የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የሬዲዮ ቢላል ጋዜጠኞችን ዳርሰማ ሶሪ እና ካሊድ መሁሃመድን ጨምሮ በተለያዩ 19 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የእስር ውሳኔ አሳልፏል።
ዳርሰማ ከህመሙ ጋር በተያያዘ 4 አመታት ከአምስት ወራት ሲፈረድበት፣ ካሊድ ደግሞ 5 አመታት ከስድስት ወራት ተፈርዶበታል።
በከድር ሙሃመድ የሱፍ መዝገብ በተከሰሱት ቀሪዎቹ ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ በጅምላ የ 5 አመታት ስድስት ወራት የእስር ውሳኔ አሳልፏል።
ሁሉም ተከሳሾች በሽብርተኝነት የተከሰሱ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ “ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ፍላጎት ነበራቸው” በማለት ጥፋተኞች አድርጓቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በሚያስተላልፍበት ወቅት፣ ተከሳሾች “ድምጻችን ይሰማ” የሚለውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የነጻነት መፍክር በማሰማት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።
ከተከሳሾም መካከል ኢብራሂም ቀመር፣ ፍጹም ቸርነት፣ ሸሃ ሱዲን እና ነስረዲን ኡስማን ቅሊንጦን እስር ቤት አቃጥለዋል ተብለው ተጨማሪ ክስ ከቀረበባቸው መካከል ይገኛሉ።
ጠበቃቸው አቶ ሙስጠፋ ሳፊ የተሰጠውን ፍርድ እንደማይቀበሉትና ይግባኝ እንደሚጠይቁላቸው ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment