Saturday, May 17, 2014

የዛሬው የጋዜጠኞቹ እና የዞን 9 ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ – “ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ተደብድቤያለሁ”

አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገባ ከአዲስ አበባ
"የሥነ ልቦና ጫና ደርሦብኛል"
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዬርጊስ



ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስየተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ሦስት ሰዓት ይሰማል የተባለው ችሎት 4፡30 አካባቢ የተጀመረ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር118721 የተከሰሱት ሦስት ተጠርጣሪዎች ኤዶም ካሣዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያ ቀርበዋል፡፡

በዛሬው ችሎት ከእየአንዳንዱ ታሳሪ ሦስት የቤተሰብአባላት ወደ ችሎት ገብተው እንዲታደሙ ተፈቅዶነበር፡፡ ፖሊስ ክሱን ከወንጀል ወደ ሽብር ከፍ አድርጎቀርቧል፡፡ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩ የተጨማሪ የ28ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎም ለችሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡


የተከሳሽ ጠበቆች ግን ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሁለትቀጠሮዎች ውስጥ አጣራቸዋለሁ ያላቸው 6 ጉዳዮችአሁንም አልተሰሩም፤ ድርጊቱ ደንበኞቻችንን በቀጠሮማጉላላት ነው፣ ማስረጃ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ከወንጀል ወደ ሽብር የተቀየረበት መንገድም ተገቢአይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ፖሊስ መተርጎምያለባቸው ሰነዶች ወደ ትርጉም ቤት ተልከዋል፣ግብረአበሮቻቸው አድራሻ እየለዋወጡ ሊያዙልኝ አልቻሉም፣ አቀርባለሁ ያልኳቸውን
ምስክሮችም እያስፈራሩብኝ ለማቅረብ አልተቻለኝም ሲልመልሷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የ28 ቀናትየጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት ጋዜጠኞቹ እናብሎገሮቹ ቅዳሜ ሰኔ 7፣ 2006 ከጠዋቱ በ3፡30ሰዓት እንዲቀርቡ አዟል፡፡ አጥናፍ ብርሃኔ ከሌሊቱበስምንት ሰዓት ወደ ምርመራ ክፍሎች እየተወሰደበመርማሪዎች ወከባ፣ ድብደባ እና ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

ባለፈው ቀጠሮ ሚያዚያ 30 ቀርበው የነበሩት በፍቃዱ ኃይሉ እና አቤል ዋበላ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ
ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡ ቀጥሎ በታየው መዝገብ 118722 ተጠርጥረው የቀረቡት አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለምወልደየስ እና ዘላለም ክብረት ክሳቸው ወደ ሽብር ተለውጦ በመቅረቡ እነሱም ሰኔ 7 ቀን 2006 እንዲቀርቡ ታዟል፡፡ ለችሎቱ የመናገር እድል እንዲሰጠው ጠይቆ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ “መርማሪው የዞን 9 አባል አለመሆኔን ቢያምንም በተደጋጋሚ ጊዜ እየተጠራሁ አንድ ዓይነት በሆነ ጥያቄ ስለዞን 9 የምታውቀው ነገር አለና ተናገር እየተባልኩ ከፍተኛየሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል፡፡ ጋዜጠኛ እንደሆንኩም ያውቃሉ፡፡” በማለት ቅሬታውን እንባ እየተናነቀው አሰምቷል፡፡

የአስማማው ሁኔታ የችሎቱን ታዳሚያን እንባ አራጭቷል፡፡ ጠበቆቻቸውም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በጠየቃቸው ቀጠሮዎች የሰራውነገር ስለሌለ የ28 ቀን ቀጠሮ ሊሰጠው አይገባም፤ ዋስትና ይፈቀድልን፤ ዋስትና አያሰጥም እንኳን ከተባለ ፖሊስ ከዚህ በኋላበጠየቀው ጊዜ ምን ሊሰራ እንዳሰበ ይግለጽልን ሲሉ ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ መልስ የሰጡት መርማሪም በመረጃ ዴስካችንውስጥ ያለን ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ፋይል ለማጣራት ጊዜ ወስዶብናል ብለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ ተደራጅተዋል፤ ከእያንዳንዳቸው ኢ-ሜይል ለአመጽ የሚቀሰቅሱ ማስረጃዎች አግኝተናል እያንዳንዱለማስተርጎም ጊዜ ይወስዳል፤ በስማቸው ከውጭ የተላከ ገንዘብ እንዳለና ለሽብር ድርጊት ሊጠቀሙበት እንደሆነ ደርሰንበታል ያለቢሆንም ጠበቆቻቸው ግን ፖሊስ የጸረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ እየተጠቀመበት ነው፤ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ተስፋለምወልደየስ የዞን ዘጠኝ አባላት አይደሉም፡፡ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡

ደንበኞቻችንን ሊያስጠረጥራቸው የሚችል ወንጀል አልተገኘባቸውም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የዞን 9 አባላት ከውጭ የሽብር አካላትስልጠና አግኝተዋል የሚለው ልክ አይደለም፡፡ አርቲክል 19 እና ፍሪደም ሃውስ ሀሳብን የመግለጽ መብት እንዲከበር የሚንቀሳቀሱዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው፡፡ የትም ሀገር እና ቦታ የሽብር ተቋማት ተብለው አያውቁም፡፡ በኛም ሀገር በፓርላማ ሽብርተኛተብለው አልተወገዙም ሲሉ ጠበቆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱት በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌትፋንታሁን እና አቤል ዋበላ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ይቀርባሉ፡፡ ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ በቁጥጥር ሥርየዋሉት ሚያዚያ 18 እና 19 ቢሆንም ጠበቆቻቸው እንዲጎበኟቸው የተፈቀደው ግን ባሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 6 እና አርብ ግንቦት8፣ 2006 ነው።












No comments:

Post a Comment