዋል፤ እኔም ኖሬ ምንም አይነት የሕግ ከለላ አላገኙም” ሲሉ መልሰዋል።